Thursday, July 21, 2016

በጎንደር የተጀመረው አመጽ የአማራው ሕዝብ የሕልውና ትግል ነው !

ከሐይለገብርኤል አያሌው (የቀድሞው የመዐሕድ አመራር አባል)
ባለፉት 25 አምታት የአማራው ሕዝብ ላይ በትግሬ ወያኔዎች የተፈጸመበት ግፍና መከራ ፤ በአይነት ፤ በመጠንና በይዘት ተሰፍሮና ተነግሮ የማያልቅ ነው። አማራው ኢትዮጵያዊነቱን ማተቡ አድርጎ በመኖሩ ፤ በዘር ማንነቱ ላይ የተከፈተበትን የማያባራ ጦርነት ለመመከት በማንነቱ ዙሪያ ተደራጅቶ ከመታገል ይልቅ ፤ የዘር ፖለቲካ ሃገር ያፈርሳል በሚል ሰፊ አተያይ ፥ ካራ ስለው ጉድጓድ ምሰው ደሙን ሲጠጡና ስጋውን ሲበሉት  የቆዩትን ሕገ አራዊት  የትግሬ ነጻ አውጪ ወንበዴዎችን ከፍ ሲል በንቀት ፤ ዝቅ ሲል በአላዋቂነትና በችጋራምነት እየታዘበ በጊዜ ሂደት ሲጠግቡ ይሰክናሉ በሚል ክፉኛ ተዘናግቶ በመቆየቱ ራሱንና ሃገሩን መከላከል በማይችልበት ደርጃ ተበታትኖ የተናጥል ጥቃቱን ሲያስተናግድ ቆይቷል።
The question of Welkait is the question of all Amhara people.
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ገና ከመነሻው ርዕዮታዊና ፖለቲካዊ የመታገያ አላማ አድርጎ የተነሳው የአማራውን ዘር የማዳከምና ብሎም ለማጥፋት  እንደሆነ የሰነድና የድርጊት ተግባሩ ምስክር ነው። ይህን  የተረዱ ጥቂት የአማራ ብሄር ተወላጆች የሕወሃትን  ፋሽስታዊ ጸረ ሕዝብና ጸረ ሃገር አላማ በሰላማዊ መንገድ ለማስወገድ በአማራነት ተደራጅተው ለመታገል ሞክረዋል። የብሄሩን  ተወላጅ ለማንቀሳቀስ ሰፊ ጥረት ቢያደርጉም አማራው  በኢትዮያዊነቱ ፍጹም የሚኮራ በመሆኑ ለጎሳ ፖለቲካው እንቅስቃሴ ጀርባውን በመስጠቱ አአስፈላጊውን የመደራጀት ተግባር ችላ ብሎ በመቆየቱ ለዚህ ዛሬ ለደረሰብት አስከፊ ሁኔታ ተጋፍጦ ይገኛል።
የአማራው ሕዝብ ቤቱ ያፈራውን ስንቅ ቋጥሮ ፤ ያለውን ጋሻና ጦር ሽክፎ ፤ ዳገት ቁልቁለቱን ወጥቶና ወርዶ እናት ሃገሩን አሰከብሮ የመኖር ታላቅ ታሪክ ባለቤትና ጀግና ሕዝብ ነው።   ለዘመናት ጠላቶቹ ሲደግሱለት የኖሩት የጥፋት እቅድ በትግሬ ወያኔዎች በኩል በሚያውቅውና በለመደውና በተደጋጋሚ
ሞክረው በከሸፈባቸው የቀጥታ ጦርነት ይልቅ ፤በተዘዋዋሪ ባለመደውና በማያውቅው አዘናጊና ነጣጥሎ የመምታት ታክቲክ በተራዘመ  የተቀነባበረ መንገድ ፤ የዘር  ማምከን ፤የዘር ማጽዳትና  ፤ ብሎም  የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ሲካሄድበ ቆይቷል። ይህ ሁሉ በዘር ማንነቱ ምክንያት በሃገር  ውስጥ የሚካሄድበትን በደል የአንባገነን ገዥዎች  የጭቆና አገዛዝ አድርጎት ቆይቷል።   በዲሞክራሲያዊና የሰላማዊ ትግል አግባብ ለውጥ በማምጣት ችግሩ ይፈታል በሚል በሕብረብሄራዊ መንገድ ተደራጅቶ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ አታካችና ብዙ መስዋዕትነት የጠየቀ ትግል ሲያደርግ ቆይቷል።
የትግሬ ወያኔዎች መረን የለቀቅ ስግብግብነትና ድንቁርና የወለድው የግፍ አገዛዝ ከግዜ ወደ ግዜ ከመቀንስ ይልቅ  እየባሰ ሄዷል ። የአማራውን ሕዝብ ሆደ ስፊነት በፍርሃት ሂሳብ በመመንዘር ሃብትና ንብረቱን የዘረፉት አንሶ በተፈጥሮ ያገኘውን  አማራዊ ማንነቱን በሃይል ቀመትው የነሱ ለማደረግ ከፍ ያለ ግፍ በወልቃይት አማሮች ላይ በተለይ ሲፈጽሙ  ቆይተዋል ። ይህ ጀግናና ኩሩ ኢትዮጵያዊ የአማራ ሕዝብ የትግሬ ወያኔዎች የፈጸሙበትን የግፍ   ድርጊት በሕግና በስርዕት ለመፍታት በሰለጠነ መንገድ ተወካዮቹን መርጦ ሲያካሂድ የነበርው መራራ የፍትህ ፍለጋ ሂደት  ያለእንዳች ፋይዳ ከአንዱ ወደሌላው ሲገላበጥ ቆይቷል።
ፍትህም ፤ ዳኛም ፤ ፈራጅም ፤ ከሳሽም  የሆነው የትግሬ ወያኔዎች ድርጅት ፤ በሕግ ስም ያላገጠባቸው አንሶ በሃይል ተጠቅሞ የጉዳዪን አንቀሳቃሾች አፍ ሊያዘጋ ተንቀሳሰ ። የትግራዩን የገዳይና የአፈና ቡድን ልኮ እንደለመደውም ብልታቸውን እየቀጠቀጠና ጥፍራችውን እየነቀለ የበቀል ዛሩን ሊወጣባአቸው በጎንደር ከተማ የሚገኙትን የኮሚቴው ተወካዮች ላይ ያደረገው የአፈና እንቅስቃሴ በጀግናው የአማራ ልጆች ከፍ ያለ የአርበኝነት ንቅናቄ ፤ የሚያስደምም የመከላክል እርምጃ መወሰዱን ተከታትለናል። በዚም ሕዝባዊ ንቅናቄ የተወሰኑትን ከአፈና ማተረፍ የተቻለና ፤ የዘረኛ ወያኔ ወታደሮችን  በማስገደድና በማስድንገጥ የአማራ ገበሬና ወጣቶች የፈጸሙት አኩሪ ተግባር ፍትህ ናፋቂውን ሁሉ ያኮራና  ስሜቱ በከፍተኛ ሁኔታ አነቃቅቷል።
ከዚህስ ወዴት የሚለው ፤ የሁሉም ሃገር ወዳድ ዜጋን ጥያቄ  አጭሯል ። ካለፉት ረጅም ዓመታት ተሞክሮዐችን በግልጽ አንደምንረዳው የትግሬ ወያኔዎች ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባና መውጫ ቀዳዳ ሲጨንቀው ከጸሃይ በታች ባሉ ነገሮች ለመወያየት ፈቃደኝነቱን ሲያሳይ ቀጣፊ ሽማግሌዎቹንና አድርባይ ካህናቱን አሰልፎ በተማጽኖ ሂዲቱን የማረገብ ታክቲክ ሲጠቀም ቆይቷል ። የተቃውሞ መዐበሉ ጸጥ ሲል ፤ ለትግል የተነሳው ሃይል ስሜት ቀዘቅዞ መበታተን ሲጀምር ፤ ያኔ አዘናግቶ ፤ የትግሉን መሪዎችንና  መላው ሕብረተሰብ ላይ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ለመተንበይ ነብይ መሆን እይጠይቅም። ከምርጫ 97 በሗላ በቅንጅት መሪዎችና በመረጣቸው ሕዝብ ላይ በተለይ በአዲስ አበባ የትግሬ ወያኔዎች የፈጸሙት ግዜ ይቅር የማይለው ሰቆቃ ፤  ዘረፋና ግድያ ፤ የብዙ ሚሊዮኖችን ሕይወት ያናጋ ለመሆኑ በህይወት ያለነው የምንመሰክረው ሃቅ ነው።
በዚህ ሰሞን በጎንደር በትጥቅ ታጅቦ የታየው ሕዝባዊ ቁጣ ፤ የትግሬ ወያኔዎችን ክፉኛ ያርበደበደ አገዛዙ ታጣቂ ሃይል ሲያይ እንዴት እንደሚርድ  የታየበት  እጋጣሚ ነበር።  ይህ ሁኔታ ለትግሬ ነጻ አውጪ ወንበዴ መሪዎች  በደምና በዘረፋ የተጨማለቀ ሕልውና ሊንድ የሚችል ሕዝባዊ መነሳሳት  ምን ያህል አገዛዙን በተከላካይነት እንዳቆመውና ፤ የሕዝቡም መታጠቅ ይከተል የነበረውን ፍጅት አንደገታው ለመታዘብ አስችሎናል። ይህ ሁኔታ አገዛዙንና ደጋፊዎቹን የበቀል ስሜት ውስጥ መክተቱን ከሚወጡት መገልጫዎችና በየማህብራዊ መድርኩ የሚታየው በቂ ምልክት የሚሰጥ  ነው። ከዚህም የተነሳ ሂደቱ ሲቀዘቅዝ መሪዎቹንና ህዝቡን ምናልባትም ከዚህ በፊት አገዛዙ ከፈጸማችው በደሎች በላይ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ የከፋ እርምጃ በአማራው ሕዝብ ላይ የመፈጸም እቅድ እንደሚተግብር መረዳት የማይችል የዋሕ ይኖራል ብዬ አልገምትም።
በጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች የታዩት ሕዝባዊ ቁጣዎች የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ ላለመሆኑ ማንም ሊገነዘበው ይገባል። ይህ ህዝብ እንኳን እንደ ወያኔ ያለ ተንበርካኪና የውጭ ሃይሎች ተላላኪ የሆነ ገለባ ቡድን ይቅርና እንቢ ብሎ ከተነሳ ለማንም ለምንም የማይመለስ ጠመንጃ ጌጡ ጦርነት ባህሉ ያደረገ የጀግኖች ጀግና በመሆኑ ባንዳና የባንዳነት ታሪክ ወራሽ የፋሽስት መቃብር ላይ የበቀሉ እንክርዳዶችን ልክ የማስገባት አቅም እንዳለው ወደፊት የምናየው ይሆናል።
የአማራው ሕዝብ ይህን ትግል የሚያደርገው ወያኔውና ዘረኝነት ሕሊናችውን የጋረደቸው ደጋፊዎቹ እንደሚያራግቡት ፤ የጸረ ትግራዊነት ትግል ሳይሆን ሳይወድ በግድ ሕልውናውን ለመከላክል የሚገባበት የሞት ሽረት ትግል ነው። ትግሉ ሕውሃት ከሚባለው በትግራይ ሕዝብ ስም ከሚነግደው ሰው በላ የሌባና የቀማኛ ቡድን ጋር መሆኑን መላው የትግራይ ተወላጅ ሊገነዘብው ይገባል።  የትግራይ ሕዝብ ማንም ሊፍቀው የማይችለው  በደምና አጥንት የተሳሰር የአማራው ሕዝብ ወገን ነው። ፋሽስቶችና የባንዳ ልጆች ቀን ወጥቶላቸው ስመጥሩና ገናና የነበረውን ትግሬነት ጥላሸት እየቀቡት ነው።  ለሺህ ዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ ሊጨራረስ ወደሚያስችል የታሪክ ምዕራፍ እያሸጋገሩት ነው።
ቢቻል የወደፊት የሕዝቡን ወንድማማችነት ለማስቀጠል ፤ የትግራይንም ሕዝብ የወንጀለኞች መሸሸጊያ ሆኖ እንዳይጎዳና ከወገኑም እንዳይለያይ ሃላፊንት ያለባችው ምሁራንና በነጻው አለም ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ፤ በስማችው የሚፈጸምው የግፍ ተግባር ሊታገሉት ይገባል ። መነገጃም ከመሆንና ከታሪክ ከፍርድ ለማምለጥ ግዜው ያልመሸ በመሆኑ ከአጉል ትብዒት የራቀ ተግባር ይጠበቅባቸዋል።
የትግራይ ልሂቃንና ተወላጆቹ ፤የሕወሃትን አገር አውዳሚና ከፋፋይ አካሄድ በመገሰጽና በመቃወም ለትግራይ ሕብረተሰብ ዘላቂ ጥቅምና ሕልውና እንዲጠበቅ በግልጽ ወጥተው ሊታዩ ይገባል ። ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ያለው አብሮነት በስላምና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ፤ ህግን ፤ ታሪክንና ፤ ሃቅን የተመረኮዘ የሃብት ክፍፍልና  የወሰን  ክልል ላይ መስማማት እንዲፈጠር ጥረት ሊያደርጉ ይገባ ነበር። ራሱን በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማህበር ሲል የሚጠራው ተቋም ፤ ባለፈው ሰሞን ያስተላለፈው መግለጫና ውንጀላ ፤ አንድ በሰለጠነ ዓለም ውስጥ ከሚኖር ተቋም የማይጠበቅ ነው። ይህ የጨለምተኛ ዘረኞች  ስብስብ ዛሬም ከተቸነከረበት የትብዒት ቅርቃር ያልተላቀቀ  መሆኑ ሳያንስ ፤ በጎንደር የተቀጣጠለው አመጽ ባለቤቱ የእማራው ሕዝብ መሆኑ ቀርቶ ጉዳዩን ከኤርትራ መንግስት ጋር በማያያዝ የቀረበው  ውግዘት ከማሳዝን እልፎ የሚያሳፍር  ነው።
የወልቃይት ጥያቄ የአማራው ሕዝብ የማንነትና የህልውና ጉዳይ ነው ። ይህንን የራሱን የመብትና የነጻነት  ችግር ለመፍታት  ከተባበር ሙሉ አቅምና ጉለብት አንሶት አጋዥ የሚጠይቅበት ሁኔታ አይኖርም። የሕወሓት ደጋፊ የትግራይ ተወላጆች ሆይ የዘነጋችሁት የምትመጻደቁበት ድርጅታችሁ ; ህወሃት ያለ ሻዓብያ ሞግዚትነት ከቶም በግሩ መራመድ የማይችል ድኩማን እንደነበር ከረሳችሁ ልናስታውሳችሁ እንገደዳለን። ሻዓብያ ሕወሓትን ሱሪ አስታጥቆ ንፍሮ እያስቀቀለ የሃሳብና የመሳሪያ ትጥቅ ሰጥቶ እኮ ነው ያሳደገው ።  የሕወሃት መሪዎች  ለሻብያ ጣዖት ቀርጸው ከማምለክ  በቀር ምን ያልሆኑት ፤ ምን ያልሰጡት ነገር አለ።  የሃገሩን ብሄራዊ ጥቅም እጅ መንሻ አድርጎ ያቀረበ ፤ የሃገሪቱን ወሳኝ የባሕር በር  እንደ ገና ስጦታ ያስረከበ ተንበርካኪና ሃገር ሻጭ ቡድን እንደ ሕወሃት ያለ በዓልም ታሪክ አለተመዘገበም። ይህን የመሰለ አሳፋሪ ቡድን ደጋፊ ሆናችሁ ሌላውን በምንም መልኩ የመቃወም  የሞራል መሰረት የላችሁም ።
የአማራው ሕዝብ የጀመረው ትግል ለማስቀጠል በአሁኑ ወቅት ለሚያድርገው ትግል   ከኤርትራ መንግስት ያገኘውም ሆነ የጠየቀው ድጋፍ የለም። ገበሬው በሬውን ከተሜው ንብረቱ ሸጦና ለውጦ   ራሱን ማስታጠቁን ከወያኔዎች በላይ የሚያውቅ ባይኖርም ፤አበው << ጃንደርባ ሎሌ በጌታው ብልት  ይፎክራል» እንዲሉ በሱማሌ ይሁን በኦሮምያ በጋንቤላ ይሁን በአማራ የሚነሳውን ተቃውሞ የሕዝቡን ጥያቄ ከማዳመጥ ይልቅ ፤ ለሁሉም ጉዳይ ሻብያን ማንሳት የልማድና  የፍራቻ ይመስላል።  ይህ ሲባል ግን በቀጣይ እኛ ኢትዮያውያን   ከኤርትራ  ሕዝብና መንግስት ጋር  የሚኖረን ግንኙነት  ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ እንደሚቀጥል እሙን ነው ። ይህ ግንኙነት   ስትራቴጅካዊና ታክቲካዊ አጋርነንትን ማዕከል ያደረገ ብቻ ሳይሆን ከታሪክ ሂደት በዕጅጉ የተማርን ወንድማማቾች በመሆናችን ድጋፍ የመስጠትና የመቀበል መተጋገዝ ለመገንባት የማንም ምክርም ሆነ ተቃውሞ የሚያስቀረው እይሆንም ።
ከዚህስ በሗላ?
መላው የአማራ ተወላጅ የሆነው በውጭ ሃገርም ይሁን በውስጥ ያለው ፤ የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ፤ 25 አመታት የጥላቻ ፤ የግድያ ፤ የዘረፋ ወንጀል አንሶት የአማራነት ምሶሶ የሆነውን የወልቃይት አማራ ማንነትን የማጥፋት ግፍ ሲፈጽም ቆይቷል። ይህ ጥጋበኛ የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ራሱ ላወጣው ሕግ የማይገዛ ፤ የፍትህን ክብር ያቃለለ ፤ በሰላምና በሰለጠነ መንገድ ችግሮችን ለመፍታት ፈቃደኝነት የሌለው መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቶናል ። ሕወሃት የአማራን ሕዝብ ጨርሶ የማጥፋት ፤የጥላቻ አጀንዳ ይዞ የሚንቀሳቀስ በታሪክ የአማራው ሕዝብ ከገጠሙት ጠላቶቹ ሁሉ የከፋ የህልውና ጠላቱ መሆኑ ላይ  በመርህ ደረጃ የጋራ ግንዛቤና የተወላጁ ማህብራዊ ንቃት ጥልቀት በማስያዝ እይቀሬውን መራራ ትግል ለመጋፈጥ መደራጀትና መዘጋጀት ይኖርብናል።
አበው  «ሊገል የመጣን ጠላት ወዳጄ ቢሉት እይትውም እንዲሉ » ሕወሓትና የዘረፋ ግብራበሮቹ እንኳን ታጥቆ የተገዳደርውን፤ አይነኬ የሆኑትን ተቋማቱንና ንብረቱን ያወደመውን ሕዝብ ይቅርና በስላማዊና ሕጋዊ መንገድ የታገሉትን ታመው እንኳ ተገቢውን ሕክምና እንዳያገኙ እንዴት እንደሚበቀል በሞትና በህይውት መካከል እንኳ ሆኖ   በፍትሕ ስም ሐብታሙ አያሌውን እንደሚበቀሉት እያየን ነው። በመሆኑም ሕግና ፍትህ ሞተው እንደተቀበሩ ቆጥሮ ማንኛውም የአማራ ተወላጅ ከትግሬ ወያኔዎች እጅ ወድቆ የከፋ ምድራዊ ስቃይ ከመቀበል ይልቅ ሕልውናውን ለማሰንብት ይሁን የክብር ሞት ለመሞት ያለው ብቸኛ አማራጭ የተጀመረውን ሕዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮና ራሱን በጎበዝ አለቃ እያደራጀ ከወራሪው  የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ጋር ለመፋለም መዘጋጀት  ይኖርበታል።
ይህ ሁኔታ ሃገር የሚያፈርስ ሕዝብ የሚያጫርስ ነው የሚል ስጋት ከተለያዩ ቦታዎች  ይደመጣሉ ። እርግጥ ነው ለሃገር አንደነትና ለዘላቂ የሕዝቦች አብሮነትን የሚበክል ለማንም ለምንም የማይጠቅም አደገኛ ነው። ጥቂቶች በዘር ተደራጅተው የፖለቲካ ምህዳሩን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረው በዘረኝነት የተሞላ የአገዛዝ   መከራ ባጸኑበት ፤ በነጻ የመዳኘት እድል በጠፋበት ፤ ከመብት ገፈፋ በላይ ማንነትን  በጉልበት ለመደፍጠጥ በሚሞከርበት ግዜ አማራጭ መፍትሄ በጨለመበት  ሁኔታ ውስጥ   የመኖርና ያለመኖር ሁኔታ የሚወሰነው ብሶት በወለደው የሃይል እንቅስቃሴ ብቻ ሲሆን ፤  የህዝብ ዘላቂ አብሮነትና ፤ የሃገር አንድነት ቅድሚያ አጀንዳ ሊሆን የሚችሉበት ሁኔታ ከቶም አይኖርም።
የአማራው ሕዝብ ዘረኛው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ከአጥፊ አካሄዱ  ተቆጥቦ የቀደመ የህዝቦችን አብሮነት በሚያስቀጥል መልኩ አገዛዙን እንዲያሻሻል ፤ በልሂቃኑም ፤ በሰባኪውም ፤ በወጣቱም ፤ በሴቱም ፤ በደጋፊውና በተቃዋሚው በተለያየ ግዜና ቦታ ያለመታከት ለመምከር ሞክሯል ። ለመሪዎቹም ተማጽኖ አቅርቧል። ይህ ሁሉ ግን ሰሚ ጆሮና  አሳቢ አይዕምሮ ከትግሬ ነጻ አውጭ መሪዎች ዘንድ አላገኘም ። በግፍ ላይ ግፍ በችግር ላይ ችግር ያለማቋረጥ ማንም  ለዘለቄታ ሊሸከመው የሚችለው ባለመሆኑ በመጨረሻ ባልሞት ባይ ተጋዳይነት ለሚወሰድ እርምጃ ተበዳዩ ሕዝብ  ተጠያቂነት የለበትም።
እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
አሜን!!!

No comments:

Post a Comment