Monday, July 25, 2016

በኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉትን ሶማሊያዊያን ዜጎች ግድያን አሜሶን በአፋጣኝ እንዲያጣራ ተጠየቀ


ባለፈው ሳምንት በቤይ ግዛት ውስጥ በኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉትን 14 ንጹሃን ያልታጠቁ ሶማሊያዊያን ግድያ ኢፍሃዊ ነው ሲሉ ታዋቂው የአገሪቱ የሕግ ምሁር ዳሂር አሚን ጄሰው ድርጊቱን አወገዙ። ሰላማዊ ዜጎችን በግፍ የገደሉ በሕግ ሊጠየቁ ይገባልም ሲሉ ከሸበሌ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በአጽኖት ገልፀዋል።
በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ስር ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወሰዱት ኢሰብዓዊ የጅምላ ግድያ ሰለባ የሆኑ ቁርዓን በመማር ላይ የነበሩ ሰላማዊ ዜጎች ግድያ በሶማሊያ የፓርላማ አባላት ዘንድ ጭምር ከፍተኛ ድንጋጤና መረበሽን ፈጥርዋል።
ከባይደዋ 37 ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኘው ዋርዲሌ መንደር አቅራቢያ የጅምላ ጭፍጭፋን አሚሶም አፋጣኝ የሆነ ምርመራ እንዲያደርግም የፓርላማ አባሉ ጥሪ አቅርበዋል። ዳሂር አሚን ጄሰው አክለውም ”የሰላም አስከባሪ ጦሩም ሆነ የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ከአልሸባብ ጋር በሚያደርጉት ውጊያ ላይ ለሰላማዊ የአገርቱ ዜጎች ሕይወት ከለላ በመስጠት ጥንቃቄ ሊወስዱ ይገባልም” ብለዋል የሕግ ባለሙያው። የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስቴርን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ከግድያው በኋላ ስፍራውን መጎብኘታቸውን ሸበሌ የዜና አውታር አክሎ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment