Sunday, July 17, 2016

የወልቃይትን ጥያቄ በተገቢው ሁኔታ ማወቅ ለሚፈልግ ፤የህዝቡን ስሜት ለመረዳት ይህን ቪድዮ ሊያይ የግድ ይገባል፡፡ በውኑ የወልቃይት ጥያቄ፤ ጥቂት አሸባሪወች የሽአብያ ተላላኪወች የሚያነሱት ጥያቄ ነው ብሎ ማጣጣል ይቻላል ወይ?! የሚከተለውን ቪድዮ ይመልከቱና የራስወትን ብይን ይስጡ፡፡ ማንም የማንነት ጥያቄ የሚያነሳ ህዝብ ፤ ጥያቄው መልስ ሊያገኝ ይገባል፡፡ አንድ ሰው ‹‹ኦሮሞ ነኝ›› ካለ ኦሮሞ ነው፡፡ የማንነት ጉዳይ የሚመለከተው ባለቤቱን ብቻ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የቅማንት ህዝብ ቅማንት ነኝ ካለ ፤ ቅማንት ነው፤ ማንም አይደለህም ሊል አይችልም፤ የራሱ ምርጫ ስለሆነ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያ ‹‹የማንነት ጥያቄ ተመልሷል›› ያሉት የተጣመመ አተያይ፣ ፍጹም ጸረ ዲሞክራሲያዊ እና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጭ መሆኑን በቀላሉ ከህዝቡ ምሬት ፣ ግፍ እና መከራ ማየት ወይም መረዳት ይቻላል፡፡ ይህን እያየ ዝም የሚል ስርዓት በውኑ ሁሉንም ህዝቦች በእኩል ዓይኑ ያያል ማለት ይቻላል ወይ?!

No comments:

Post a Comment