Sunday, July 24, 2016

“ግማሹ መሬቱን… ሌላው ማንነቱን በወያኔ ሲነጠቅ!!” – ከአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማኅበራት ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ

  australia ethiopiansበኢማማምአ የተሰጠ መግለጫ!! ግማሹ መሬቱን... ሌላው ማንነቱን በወያኔ ሲነጠቅ!! እ.ኤ.አ 21/07/2016 በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እነ ከተማ ይፍሩና እውቁ ደራሲ አዲስ ዓለማየሁ ከዚያ ዘመን ትውልድ ራሳቸውን እጅግ በጣም ተራማጆች አድርገው ይቆጥሩ ስለነበር በወቅቱ በምሥራቁ አውሮፓ የተራማጅነት ምልክት ተደርጋ የምትቆጠረውን ቀይ ባጅ (ምልክት) በእግራ የደረት ኪሳቸው ላይ ይሰኩ እንደነበር የዚያ ትውልድ መጻጽፎች በዋቢነት የሚጠቀሱ ሲሆን እንዲሁም በዓለማችን የተለያዩ ጠንፍ ላይ የሚገኙት እነ ቸጉቤራና ሆቺሚን የኢትዮጵያን የአምስት ዓመት የአርበኝነት የነፃነት የሽምቅ ውጊያ ስልትን ለነፃነት ትግላቸው በያሉበት በዋቢነት መጠቀሙ እንዳለ ሆኖ የቸጉቤራ ለሰው ልጆች እኩልነት ሲል (በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ቅኝት ለማለት ነው) የወጣ የወረደባቸው ጋራ ቁልቁለቶችና የዘመራቸው የእኩልነት መዝሙሮች እንደ ሰደድ እሳት በአዲሱ ትውልድ ሕሊና ውስጥ በመቀጣጠላቸው በሂደት በ1960ቹ አጋማሽ አካባቢ በነ አዲስ ዓለማየሁ እግር የተተካው ኢትዮጵያዊው ወጣቱ ምሁርና በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች እጅግ በጣም ቀልብ የሚስቡ ብሔራዊ መፈክሮችን አንግበው ለአብነት ያህል "መሬት ላራሹ፣ ሕብረተሰባዊነትና እኩልነት፣ ሕዝባዊ መንግሥት፣ ወ.ዘ.ተ" የመሳሰሉትን በግልጽና በድፍረት በአደባባይ ያስተጋቡ ነበር:: እርግጥ ነው “የመሬት ላራሹና የእኩልነት” መሠረታዊ የሕዝብ ጥያቄዎች ዛሬም ድረስ ሰሚ ጀሮ ያጡ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ይበልጥ እየተደፈጠጡ ያሉ መሆናቸው እንዳለ ሆኖ ያ የምሥራቅ አውሮፓ የፖለቲካ ቅኝት ለአገራችን ወጣት ፖለቲከኞች ባይታወር እንደነበር በሂደት የታየ ቢሆንም ቅሉ በዚያ የታሪክና የፖለቲካ ምዕራፍ ወቅት ግን እነዚያ መፈክሮች የወጣቱ ትውልድ የትግል ማዕከል ሆነው ወደ አደባባይ መውጣት በመቻላቸው ያ ጠንካራ ወጣት ትውልድ መተኪያ የሌላትን አንድና ክቡር ሕይወቱን ሳያመነታ ቤዛ ሲያደርግባቸው የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንዲሉ ከየትምህርት ተቋሙ በችሎታ ማነስ የተባረሩና የኋላ ጀርባቸው በጠንካራ ኢትዮጵያዊነት ፍቅር ላይ ችግር ያለባቸው የትግራይ ተወላጆች የተሰባሰቡበት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት (ት.ህ.ነ.አ.ድ/ያሁኑ ሕ.ወ.ህ.ት - ወያኔ) በሚል የካቲት 1968 ዓ.ም የትግል ማንፌስቶአቸውን ሲያወጡ ብዙ ሰማዕታት ራሳቸውን ቤዛ ላደረጉበት ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ አንድነትና እኩልነት ሳይሆን ነፃ የሆነች ታላቋን ትግራይን ለመገንባት በክፉ ቀን አስጠግቷቸውና ሰርተው በክብር የሚበሉበትን የጎንደር ክ/ሀገር የግዛት አካል የሆኑትን ወልቃይትንና ፀለምትን (በሂደት ደግሞ ከፍታው ሁመራንና ፀገዴን) በስም በመጥቀስ የትግራይ የግዛት አካል ናቸው በሚል ነበር:: እንዲሁም የወሎን እንደ-መሓሪ፣ ራያ አዘቦ፣ ወፍላና አላማጣን በ1983 ዓ.ም በጭካኔ ወደ ትግራይ በማካተት በአማራው ሕብረተሰብ ላይ እጅግ በጣም ዘግናኝ የግድያና የማፈናቀል ወንጀሎችን ሲፈጽሙ ኖሩ:: ወያኔ በወቅቱ የማታጋያ ማንፌስቶውን ሲያወጣ የጎንደርንና የወሎን ለም መሬቶች በሕገ-ወጥነት ወደ ትግራይ ለማጠቃለል ከመወሰን ባሻገር አማርኛ ተናጋሪው ሕብረተሰብ ለትግራይ ሕዝብና ለመሰረቱት ጠባብ ድርጅታችው ሕ.ወ.ህ.ት ዋነኛ ጠላታቸው ተደርጎም ነው:: በመሆኑም ወያኔ ከተመሰረተበት ዘመን 1968ዓ.ም ጀምሮ በአማራው ኅብረተሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ወንጀል መሬቱን በመንጠቅና ልጆቹን በማሳደድ ብቻ የተገደበ ሳይሆን በተለያዩ ስልቶች ዘሩን ማጥፋትና ቀሪውንም የአማራነት መገለጫ የሆኑትን ቋንቋውን፣ ታሪኩ፣ ባሕሉንና በአጠቃላይ ማንነቱንም በመክዳት ጭምር መሆኑ ነው:: መለስ ዜናዊ ከጡት አባቱ ፕ/ር እንድሪያስ ሸቴና ፕ/ር መሥፍን ወ/ማሪያም ጋር ከሰኔው 1983 ዓ.ም የወያኔ የሽግግር መንግሥት ምስረታ ማግስት በተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይና ስለሽግግር መንግሥት ተብዮው ቃለ መጠይቅ ባደሩጉ ግዜ ከራሱ ጋዜጠኞች "ለምን የአማራን ብሔር የሚወክ አካል በሽግግር መንግሥቱ ምስረታ አልተሳተፈም?"ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ "አማራ እኛ ጭቁኖች የምንወስንለትን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ አለበት" በሚል በትዕቢት እንደመለሰ በተለያዩ የብዙሃን መገንኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር መደመጡን ልብ ይላሉ:: ለማስታወስ ይረዳ ዘንድ በዚያው ቃለመጠየቁ ግዜ ነበር "ኢትዮጵያውያንን በዓመት ለቅያር ልብስ እንዲበቁና በቀን ሦስት ግዜ ጠግበው እንዲመገቡ እናደርጋለን" ያለው!! እርግጥ ነው ደርግ ከመውደቁ ትቂት ዓመታት በፊት በተደረገው ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ 27 ሚሊዮን የነበረውን የአማራ ኅብረተሰብ ቁጥር (በወያኔ አስተዳደር 10 ሚሊዮኑ ይፋ ግድያ ተፈጽሞበት አሁን ወደ 17 ሚሊዮን የወረደው)ን ወክሎ በሽግግር መንግሥታቸው የሚቀርብ አንድም አካል አለማሳተፋቸው ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጉዳይ ላይ ወያኔ መድረክ መሪ ሆኖ መቅረቡ "ጊዜ የሰጠው ቅል ዱባ ይሰብር" ሆነና ነገሩ ስለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅነነትና ጥቅም ኢትዮጵያን ወክሎ የሚቀርብ አንድም የፖለቲካ ድርጅት በመካከላቸው ለይምሰል እንኳን እንዲሳተፍ አለመደረጉ ጭምር እጅግ በጣም የሚገርም ነው:: እናም ሁሉም የተሰባሰቡት ወያኔ ደደቢት ላይ አስቀድሞ የቀረጸውን "ፍትሕ አልባ የክልል አከላለል" ይቀበላሉ የሚባሉትን ብቻ ለይቶ ሲሆን በሂደት ደግሞ ለንግሥናው የተጠቀመበትንና - the king maker ተብሎ ዛሬም ድረስ የሚታወቀውን - ለግል ሥልጣኑ እያሰጋኛል ያለውን የኦሮም ነፃነት ግንባርን (ኦነግ)ን እንደ ክፉ አውሬ ከሽግግር መንግሥት ተብዮው አባሮ ወያኔ ሁሉንም ለብቻው የገፋበትና በመንግሥት ሰም አገር እያተራመሰ ያለ በአጽሙ የቀረ ነውረኛ የጎሳ ድርጅት መሆኑ ነው:: ይህም በመሆኑ ወያኔ በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ብርቱ የሎጀስቲክና የመረጃ እገዛና የዓለማችንን የኃይል አሰላለፍ ክፍተት በማሳበቅ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በ1983ዓ.ም እንደወረረ በአገሪቷ ምሥራቅ፣ በደቡብና ምዕራብ በሚኖሩ የአማራ ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ ከቶ ስንት ዓይነት የዘር ማጥፋት ወንጀል በስውርና በይፋ አካሄደ? ስንቶችን በቤታቸው ውስጥ እንዳሉ በውድቅት ሌሊት እሳት ለኮሰባቸው? ስንቶችንስ በጸራራ ፀሓይ ወደ ገደል ወረወራቸው? ስንቶችንስ ቤት ንብረታቸውን በመቀማት የአማራ ክልል ወደ ሚለው ያለ ምንም ርህራሄ አባረራቸው? ስንቶችንስ በዶ/ር ቴድሮስ አዳህኖም በቤተሰብ እቅድ መምሪያ ስም በመርዛማ መርፌ በመውጋት የእናትነት ክብር ማዕረጋቸውን ጭራሹን መና አስቀረው? ስንቶቹስ በቤተሰብ እቅድ መምሪያ ስም በዘመን አመጣሹ ኤድስ ቫይረስ ሆን ተብሎ እንዲለከፉ በማድረግ እንዲሞቱና ቁጥራቸው እንዲመናመን (deliberatly exterminated and depopulated) ተደረገ? ስንቶቹስ 10 የወባ ከኒን አጠው በወባ ትንኝ እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ተደረገ? በአጠቃላይ ግድያው፣ ግፉና መከራው የትየለሌ ሆኖ ተፋፍሞ በመቀጠሉ ይሄውና አሁን ደግሞ በአማራ የማንነት ጉዳይ ላይ ከ11 ግዜ በላይ ወደ አ/አበባ ለአቤቱታና ለደጅ ጥናት በሰላማዊ መንገድ ይመላለሱ በነበሩት የወልቃት-ሁመራ-ፀለምትና ፀገዴ የማንነት ኮሚቴ አባላት ላይና በጎንደር ሰላማዊ ሕዝብ ላይ ይፋ የሆነ የግድያ ወንጀል እይፈጸመ ይገኛል!! ከቶ ሰንት ግዜ ነው በጋምቤላ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ ይፋ ይሆነ ጭፍጨፋ፣ የመሬትና የልጆች ነጠቃ ድርጊት የተካሄደው? ወይስ በኦጋዴንና በአፋር ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ? ወይም ካለፈው ኅዳር ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የከፈተው ዐይን ያወጣ ወረራ፣ ግድያና እስራት መቆሚያው ከቶ የት ይሆን? ለመሆኑ ስንት ግዜና እስከመቸ ድረስ ነው ወያኔ ሕዝባችንን እርስ በእርስ በቋንቋና በጎሳ ከፋፍሎ በተለያዩ ቦታዎችና በተላያዩ ግዜያት እንዴ ተኩላ ነጣጥሎ ሲፈልግ መሬቱን አልያም ማንነቱን እየነጠቀና እየጨፈለቀ የሚቀጥለው? ወይስ ስንት ግዜ ነው የትግራይ ሕዝብ ታጥቀህና ተጠንቅቀህ ‘የደርግ እርዝራዦችን’ ተጠባበቅ እየተባለ በወያኔ መሪዎችና ካድሬዎች መመሪያ የሚሰጠው? በአዲስ አበባና በአገሪቱ ትላልቅ ከተሞች የተገነቡት የወያኔና የተላላኪዎቹ ሕንጻዎች ሁሉም ነባሩን ሰላማዊ የኅብረተሰብ ክፍል ከአባቱ፣ አያቱና ቅደመ-አያቱ ባድማ ላይ በማፈናቀልና በማባረር መሆናቸው በሚገባ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሦስት ግዜ በልቶ ወደ ሚያድርበት ዘመን ሳይሆን እየወሰዱን ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዕለት ዕለት ጥሪት አልባና ለዕለት ጉርስ እጅ እያጠረውና ነጋ ጠባ በግድያና በእስራት እየተዋከበ ከመሆኑ ባሻገር ራሱ ገበሬው እንኳ የመሬቱ ባለበት ባለመሆኑ የኑሮ ዋስትና የለውም --- በአገሩ ላይ ወደ ተራ ስደተኛነት ተለውጧል:: በእርሻ ላይ ተሰማራ የሚባለውም በዓመት ጠብቆ የሚያመርታት ምርት ወዲያው በወያኔ ካድሬዎች ለማዳበሪያ እዳ ክፍያ ተብላ ከአውድማው ላይ ተነጥቃ ትሄዳለች!! ይህን ጭካኔ የተሞላበትንና የማንነትን ጉዳይ አደጋ ላይ የጠለ የወያኔና የተላላኪዎቹ አስተዳደርን የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማኅበራት ም/ቤት በአውስትራሊያ እጅግ በጣም በጽኑ ያወግዘዋል፤ በአስቸኳይ እንዲቆምም ጥሪ ከማቅረብ ባሻገር ሁሉም ሕዝባችን (በውስጥም ይሁን በውጭ ያለው) ጥቃት እየተፈጸመበት ባለው የጎንደርና የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆነው ሕብዛችንና በተለያዩ ቦታዎች በተናጠል ጥቃት እየተካሄዳባቸው ካሉት ወገኖቻችን ጎን አብሮ በአጋርነት እንዲቆም ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!! ኢማማምአ 

No comments:

Post a Comment