Friday, July 29, 2016

አጋጣሚውን መጠቀም ብልህነትና ማስተዋል ነው።



አሁን የደረስንበት ሰዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ያለውን እውነተኛ ስሜት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ከጫፍ ጫፍ በሚባል መልኩ እየተቀጣጠለ ይገኛል በውስጥም በውጭም
ይህንን እንቅስቃሴ ለድል ለማብቃት ትግሉን የጋራ ማድረግና በጥበብ መምራት ግድ ይላል።
ከአፋኞቻችን ውልደት ጀምሮ በብሔር በክልል በፖለቲካዊ ቡድን እየተቧድንን በሰላማዊ መንገድም ሆነ በአመጽ በተናጠልና ህዝቡን ባላማከለበት መንገድ ስናካሂደው ቆይተናል ውጤቱ ግን ዋናዎቻችንን መገበርና የአፋኙን ሥርዓት እድሜ ማራዘም ንው
"የብዙ ኪሎ ሜትር ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀመራል"ጉዞውን ለማስካት ደግሞ የጉዞ አቅጣጫውን መያዝ ግድ ይላል።
ነፃነታችንን ለማስመለስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በአስቸኳይ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ምሁራንን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን የሚዲያ ሰዎችን በህብረተሰቡ ተደማጭ የሆኑ ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ ቡድን ተመስርቶ ትግሉ ሊመራ ግድ ይላል መከፋፈል ይቁም
የአብዛኛው የትግል እንንቅስቃሴ ነፃነታችንን ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቻችንን ማስከበርና ተከባብረን በሰላም የምንኖርባት ሉዓላዊነቷ የተከበሀገር እንድትኖረን ነውና 
የአባቶቻችንን ክብር እንዉረስ ተዋርደናልና ክብራችንን እናስመልስ ሀገር እያለን ባይተዋር ሆነናልና እንተባበር
ይህንን ከጫፍ ጫፍ ያለ ህዝባዊ እንቢተኝነት ተባብረንና ተከባብረን እንምራው ልዩነቶች ካሉ ከድል በኋላ በሰለጠነ አግባብ በጠረንጴዛ ዙሪያ ተወያይተን እንፍታ
እርስ በእርስ ተጋጭተን ሀገራችንን አደጋ ላይ እንዳንጥል በማስተዋል እንራመድ።
ከአዲስ አበባ ወጣቶች የተላከ መልእክት

No comments:

Post a Comment