Thursday, July 21, 2016

ሰበር መረጃ... በህወሃት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዉስጥ የነበረዉ ጉምጉምታ ወደ ተግባራዊ ተቃዉሞና ፍጥጫ እየተሸጋገረ እንደሚገኝ ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።



የወታደራዊ ፖለቲካ መምሪያ እና የፕሮፓጋንዳ ክፍሎች ምንጭ እንደሚያመለክተዉ በሰሞኑ ጎንደር ላይ የተገደሉትን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ትዉልድ ቦታቸዉ ተወስደዉ በክብር መቀበራቸዉ ተንተርሶ በሰራዊቱ ዉስጥ ቅራኔ ተፈጥሯል!.....ይህዉም 
1. ከሟቾች ዉስጥ ትግሬ የሆኑ አባላት ስላሉበት ነዉ የቀብሩ ስነ ስረአት በክብር የተከናወነዉ.....!
2. ዉስጥ ዉስጡን የሚሰራ የብሔር ማናከሱ ደባ በአማራ የተገደሉ ትግሬዎች ናቸዉና ትግሬ የሆንክ ሁሉ ለዘላቂ መኖርህ ሕልዉና ስትል ከህወሃት ጋር እስከ ሞት ድረስ ቁም የሚል የጽንፍ መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ ነዉ።
የሚሉ ሲሆን ሰራዊቱ በሶማሌያ፣ በኤርትራ፣ በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በጋንቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በተለያዩ የቦርደር አካባቢዎች ሲገደሉ ወይም ሲሰዉ የመከላከያ አባላቶቹ ከነመፈጠራቸዉም ስማቸዉ ተነስቶ አይታወቅም።
ይህ ለምንና እንዴት እንደሆነ ባለስልጣናት የሆኑ የህወሃት አመራሮች ሲጠየቁ ህወሃት ከጅምሩ ወታደሮችን በሞቱበት ስፍራ የመቅበር ባሕል አላት ብለዉ ይቀልዳሉ በማለት ማጉረምረሙ ወደ ቅራኔ እየተቀየረ መምጣቱን ለመረዳት ምንጮች ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና በአሁኑ ወቅት በጎንደር የተከሰተዉን የህዝብ መከላከል ተንተርሶ ህወሃት ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቀ ሲሆን በተጨማሪ በዚህ ሁለት ቀናት ዉስጥ በጎረቤት ሐገር ቦርደር አካባቢ የህወሃት 24ተኛ ክ/ጦር ድንገተኛ ጥቃት ደርሶበታል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment