"ሠላም ባስ" ጎንደር ላይ በእሳት ጋየ። "ሠላም ባስ" በነቀምቴ በእሳት ነደደ። "ሠላም ባስ" ጋምቤላ ጥቃት ደርሶበት ከ17 ሰዎች በላይ ተገደሉ። እውነት ነው። ምንም የሚገረም፣ በድንጋጤ እጅ አፍ ላይ የሚያስጭን ወይም ጭንቅላት የሚያሲዝ ጉዳይ አይደለም። ያለ አንዳች ጥርጥር ህወሓት እስካለ ነገም ከነገ ወዲያም "ሠለም ባስ" የጥቃት ዒላማ ይሆናል። አውቶብስ ሆኖ መንቀሳቀሱ እንጂ የትኛውም የህወሓት ንብረት በተቃውሞ ወቅት መውደሙ አይቀሬ ነው። ንብረት ቁስ ነው።
የሰው ልጅ ንዴት፣ ብስጭት፣ ቁጭት፣ ...በተለይ የሩብ ምዕተ-ዓመት (25 ዓመታት) ጭቆና ያበቀለው ንዴት፣ብስጭት፣ ቁጭት...ፈንቅሎ ሲወጣ ማብረጃው ቁሳቁስ ወይም ንብረት ላይ ከሆነ ብጹዕ ቁጣ፣ ጻድቅ ቁጣ፣ የተባረከ ቁጣ ነው። ገዳዩ ፊቱ እያለ አጠገቡ ያለውን ግኡዝ በቡጢ ቢነርት ሰውዬው ኃጢያተኛ እንዴት ሊባል ይችላል? ስለዚህ ጥያቄው መሆን ያለብት ንብረት ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንዴት እና ለምን መጣ እንጂ ለምን ቁስ ወደመ መሆን የለበትም። እንዴት፣ ለምን "ሠላም ባስ" ስለምን "ጦረነት ባስ" ሆነ ብሎ መጠየቅ::
አዲስ ነገር ጋዜጣ ለሥራ ልኮኝ ወደ ድሬዳዋ ተጉዤ አንድ የከተማዋ ታሪክ መሰጠኝ። ድሬን ከልጅነቴ ስለማውቃት የቤተሰቦቼ እና የማውቃቸው ሰዎች ሕይወት ከከተማዋ ጋር አብሮ እንዴት እየከሰመ እንደመጣ እንኳን እኔ ባቡሩ ጠንቅቆ ያውቀዋል። ግን ተቆርቋሪ ስለሌላት የሚናገርላት ያጣች ልሳነ ቢስ ባለቤት አልባ ከተማ ሆናለች።
ምድር ባቡር ፊት ለፊት ባለችው እና የከተማዋ ሰንደቅ በሆነች ሆቴል በረንዳ ቁጭ ብዬ እንደ እሳት የሚጋረፈውን ወላፈን ለመቋቋም ከቢራ ይልቅ ሻይ ሙቀቱን ይበርድልሀል ያለችኝን አስተናጋጅ ሰምቼ የማሽን ሻይ ፉት እያልሁ ላቤ በጆርዬና በግንባሬ እንደውሀ ሲወርድ ይሰማኛል። ይህን ስቃዬን የተመለከተ አንድ ከጎኔ ካለ ጠረጴዛ አጠገብ የተቀመጠ ሰው ስለሙቀትና ሻይ እያወራን፣ "ለሙቀት ቢራ ፍቱን ነው የሚሉም አሉ" እያለኝ በዚያች ቅጽበት ተግባባን። ድሬ እንኳን ሙቀቱ እና ሌላ-ሌላው... ድኅነትም ሕብረተሰቡን አግባብቶ ያለውን ተካፍሎ የሚኖርባት ከተማ ስለሆነች ከሰውዬው ጋር በቶሎ መቀራረባችን የሚደንቅ አልነበረም።
ሰውዬው ከተቀመጥንበት ሆቴል ማዶ የሚገኘው የኢትዮጵያና ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት Chemin De Fer Djibouto Ethiopien የባቡር ሾፌር ነው። እጁን አሻግሮ እየጠቆመኝ ባቡር ጣቢያው ፊት ለፊት የቆመውን አውቶብስ ተመለከትክው አለኝ። "ሠላም ባስ" ነው? አዎ:: አልኩት ከአዲ'ሳባ የመጣሁት በርሱ እንደሆነ እየነገርኩት። "የኛን እስትንፋስ አቁሞ እናንተን ከሀገር-ሀገር ያንቀሳቅስ" አለኝና አቀረቀረ።
ከአጠገባችን ቢራ እየጠጡ የሚዝናኑ ነጮችን እያሳየኝ እነዚህን ሶላቶዎችን (የሀገራችን ሰው በዘልማድ ጣሊያኖችን ሶላቶ ብሎ ይጠራቸዋል። በርግጥ በጣሊያንኛ soldato ማለት ወታደር ነው) አየኻቸው አለኝ። ለዓመታት ሥራውን አቁሞ የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ ገድሎ የነዋሪውን እስትንፋስ ያቆመውን ባቡር ሐዲድ ዝርጋታ ይሰራል ተብሎ ኮንትራት የወሰደው ኮንስታ የተባለ የጣሊያን ድርጅት ሠራተኞች ናቸው።
ሰውዬው ለረጅም ዓመታት በባለቤትነት ፍቅር የሰራበት ድርጅት መንኮታኮት ያበገነው በመሆኑ ጋዜጠኛ እንደሆንኩ እና ስለጉዳዩ ይበልጥ መረዳት እንደምፈልግ ስጠይቀው ይገርምህ ብሎ ባቡር ጣቢያው ቅጥር ግቢ አስገብቶ እያስጎበኘ እያንዳንዱን ታሪክ አጫወተኝ።
የኮንስታ ሠራትኞች የባቡር ፉርጎ በቅንጦት አሰርተው መኖርያ ቤታቸውን እዚያው አድርገው ቀን-ቀን የጥንቱን ሙሉ ብረት ሐዲድ እየነቀሉ ማታ-ማታ የድሬዳዋ መሸታ ቤቶችን ያካልላሉ። የተነቀለው የብረቱ ሐዲድ ሽርካቸው ለሆነው ለህወሓቱ መስፍን ኢንጂሪንግ ይላካል።
የድሮዎቹን፣ አረጁ_አፈጁ የተባሉትን ይተካሉ ተብልው ብዙ ሚሊየን ዶላር ፈሶባቸው ከቤልጂየም ተገዙ የተባሉት ባቡሮች ተበላሽተው በመቆማቸው የተወሰኑ ቀናት ወደጅቡቲ በሚደረገው ጉዞ ዕቃ የሚያመላልሱት የድሮ "ኦቶራይ" ባቡሮች ናቸው። የባቡር መግዣውን ገንዘብ ባለጊዜዎች ቆርጥመው በልተው የዛገ ባቡር ለሕዝቡ አምጥተዋል።
ከሌላ ቦታ ሥራ ያጡ፣ ኑሮ አልሰምር ያላቸው... የሰው እጅ ሳያዩ የሚኖሩባት የድኸዎች አልኝታ ከተማ ትባለ ነበር ድሬ፣ ድሮ::
"በፊት የምድር ባቡር ሠራተኛ ከሆንክ ልጁን እንዲድርልህ የጠየቅኸው ቤተሰብ ሳያመነታ ይድርልሀል።የተከበርን ሠራተኞች ነበርን:: ዛሬ ግን ሱቅ ሄደህ ብድር ስትጠይቅ የምድር ባቡር ሠራተኛ ከሆንክ ማንም አይሰጥህም። ብዙ ሺ ሠራተኛ ተባርሮ የቀረነው ደሞዛችን የሚደርሰን በየሁለትና ሦስት ወራት ነው። ባቡሩን ሲገድሉት የኛን ብቻ ሳይሆን የከተማዋንም ኢኮኖሚ ገደሉት። ድሬ እንደበፊቱ ደኸ ለተሻለ ኑሮ የሚመጣባት ሳትሆን ልጆቿ የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ጥለዋት የሚሄዱባት ከተማ ሆናለች። የኛም የከተማዋም ክብር ተቀማ" እያለ ድሮና ዘንድሮን እያነፃፀር ወደዋናው መውጫ በር ይዞኝ ሄደ።
እንደወጣን "ሠላም ባስ" ከአዲ'ሳባ የመጡ መንገደኞችን እያወረደ ነው። "ባቡር ቆሞ የድሬዳዋ ሕዝብ ጉሮሮ ተዘግቶ በህወሓት ጉሮሮ ቅቤ ይፈሳል" ሲለኝ ያላስተዋልኩትን ጉዳይ መልሼ እንዳጤን አስገደደኝ። ወደ ድሬ ስመጣ የተሳፈርኩት አዲ'ሳባ ያለው ለገሀር ፊት ለፊት ካለው የ"ሠለም ባስ" መናኸሪያ ነበር። ሾፌሩም ሁለት ረዳቶችም የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ከሩቅ በሚታየው ስክሪን ላይ የNational Geography የእንስሳት ፊልም ይታያል። በስፒከሩ ደግሞ ህወሓት በበረኸ እያለ ካመረታቸው የትግርኛ ሙዚቃዎች፣ በመሐል ቆንጆ-ቆንጆ ዘመናዊ ትግርኛ ዘፈኖች እያደመጥን እኔና አብሮኝ ያለው ባቡር ሾፌር ከቆምንበት መውረዴ ትዝ አለኝ።
"የድሬ ሕዝብ ይህን አውቶብስ ይጠላዋል" አለኝ። "ሕዝብን መናጢ ደኸ አድርጎ የትራንስፖርት ኢኮኖሚን ያለተቀናቃኝ ተቆጣጥሮታል።"
ምን ሠላም ባስ ብቻ?!
*መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጂሪንግ (ከአባይ ግድብ ጀምሮ)
*መሶቦ ሲሚንቶ (ከአባይ ግድብ እስከ በርካታ መንግስታዊ የሕንፃ ግንባታዎች)
*አዲስ መድኃኒት ፋብሪካ
*ሼባ ቆዳ ፋብሪካ
*ማይጨው ፓርቲክልቦርድ ማኑፋክቸሪንግ
*ኢዛና ማዕድን (ወርቅ!)
*ሳባ እምነበረድ
*አልመዳ ጨርቃጨርቅ
*ሱር ኮንስትራክሽን
*ሕይወት እርሻ ሜክናይዜሽን
*ብሩህ ተስፋ
*ትራንስ የጭነት ማመላለሻ (ጅቡቲ፣ ሱዳን )
*ጉና ትሬዲንግ (ቡና!)
ከላይ የተጠቀሱት በትግራይ መልሶ ማቋቋም EFFORT ስር ያሉ ሀገሪቷን የሚያልቡ የንግድ ድርጅቶች ናቸው።
በአንድ መንግስት ውስጥ ቁልፍ የሚባሉት የስልጣን ቦታዎች ውጭ ጉዳይ፣ መከላከያ፣ ደኅንነት እና አራተኛው መንግስት የሚባለው ሚዲያ:- ቴሌሺዥን ጣቢያውም ሆነ የግል ሚዲያ ፈቃድ ሰጪና ከልካዩ ብሮካስት ባለስልጣን በህወሓት ቁጥጥር ስር ነው። በአየር መንገድና ሌሎች መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ዋና ጥቅም እና የስልጣን ኃይል ካለባቸው ቦታዎች አንስቶ እስከ ቀበሌ ድረስ የህወሓት አባልት በተቆጣጠሯት ኢትዮጵያ ሌላው ሕዝብ ስው የለውም እንዴ ብሎ እስከመጠየቅ ያስደርሳል::
ለሌላው ምን ተሰጠው? ጥይት!
1.ሚያዚያ 1994 ሎቄ ላይ በሲዳማ ላይ የተፈጸመው 69 ሰዎችን የፈጀው እልቂት
2.ታኅሳስ 1996 ጋምቤላ ላይ የ423 አኙዋኮች ጭፍጨፋ
3. ሰኔ 1997 እና ኅዳር 1998 ከ250 በላይ የተገደሉበት እና ከ700 በላይ የቆሰሉበት የአዲሳባ ግድያ
4. ከ1999-2000ዓ.ም በኦብነግ ስም የህወሓት ሠራዊት በኦጋዴን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ከ1000 ባላይ ሰላማዊ ዜጎች ሲገደል የንብረት ዝርፊያና አስገድዶ መድፈር ፈጽሟል።
5.መጋቢት 2006 በአምቦ ተቃውሞ ከ50 በላይ ዜጎች በአጋዚ ጦር ሕይወታቸው ረግፏል።
6. ጥር 2007 በሐመር የግጦሽ መሬት ለምን ይወሰዳል በማለታቸው ከ10 ሰው በላይ ተገድለዋል
7. 2008 ዓ.ም የመሬት መብት ጥያቄ ባቀጣጠለው ሰላማዊ ተቃውሞ ከ400 በላይ ንጹሐን በኦሮሚያ ተገድለው በሺዎች ቆስለዋል
8. 2008 ኮንሶ የራስ አስተዳደር ጥያቄ በመነሳቶ 2 ሰዎች ተገድለው ከ200 በላይ ታስረዋል
9. 2008 ጎንደር:- ያለፈው የእስር ቤቱን ሳንቆጥር በሰሞኑ ግጭት ከ7 በላይ ሰላማዊ ዜጎች ተገድለዋል (በወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ እስከዛሬ የተገደሉትን ቤቱ ይቁጠራቸው)
*በትግራይ "ወልቃይት-ጠገዴ የትግራይ ነው" የሚሉ 2 ሰልፎች ክላሽንኮቭ አንግበው ፎክረው-ሸልለው በሠላም ወደቤታቸው መግባታቸውን ማስታወስ ያሻል::
በኔ የወፍ በረር ማስታወስ አቅም የተዘረዘሩት ጭፍጨፋዎች፣በየእስርቤቱ የሚፈጸምውን ሰቆቃ ሳንቆጥር፤ ህወሓትን በቃ ለማለት፣ ይሄ ዘረኛ ቡድን የትግራይ ሕዝብን አይወክልም ብሎ መቀሌ ሰማዕታት ሐውልት ጋር ሕዝባዊ ማዕበል ለማስነሳት ከበቂ በላይ ናቸው። ሌላውን እየገደሉ ንብረት ላፍራ እና የበላይ ሆኜ ልግዛ ማለት አለያም የሚገዛውን መደገፍ የንክ አዕምሮ ባለቤት መሆን ይጠይቃል። ንክ የሚያደርገው ዘረኝነት ነው። የዘረኛ ትርጉሙ እኔ የሌላው የበላይ ነኝ ማለት ነው። ይህ የእብደት ጎዞ መድረሻው ከ”ሠላም ባስ” ጥቃት ያለፈ የበቀል እልቂት ስለሚያስከትል የትግራይ ሕዝብ ህወሓት ለፈጠረው ሸለቆ ድልድይ ቢያበጅ ይሻለዋል። "በህወሓት ስም ትግሬ ላይ ተነጣጠረ፣ ህወሓት የትግራይን ሕዝብ አይወክልም" የሚል ብስጭቱን የህወሓት ንብረት ላይ ቢወጣ ጽድቅ ነው። ይበልጥ ንብረትን ሳይሆን ከሌላው የለያየውን ሥርዓት ንዶ ከ"ሠላም ባስ" በላይ ኢትዮጵያን ማዳን የጽድቅ-ጽድቅ ነው! ያኔ ሠላም የሚለው ቃል ከአውቶብስ ስም-ነት ባለፈ በሕዝብ መካከል ለተፈጠረ እውነተኛ ሠላም መጠሪያ ይውላል::
"እኛ እና እነርሱ" የሚል ግንብ በሕዝብ መሐል ያቆመውን ሥርዓት አፍርሶ፤ ሁሉም ዜጋ፣ ሁሉም ዘር እኩል የሚሆናባት ሀገር ለመፍጠር አልረፈደም:: የሚጠይቀው አንድ ጥበብ ብቻ ነው፣ ህወሓት ካጠለቀው የዘረኝነት ሠንሰለት መላቀቅ! የትግራይ ሕዝብ ህወሓት ከመሸገበት ልቡ ነቅሎ ለማስወጣት ድፍረትን፣ ዘረኝነትን ማሸነፍ፣ ስብዕናን ይጠይቃል።
ከዚያ "ሠላም ባስ" እና ሌሎች የህወሓት ንብረቶችን ለማውደም መሠረታዊ፣ ተጨባጭ እና አሳማኝ ምክንያቶች በርግጥም እንዳሉ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በቁጣ ንብረት የሚያጠፋ ሕዝብ የሞራል ልዕልና አለው። የዋህ ነው:: መብቱን ያጣ ፣ ነጻነቱን የተነፈገ፣ ማንነቱን የተነጠቀ ሕዝብ ፍትሕ በማጣቱ ቁሳቁስ ቢያወድም ያ ሕዝብ ጻድቅ ነው። ለዚያውም 25 ዓመታት ሙሉ ገዳዩን የተለማመጠ ቅዱስ ሕዝብ ነው። ፀፀት የለውም:: Righteous anger is typically a reactive emotion of anger over mistreatment, insult, or malice. It is akin to what is called the sense of injustice! Free from guilt or sin.
እናም ይኼ ሁሉ ሰብአዊ ፍጡር በአምባገነናዊ ሥርዓት ሲጨፈጨፍ አይቶ እናዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ "የህወሓት ንብረት ጥቃት ደረሰበት ብሎ አንደበቱን ሊያላቅቅ የሚሞክር ካለ፣ ያ ሰው ከነፍሰ-ገዳዮቹ ዘረኞች አንዱ ነው።
There are many transport companies but as you are stupid you single out selam bus .shame on you.
ReplyDelete