Tuesday, July 26, 2016

የጎንደር ሰላማዊ ሰልፉ


SHARE!
የማይቀርበት... የጎንደር ሰላማዊ ሰልፉ ብአዴኖችንም የሚያሳትፍ ነዉና ማንም እንዳይቀር!...ፈቃድ አግኝቷል። ሰልፉ በአማራ ህልዉናና ማንነት ላይ የተቃጣዉን የህወአት እብሪታዊ ንቀት ማዉገዝና የነፃነት ጥያቄ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ሲሆን እሁድ ሀምሌ 24/2008 የህወአት እኩይ የማን አለብኝነት የዘረኝነት የገዳይነት የዘራፊነት የአገርሻጭነት ጉድ ሁሉ ይወገዛል፤ ይዘረዘራል። 
መላዉ ተሰላፊ ህወአት በአገራችን በህዝባችንና ከኢትዮጵያዊ እስከ ብሄራዊ ህልዉናችን ያደረሰዉን አንድ አንድ የምናዉቃቸዉን በደሎች በኮምፒዉተር በማርከር በስክሪፕቶ እየፃፍን በየምንገኝባቸዉ ከተሞች እንጣለዉ።
የምንፈልገዉን መልእክት ሁሉ ፈለግነዉ መልኩና የፈለግነዉን ህወአት ያደረሰዉን በደል የሚገልፅ መልእክት እየፃፍን በየምንሰለፍባቸዉ አምስቱ ከተሞች ማለትም በጎንደር ባህርዳር ደሴ ደብረ ብርሀንና ማርቆስ በየመንገዱ መጣል ነዉ:: አንድ ሰዉ አንድ ገፅ ፅፎ አስፅፎ መጣል አለበት።ለምሳሌ:....የወልቃይት አማራነት ይከበር!!...የወልቃይት ህዝብ ሞት፣ ስቃይና እስር ይብቃ!.....አገራችንን አሳልፈን ለሱዳን አንሰጥም!..ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!....ህወሃት ውሸታም ነው!.....አባይ ወልዱ ለፍርድ ይቅረብ!!!...ወዘተ

No comments:

Post a Comment