እሄን ሁሉ የመከራ አገዛዝ ተሸክሞ የኖረው አማራ ሕዝብ ትዕግስቱ ተንጠፍጥፎ አልቋል ሲል፥ እነ በረከትን በስም ጠርቶ በመወረፍ "ዋ ንገሯቸው ይረፋ" የታሰሩትም ይለቀቁ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
===================================================
የዛሬው እና የሰሞኑ የጎንደር ስብሰባ ዝርዝር ሁኔታ እነሆ,,,,,
የጎንደር አማራ የብአዴን ሰዎችን ቁጭ አድርጎ ብሶቱን አንድም ሳያስቀር ነገሯቸዋል። ስብሰባው ላይ የተገኙ እናቶች ሳይቀሩ የህወሓትን ፀረ አማራነት አውግዘዋል።
እነ በረከትን "ዋ ንገሯቸው ይረፋ" ብለዋቸዋል፥ እነ ኮሎኔል ደመቀ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ህዝቡ በአፅንኦት ተናግሯል። ህዝቡ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ እራሱን ለመከላከል እንደተዘጋጀና ልበ ሙሉነቱን አሳይቷል።
አቶ በረከትን በስም ጠርተው… የጎንደር እንባ ይፋረድህ ፣ ጎንደር ላይ አንዲት ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ከፍታችሁ ልጆቻችን ሰካራም ስታደርጉ፣ ትግራይ ላይ ከ60 በላይ ፋብሪካ ከፍታችኋል።
አማራ ይሄን ሁሉ በሰፊ ትዕግሥቱ ችሎ ተቀምጧል።
አሁን ግን ትግስታችን ተንጠፍጥፎ አልቋል። እያሉ ምሬታቸውን በቀጥታ አቶ በረከት ላይ አስቀምጠዋል። አቶ በረከት ድምፁን አጥፍቶ አዳምጧል። መልስ ሲመልስም ተጠንቅቆ ፣ የህዝብ ወገንነቱን በሚያሳይ መልኩ ነበር።
በኢቲቪ ወያኔያዊ ዜናዎች እንደ ሚበሳጭ በግልፅ ተናግሯል። አቶ ገዱ ጭምተኛ ሆኖ ነው የዋለው። ሲናገርም በጥንቃቄ ህዝብን ላለማስከፋት እዬታገለ ነበር።
አቶ ብናልፍ አንዷለም ዛሬም የህወሓት ሎሌነቱን አስመስክሯል። " የፌድራል ፖሊስ ህጋዊ ነው…" የሚል ስብከት ሊያሰማ ሲፍጨረጨር እንደተለመደው በተሰብሳቢው ጩኸት ንግግሩ በተደጋጋሚ ተቋርጧል።ትናንትም ዛሬም ተሰብሳቢው አቶ ብናልፍን እንደ ምናምንቴ ሲቆጥረው ታይቷል።
የሰው ዘር አይመስልም ብለውታል።
በአጠቃላይ የብአዴን ባለስልጣናት እስኪበቃቸው የጎንደር አማራን ብሶት ተግተዋታል። ህወሓት አንዳች ርምጃ እወስዳለሁ ብትል የሚመጣው አፀፋ የከፋ እንደሆን የጎንደር አማራ መልክቱን በብአዴን በኩል ልኮላታል።
አማሮች ጎንደር ላይ ተሰውተው አማራነታቸውን ለማስከበር በሚገባ እንደተዘጋጁ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
ያው ብአዴን የተላከው ህዝቡን እንዲያበርድ መሆኑ ይታወቃል። ህዝቡ ግን ብሶቱ እንደ ማይበርድ አረጋግጦላቸዋል።
ኮሎኔል ደመቀን… ወደ አዲስ አበባ ለመውሰድ ውስጥ ለውስጥ እዬተሰራ እንደሆን ጭምጭምታ ተሰምቷል። በአቶ ብናልፍ አንዷለም አስተባባሪነት ይሄ ነገር ሊሰራ እንደታሰበ የውስጥ አዋቂዎቻችን ገልፀዋል። የጎንደር እና የአካባቢዋ አማራ ነቅቶ እንዲጠብቅ እናሳስባለን።
የሰላማዊ ሰልፉ ነገር ሳይነሳ ስብሰባው ተበትኗል። በእርግጥ ሰላማዊ ሰልፉ በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚካሄድ ህዝቡ ሰምቷል።
በመሃበራዊ ድህረ ገፆች እዬተሰራጩ ያሉ የቀናት መፋለሶችን ለማስተካከል ቤተ አማራ ከሰልፉ አዘጋጆች ትክክለኛ መረጃ እዬጠበቀች ነው። እንደደረሰን ለእናንተ እናሳውቃለን።
No comments:
Post a Comment