Tuesday, July 19, 2016

መረጃ... ጎንደርን ለማንበርከከ ፕላን ኤ. ፕላን ቢ. ፕላን ሲ. ቦንብ ተጠምዷል!!



የኢትዮጵያ የብሐራዊ መረጃንና መከላከያ ሰራዊትን ወታደራዊ ደህንነት ዋቢ ባደረገ መልኩ በጎንደር የአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚጠይቅ ረቂቅ እንዲጸድቅ ለሚመለከተዉ ተባባሪ አካል ተሰናድቶ ቀርቧል።
በዚህ ረቂቅ ዉስጥ የሐገሪቷ ክልላዊ መንግስታት እና የኢሃዲግ እህትማማች ድርጅቶች ወይም ፓርቲዎች አመጹን ማዉገዛቸዉ አበክሮ የተገለጸ ሲሆን በጎንደር የተቀናጁ የሽብር ሐይሎች መንግስት በህጋዊ መንገድ የሚፈልጋቸዉን ግለሰቦች ለህግ እንዳይገዙ ሽፋን በመስጠት በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ እርምጃ በመዉሰድና የሀገሪቷ ሐብትና ንብረት ላይ ጥቃት በመፈጸም ከፍተኛ እረብሻ ፈጥረዋል ይላል፡......
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ላይ የተቀሰቀሰዉን ሁከት ለማብረድ የክልሉ ፖሊስ እና ልዩ ሐይል ህግ የሚፈልጋቸዉን ግለሰቦች ከህዝብ በአደራ ተቀብያለዉ በማለት ለፌደራል መንግስት የማስረከብ ፍላጎት ባለማሳየቱ ጉዳዩ እየተካረረ በመምጣት ላይ መሆኑን አክሎ ይገልጽና ጉዳዩ አስቸኳይ እልባት እንዲያገኝ ከማሰብ አንጻር የሐይል አማራጭ ለመጠቀም እንዲቻል በጥብቅ ያትታል!!!!!!!!!!!።
በመሆኑም የሐይል አማራጭ ለመዉሰድ በሚቻልበት መልኩ የመከላከል ይልና በቅንፍ ዉስጥ ( ሐገር የማዳን ) ተግባር ለመፈጸም የፌደራል ፖሊስ ( የአጋዚ ) ሰራዊት በጎንደር ቁልፍ ቁልፍ ስፍራዎች ላይ በተጠንቀቅ እንደሚገኙ ይጠቅሳል።
ዉድ ኢትዮጵያዊ ወገኔ ይህ ፍንጭ እጅግ ቁልፍ ከሆኑ የብሔራዊ መረጃ ወገኖቻችን የተገኘ መሆኑን እየጠቀስን ፕላን ኤ....በድርድር ፕላን ቢ... በሐይማኖትና በሐገር ሽማግሌዎች ፕላን ሲ... ከፍተኛ በሆነ የሐይል አማራጭ ተጠቅሞ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አማራዉን ለማኮላሸት ባለዉ በሌለዉ ሐይሉ መነሳቱን ጠንቅቃችሁ እንድትረዱት በጥብቅ እናሳስባለን።
ድል ለኢትዮጵያዊያን ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment