Friday, July 22, 2016

ይድረስ ለጀግናው የጎንደር ህዝብ - የጀኔራል ኃይሌ መለሰ መልዕክት


የጎንደር ህዝብ ወንድሙን አሳልፎ የመስጠት ባህል የለውም። እኔ ከወረታ እስከ ባህርዳር በተደረገው ጦርነት በ1983ዓ.ም ሰባት ጊዜ ሰባት ቦታ ላይ ቆስዬ አዲስ አበባ ሄጀ ልታከም የሚል አጋጣሚ ሊኖረኝ ይችል ነበር፤ነበረኝም። ሂዶ መታከም እችል ነበር ያኔ ደርግ ጨርሶ አልፈረሰም ነበርና። ግን የነገሩን ማለቅ ስለተረዳሁት በቀጥታ በታንኳ ተሻግሬ ዘጌ አርፌ እንደገና ሌላ ታንኳ ይዤ እብናት ነው የገባሁት። እብናት ገብቼም ህዝቡ ትጥቁን እንዳይፈታ መጥቸልሃለሁ ትጥቅህን አትፍታ ነው ያልኩት ህዝቤን እና ብዙ ሽምቅ ተዋጊዎችን አደራጅቼ እየተዋጋሁ ለ5 ዓመታት ያክል ስዋጋ ቆይቻለሁ።
በዚያን ሰዓት በኔ በግል በደረሰብኝ ችግር፤ ቤተሰቦቼ ላይ በደረሰ ሰቆቃ፤ ወያኔ እኔን አሳልፈው እንዲሰጡ እንዲሁም አብረው በሚታገሉ ወገኖቸም ዘንድ የደረሰው ግፍ ይሄ ነው ተብሎ ሊገለፅ የሚችል አይደለም።ይሄ ሁሉ ችግር እያለብኝ ግን እጄን ለጠላቴ ለወያኔ አንስቼ ልሰጥ ፈፅሞ አልዳዳኝም። ወጣሁ ቆርጨው በአዲስ አበባ አቋርጨ ቀጥታ በኬንያ ነው የወጣሁት! ከኬኒያ እንደገና ሱዳን ገብቼ ነው ውጊያ የጀመርኩት።
ያገሬ ህዝብ ጎንደር እኔን አሳልፈህ እንዳልሰጠህ እንዲያውም የኔን ሞት እንደሞትክ ሁሉ የጀግናው ወንድማችንና ልጃችን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ህይወትም ማትረፍ መቻል አለብህ። እና አምኖ አድነኝ ብሎሃል፤ወንድምህ ነው አድነው፤ ተዋደቅለት። ሌላም ልጨምር! የምችለው ነገር ብኖር ሁሉም ሸዋ፣ወሎና ጎጃም እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄ ሁሉ ግፍና ሰቆቃ በአማራው ላይ የሚሆነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ስለሆነ አማራው ብቻ ሳይሆን መነሳት ያለበት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተነስተህ ይሄ ያገር ጠንቅ የሆነውን ወያኔ ንቀል፤ጊዜው አሁን ነው ተጀምሯል፤ከአሁን በኋላ ይሄ ነገር መክሸፍ የለበትም። ከዚህ በፊት ብዙ አጋጣሚዎች አምልጠውናል፤ይሄ ግን ሊያመልጠን አይገባም። በድጋሜ ይሄንን የመሰለው ወርቃማ ጊዜ ሊያመልጠን አይገባም እና ተነስ የኢትዮጵያ ህዝብ። ይህ የመጨረሻ ጥሪዬ ነው የማቀርብልህ።
በተለይ በተለይ የደቡብ ጎንደር ህዝብ ባለፈው ጊዜ ብዙ እንዳስቸገርኩህ አውቃለሁ። አሁን የማስቸግርህ ለመጨረሻ ጊዜ ነው፤ተነስ! ተነስ! ተነስ! ይህንንም ደግሞ ላንተው መዳን ሲባል ነው፤አንተ ህይወትህ እንዲቀጥል ነው የምለምንህ። እና እስከዛሬ እንዳላሳፈርከኝ ሁሉ ዛሬም እንደማታሳፍረኝ ፅኑ ዕምነቴ ነው።
በመጨረሻም የጎንደር ህዝብ ማድረግ የሚገባህን ተጋድሎ ሁሉ ማድረግ አለብህ። በምንም ታዓምር ወያኔን አሳፍረኸዋል፤ አሁንም ደግመህ ደጋግመህ አሳፍረው። ሌላውም ህዝብ ይሄንን የጎንደርን ህዝብ ማገዝ መቻል አለብህ። በምንም ተዓምር ወያኔ ሁልጊዜ አሸናፊ እየሆነ መውጣት የለበትም፤ይሄ የመጨረሻው መሆን አለበት። እያታለለ አንድ ጊዜ ኦሮሞውን፣ሌላ ጊዜ አማራውን፣ሌላ ሰሞን ደሞ አኙዋኩን እንዲሁም ሱማሌውን እየደበደበና እርስበርስ እያባላ የሚነግድበት ካርድ ለመጨረሻ ጊዜ ማቃጠልና ማስቆም አለብህ። ይሄንን መሰሪ ቡድን ማጥፋትና ነፃነትህን ማገኘት መቻል አለብህ።
ጀኔራል ሃይሌ መለስ።
ሐምሌ ፩፭ ቀን ፳፻፰

No comments:

Post a Comment