Tuesday, July 26, 2016

‎የጎንደር_ስብሰባ_አማራነት‬ የደመቀበት ነበር።


ጎንደር ላይ በነዋሪውና በብአዴን ሹማምንቶች የተካሄደው ስብሰባ ተፅዕኖው ቀላል አይደለም።እኛ ህግና ስርዓትን የምናውቅ በኢቢሲ፣ ፋና፣ በኮሙኒኬሽን እንደሰደባችሁን "ሽፍቶች፣ ፍርፋሪ ለቃሚ፣ሽብርተኛ"....አይደለንም።ጥያቄያችን ግልፅ ነው። የማንነት እና የድንበር እንጅ እናንተ እንደምትሉት የመልካም አስተዳደር አይደለም።"ወዳሃክር" እንጀራም እየበላን በሰላም እየኖርን ነው።ድንበራችን ተከዜ ማንነታችን አማራ ነን ኮሜቴዎቻችን በአስቸኳይ ፍቱ ..የሚል የአማራነት መንፈስ በአደባባይ ተንፀባርቋል።
ከመድረክ (ከሰብሳቢዎች) በአሁኑ ስብሰባ በጎ ነገር መጠበቅ ወይም ግልፅ አቋም ይንፀባረቃል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። እዚያ መደረክ የተገኙት ህዝቡን ለማረጋጋትና ስሜቱን ለማወቅ አዳማጭ ለመምሰል ነው።በዚህ የተነሳም ስለ እርከን ስራ፣ስለ ህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር ሲያወሩ ተሰብሳቢው ያስቆማቸው ነበር።
በረከት የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ጎንደር ህዝብ አንድ ነው የምትል መልዕክት አዘል ንግግር ሳያስበው ይሁን አምኖበት እንደተናገረ ከተሳታፊዎች ሰምቻለው። በጥቅሉ ስብሰባው ተፅዕኖ ፈጣሪ እንደነበር መገንዘብ ይቻላል። (የረጅም ጊዜን ውጤት የሚያስብ ካለ)
የብናልፍ የዋዠቀ አቋም አሁንም አልጠራም።ተጨባጭ እና ወደ ህዝብ ጆሮ የሚገባ ንግግር ባያደርግም "የህግ የበላይነት፣መልካም አስተዳደር" ምናምን የሚሉ ሀሳቦችን ማንሳቱ የወልቃይት አማራ ማንነትን ጥያቄ እንዳልተቀበለውና የኮሚቴዎችን አፈና ደጋፊ ሊሆን እንደሚችል አመላከች ነው።

ገዱ ገና ሲጀምር "የመጣነው የእናንተን ጥያቄ ልንሰማ ነው" ነበር ያለው።
ለጥያቄዎቻቸው ግን አጥጋቢ ወይም በቂ መልስ አለመስጠታቸው እንዳለ ሆኖ አቅጣጫ ለማስቀየር ዳር ዳር ሲሉ እንደነበር ተሳትልፊዎች ተናግረዋል።

ከጎንደሩ ስብሰባ ቀደም ብሎ ባህር ዳር ላይ ብአዴን ቢሮ በአቶ ገዱ የሚመራ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር።
Ayalew Menber

No comments:

Post a Comment