Wednesday, July 20, 2016

አፈትልኮ የወጣ መረጃ



ህሊና ጀለ ሙረን
ወያኔ እንደሚታወቀዉ ዛሬ ለእረፍት የተበተነዉን የአሻንጉሊት ስብስብ ፓርላማ ለአንዳች አስቸኩዋይ ጉዳይ ጠርተዋል::
ለምን ጠሩ? ለሚለዉ መልሱ የተገኘ ይመስላል:: ህወአታዊዉ ኢህአዴግ በመላዋ ኢትዮጵያ ከጫፍ እስከጫፍ በተቃዉሞ እየታመሰና በህወአታዊዉ ቡድን ላይ እየደረሰ ያለዉ ኪሳራ ይሄ ነዉ የሚባል ቀላል ደረጃ ላይ አይደለም:: ይህ ህዝባዊ አመፅም ከህወአታዊዉ ኢህአዴግ አልፎ ሀያላኑን አገራትንም እያስባባ ያለ ኩነት ነዉ:: በኦሮሚያና በደቡብ ያለዉ ተቃዉሞ ወያኔ ሲፈራዉ ወደቆየዉ ወደአማራ ተዛምቶ ትግሉም መልኩን በመቀየር ህወአታዊዉን ቡድን እጅግ ባልታሰበ መልኩ ማርበድበዱና ይህ በጦር መሳሪያና በተደራጄ ሀይል የሚታገዘዉ የአማራዉ አመፅ መላዉ አማራ ላይ ‪#‎ማዳመኑ‬ ለወያኔ የሞት ቲኬት የቆረጠና ለኢህአዴግ ህልዉናም ጊዜ ያልገዛ ሆኖ ተገኝቷል:: በተጨማሪም ህወአት ብአዴንን እንደወትሮዉ ማሴደንገጥ የማትችልበት ደረጃ ላይ መድረሷና ብአዴን ማቅማማቱ የህወአት ‪#‎ያላለቁ‬ መደባዊና በዘር ላይ የተመሰረተ የቤት ስራወች አደጋ ላይ መጣሉ ህወአታዊያን የመጨረሻ እድላቸዉን ለመሞከርና የበሰበሰ ዝናብ በአይፈራም ብሂል ጉዳዩን ከአግ7 እና በኤርትራ ላይ በመቆለል በፓርላማዉ የተወሰነ በማስመሰል ህወአታዊ'ንጅ አገራዊ ያልሆኑ እቅዶችን ማሳወጅ አልመዋል::
1. ጦርነት አተራማሽ የተባለችዉ ኤርትራና አግ7 ላይ ማሳወጅ
2. በየክልሉ የሚገኙ የልዩ ሀይሎችና ፖሊስ ተጠሪነታቸዉ ለጠ/ሚ.ሩ እንዲሆኑና እንዲፐወዙ ማድረግ
3. የትኛዉም የአገሪቱ ክፍል ላይ የሚገኘዉ ህዝባዊ አመፆች ላይ የክልል መንግስት ሳያገባዉ በቀጥታ በፌደራል መንግስት እንዲዳኝ ማድረግ
4. የማንነት ጥያቄን የማያስተናግድ አዋጅ ማወጅ
5. ማንኛዉም ከመንግስት አካል እጅ ዉጭ የሚገኝን የጦር መሳሪያ ለማስዉረድ ማወጅ

No comments:

Post a Comment