ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ከተቋቋመበት መሰረታዊዓላማዎች አንዱና ዋነኛው በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ኢ–ፍትሃዊና የአንድ ዘርየበላይነት አገዛዝ የሰፈነበትን አምባገነን ሥርዓት በማውገዝ እንዲሁም በመታገል ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ማለትም የዜጎችን እኩልነት የተረጋገጠባት፣ ሕዝብየሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ፣ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችየተከበረባትና የተረጋገጠባት ፣ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት፣ እንዲሁም ሁሉምየህብረተሰብ ክፍል በኩል አይን የሚታይባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመገንባትየሚደረገውን ህዝባዊ ትግል መደገፍና ብሎም በአጋርነት መቆም ነው፡፡
እኛ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አባላት የወያኔ መንግስትበመላው አገሪቱ ዜጎችን በማናለብኝነት ከትውልድ ቦታቸውና ከመኖሪያ አካባቢያቸው ማፈናቀልም ሆነ ይዞታቸውን በጠመንጃ አፈሙዝ መንጠቅ አንድን አገር አስተዳድራለሁያለን መንግስት ለሕዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል። ወያኔ ስልጣን በጠመንጃ ከያዘ ጀምሮበ መላው አማራ በጉራ ፈርዳ ፣ በጋምቤላ ፣ በኦሮሚያ ክልል በማስትር ፕላን ሰበብ፣እንዲሁም አዲስ አበባ ዜጎችን የመኖሪያ ቤታቸውን ከሀና ማርያም፣አቃቂ ቃሊቲ፣ላፍቶ ክፍለ ከተማና ሌሎችም አካባቢዎች ህዝብን ከይዞታቸውማፈናቀል አሁን ደግም በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን በጠመንጃ አፈሙዝ ለማፈን የሚደረገውን ትግል በማናለብኘነትና በአምባገነንነትየተወሰደና ሕገ ወጥ እርምጃ ነው ።
በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በጎንደር ከተማ ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን ተንተርሶ በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ቀደም ሲል በቤጌምድር በኋላም በሰሜን ጎንደር በአማራነቱ ተከብሮ የኖረ ሕዝብ ስለሆነ ወደ ትግራይ ክልል መካለሉንበመቃወም ጥያቄዉን በአግባቡ ያቀረበ ቢሆንም ይህን በሰላማዊ መንገድ ላቀረበዉ ጥያቄ አንባገነኑ የወያኔ ጉጀሌ ቡድን የሕዝቡን ጥያቄ በሃይልለማፈን የኮሚቴ አባላቱን ማሰርና ማፈን የቀጠለ ሲሆን ኮረኔል ደመቀ ዘዉዴ ለማሰር የሞከረዉን ሙከራ ተንተርሶ ሕዝብዊ ማዕበል/ቁጣ ተነስቷል።የሕዝብን ጥያቄ በሃይል ለማፈን እንደማይቻል ትላንት በኦሮሚያ የታየዉን ሕዝባዊ አመጽ ዛሬ በታሪካዊቷ ጎንደር ተደግሟል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት25 ዓመታት በአሸባሪውና በፋሽስቱ ወያኔ ቁጥጥር ሥር ከወድቀበትጌዘ አስቶ የፍዳ ዓመታትን እያሳለፈ ሲሆን በእነዚህረጅም የመከራ ዓመታት አንድም ቀን ወያኔን ከመታገል የተቆጠበበት ጊዜ ግን አልነበረም:: ወያኔ የማህበረሰቡን እሴት በቁጥጥር ስር ለማስገባትበአካሄደው አረመኔያዊ ድርጊት አሉ የሚባሉትን ማህበራዊ እሴቶቻችንን በሙሉ ተራ በተራ ያፈራረሳቸዉና በራሱ አሻንጉልቶች በመተካት ፀረማህበረሰብ ዘመቻውን በሰፊው ገፍቶበታል። ይህ አንባገነን ሥርዓት ኢትዮጵያ እንደሃገር ሕዝቧም እንደ ሕዝብ ቀድሞ በነበረዉ ሃገራዊ ትስስርእንዳይቀጥል ለእኩይ ዓላማዉ ሲል ብቻ የሃገሪቷን ሕዝቦች በዘርና በቋንቋ በመከፋፈል የሃገሪቷን ሕዝቦችን ሲያጣላና እርስ በርሳቸዉእንዳይተማመኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሰራና በሃገሪቷ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦች ወይም ብሄረሰቦች ከራሳቸው ዘር ውጭ ሌላውን ማመንየማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እየገቡ ለመሆናቸው በቅርቡ እየተፈፀሙ ያለው ድርጊት ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። በጋራ ሁላችንም በሰውነታችን ብቻልንቀበላቸው የሚገቡ፣ ዘርን፤ ቋንቋንና ባህልን ተሻግረው ሊያስተሳስሩን የሚገቡ ጉዳዮቻችንን እያፈራረሳቸዉ ይገኛል።
የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በህዝብ ያልተወከለ አገሪቱን የግዛት አንድነት ያላስጠበቀ፤ የሃገሪቷን አኩሪ የነፃነትና የአንድነትን ታሪክ ገድል የካደናየናደ እኩይ ቡድን ስለሆነ ይህ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ ላይ ማስወገዱ አማራጭ የሌለዉ ወቅታዊና ሃገራዊ ግዴታ መሆኑን ዲሞክራሲያዊ ለዉጥበኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በጽኑ ያምናል። በወልቃይት ጠገዴ መሪዎች ላይ ይህ አንባገነን ታጣቂዎችን ከትግራይ ወደ ጎንደር በመላክየኮሚቴ አባል የሆኑትን ኮለኔል ደመቀንና ሌሎችንም ለማፈን እንዲሁም ላለፉት ዓመታቶች በወልቃይት ጠገዴ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች ላይ የጦርሀይል፤ ደህንነትና ፖሊሶችን በማዝመት ጥያቄዉን ለማኮላሸት ቢሞክርም የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄዉን እንዲያቀርቡለት የመረጣቸዉየኮሚቴዉ አባላቶች ለሚደርስባቸዉ ወከባና እንግልት ሳይበገሩ የተጣለባቸውን አደራ ያለማወላወል በመጠበቅ ባካሄዱት አኩሪ የትግል ገድልኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ታሪኩን በወርቅ ቀለም ፅፏል። ዘረኛው ወያኔንና ተባባሪዎቹ የማይገባቸውና እስከ ዛሬ ያልተረዱት የሕዝብ ፍላጎት ብሎምቁጣንውን አሻፈረኝ አልገዛም ብሎ ማመጽ ወቅቱ ጠብቆ የሚመጣ ክስተት ነው። የወያኔ መንግስት ይሄንን ሕዝባዊ መነቃቃት ለማጥፈት በሌሎችምላይ እንደሚያደርገው ሁሉ የተለያዮ ዘዴዎችን በመጠቀም ያላሰለሰ የሞት ሽረት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።አሁንም በተግባር እየፈፀመ ነው።
ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አምባገነኑ ህውሃት(ኢህአዴግ) በሰላማዊና በንፁሃን ዜጐች ላይ የወሰደውን ኃላፊነትየጐደለው እርምጃ አጥብቀን እያወገዝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነቱን ወደ ጐን በመተው ይህንን ዘረኛ ና አምባገነን ስርዓት ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜበላይ ተባብሮ እንዲነሳ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊያሰሙ በወጡ ዜጎች ላይ የወሰደውን አረመኔያዊእርምጃ በጥብቅ እያወገዘን የጎንደር ሕዝብ እያደረገ ያለውን ፍትሃዊ ትግል ሙሉ በሙሉ እንደግፋለን።ለተጀመረው የነጻነት ትግል ዴሞክራሲያዊለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አጋርነቱን ይገልጻል።
ወያኔ በማስወገድ የሃገራችንን አንድነትና ዳር ድንበር እናስከብር!!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!!!
No comments:
Post a Comment