የሚለውን በስፋት መረጃ ለማፈላልግ ሞክሬ ነበር የፈለኩትን ያክል አጥጋቢ ነገር ማግነት አልቻልኩም ምናልባትም ስነሱ የጠለቀ እውቀት ያለው ይህንን ያነበበ አንባቢ እኔ ማግኘት ያልቻልኩን ( ጎደሎውን ሞልቶት ) በስፋት ሊያስቃኘን ይችላል የሚል እምነት አለኝ በኔ በኩል ያገኘሁትን እነሆ
የመቶ አለቃ ማስረሻ ሠጤ የትወልድ ሀገር ከጀግናው በላይ ዘለቀ ሀገር ጎጃም ነው እሱ የተወለደባት ቦታ ምዕራብ ጎጃም መርጦለማሪያም ሲሆን የት እንደተማረ እና መቼ አየር ሀይልን እንደተቀላቀለ ባለውቅም ከፎቶው መረዳት የምንችለው በዘመነ ወያኔ ይመስለኛል
ይህ ሠው ለእስር እስከተዳረበት ታህሳስ 2007 ዓም ድረስ በኢትዮጵያ አየር ሀይል ድሬደዋ አየር ሀይል ምድብ ይሰራ እንደነበረ ለማወቅ ችያለሁ ከእሱ ጋር ቅሊንጦ ታስረው የነበሩት እንዳጫወቱን ለሀገር ያለው ጥልቅ ፍቅር የተለየ ነው በአየር ሀይል ውስጥም የህወሓት አገዛዝ አጥብቆ ይተች እንደነበረ ለመታሠሩም ምክንያት ይኸው ሳይሆን እንደማይቀር ይታመናል ቅሊንጦ እስር ቤት ውስጥ የሚደርሰውን አስከፊ የእስረኛ አያያዝ በተመለከተ አምርሮ ይቃወም እንደነበረ ሠምቻለሁ አሳሪዎቹ ሌሎች እስረኞችን ያነሳሳል የሚል ስጋት ውስጥ እየገቡ ተደጋጋሚ ቅጣት እንደተቀጣ በመጨረሻም ከግንቦት 27/2008 ዓም ጀምሮ ከሰው ተገልሎ ለብቻው እንዲታሰር ተደርጓል ፡፡
መቶ አለቃ ማስረሻ ለእስር የተደረገው ብቻውን አይደለም ከሱ ጋር አብረው ይሰሩ የነበሩ የአየር ሀይል አባላት ጓደኞቹም ለእስር ተዳርገዋል ስማቸውንና የመጡበትን አካባቢ ያወኳቸው የሚከተሉት ናቸው
1, መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ም/ብ ጎጃም
2 ,መቶ አለቃ ዳንኤል ግርማ የናዝሬት ልጅ
3, መቶ አለቃ ገዛኸኝ ድረስ የጅማ ልጅ
4, መቶ አለቃ ብሩክ አጥናየ የአዲስ አበባ ልጅ
5, መቶ አለቃ አንተነህ ታደሰ የናዝሬት ልጅ ናቸው
ከአንድ እስከ አራት ያሉት በመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ሲሆን አንተነህ ታደሰ ለብቻው የተከሰሰ ነው
ሁሉም ተከሳሾች ላይ የቀረበባቸው ክስ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር ሀይል የሆነ የጦር አውሮፕላን ይዘው ከሀገር ለመወጣት አሲረዋል እንዲሁም መንግሥትን በጠመንጃ ለመቀየር በኤርትራ ካሉ ሀይሎች ጋር በመገናኘት ወዘተ የሚል የሽብር ክስ ቀርቦባቸዋል ፡፡
ተከሳሾቹ በአሁኑ ሠአት ቅሊንጦ እስር ቤት ይገኛሉ መቶ አለቃ ማስረሻ ሠጤ ታስሮ በሚገኘበት ቅሊንጦ ዞን ሁለት ከግንቦት 27/2008 ዓም ጀምሮ ለብቻው ጨለማ ቤት እንዲታሰር መደረጉን ለማወቅ ችያለሁ
መቶ አለቃ ማስረሻ ሠጤ እና ሌሎች ይህንን የግፍ አያያዝ በመቃወም ከአንድ ሳምን በፊት የምግብ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ታውቋል በአሁኑ ሰዓት እጅግ በጣም በመዳከማቸው እዛ ክፍላቸው ውስጥ ጉልኮስ እንደተሠጣቸው ተገልጿል ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ አስከፊ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለኝ ፡፡
በመጨረሻም ለአሳሪዎች የማስተላልፈው መልክት ዜጎችን በግፍ ማሰራችሁንና ማሰቃየታችሁን አቁሙ በሠው ልጅ ላይ የምትፈፅሙትን ግፍ በቶሎ አቁሙ ና ከኢትዮጵያ ህዝብ ቅጣት አምልጡ ይህንን በማድረጋችሁ ከራሳችሁ አልፎ ለልጆቻችሁ የምታስተላልፉትን ግፍ እና ቅጣት ትንሽም ቢሆን ትቀንሳላችሁ ፡፡
No comments:
Post a Comment