Wednesday, July 20, 2016

ጥርስ ኣልባው ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ቢለቅ ለሕወሓት ትልቅ ኪሳራ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል ::

ጥርስ ኣልባው ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ቢለቅ ለሕወሓት ትልቅ ኪሳራ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል ::

ለወልቃይት የማታለያና የጊዜ መግዣ እንዲሆን ጊዜያዊ የራስ ገዝ ኣስተዳደር ሊሰጥ ይችላል::
Minilik Salsawi - mereja.com - ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ኣስጥ እየዋዥቀች ነው። በሃይለማርያም ደሳለኝና በደህንነት ቢሮው ሃላፊ እንዲሁም በሕወሓት ጄኔራሎች መካከል ኣለመግባባት የተከሰተ መሆኑ እየተነገረ ሲሆን ሕወሓት ሃይለማርያም ኣርፎ እንዲቀመጥ ኣስጠንቅቃዋለች፥ ወታደራዊ እና የደሕንነት ሪፖርት የፈለገው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የሕወሓት ባለስልጣናትን መልስ ተከትሎ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጥርስ ኣልባነቱ ቢጮሕም የሚሰማው ኣላገኘም።በስልጣን የመቆየት ፍላጎት እንዳሌለው የሚያስነግረው ሃይለማርያም በነዱት የሚሄድ በግ መሆኑን ሕወሓቶች ራሳቸው መስክረውበታል።ፓርላማው ኣስቸኳይ የተጠራው ግድያን እና መንግስታዊ ሽብርተኝነትን በኣለማቀፍ ደረጃ ሕጋዊ ለማሰኘት ነው።በሃገር ውስጥና በውጪው ኣገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተል እና ለለውጥ በሕዝቡ እየተደረገ የሚገኘውን ንቅናቄ እንዲያግዝ ሕዝቡ እየተናገረ ይገኛል።

በማስፈራሪያ የታጀበው የሳሞራ የኑስ መልስ ቁጣን የቀላቀለ እንደነበር
ምንጮቹ ይናገራሉ፥ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ቢለቅ ለሕወሓት ትልቅ ኪሳራ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፥ፓርላማው ኣስቸኳይ ስብሰባ የተጠራ ሲሆን በምን ጉዳይ ላይ ይወያያል የሚለው ኣጀንዳ እስካሁን ይፋ ኣልሆነም።ሕወሓት የኣማራውን ሕዝብ ንቅናቄ ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤና ውጥረት ውስጥ የገባ ሲሆን በብአዴን ላይ ያለው ተስፋ እየወረደ ስለሆነ ኣስጊ የሚባሉ ባለስልጣናትን ያስወግዳል የሚል ኣስተያየት እየተሰጠ ይገኛል፥ለወልቃይት የጊዜ መግዣ እንዲሆን ጊዜያዊ የራስ ገዝ ኣስተዳደር ሊሰጥ ይችላል የሚሉም ኣልጠፉም።የሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ በግድያ በማሰር ዜጎችን ኣሸባሪ ብሎ በመፈረጅ እና ሕዝብን በመናቅ ላይ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ በክፋት አና በተንኮል የተሞላ እኩይ ተግባሩናን ጸረ ሕዝብነቱን ቀጥሎ ይገኛል።በሃገር ውስጥና በውጪው ኣገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተል እና ለለውጥ በሕዝቡ እየተደረገ የሚገኘውን ንቅናቄ እንዲያግዝ ሕዝቡ እየተናገረ ይገኛል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment