ህወሓት በአማራ ክልል መንግስት ከመናደዱ የተነሳ እሱ በሚቅጣጠረው ቴሌ አማካኝነት የቴሌቪዥን ጣቢያው ከናይል ሳት እንዲቋረጥ አድርጓል፡፡ እንደ አማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ገለፃ ከሆነ ምክኒያቱ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ነው፡-
የአማራ ቴሌቪዥን በናይል ሳት ሳተላይት ስርጭቱን ለተመልካቹ እንደሚያደርስ ይታወቃል፡፡ የሳተላይት ክፍያው ለመፈፀም ደግሞ የአማራ ብዙሃ መገናኛ ድርጅት ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በወቅቱ ይከፍላል፡፡ ኢብኮ ደግሞ ለኢትዮ ቴሌኮም ክፍያውን ያስገባል፡፡ በዚህ ሂደት ላለፉት 2 አመታት የተፈፀመውን ክፍያ ኢትዮ ቴሌኮም ለሳተላይት አከራዩ ድርጅት ባለመክፈሉ የአማራ ቴሌቪዥን ስርጭቱ ዛሬ ንጋት ጀምሮ ተቋርጧል፡፡ ይላል፡፡ ሆኖም አሁን ላይ መሆኑ የጎንደሩን ጉዳይ አሸባሪ ምናምን እያለ እንደ ህወሓት ባለማስጮሁ ተበሳጭተው እድርገውት ይሆናል፡፡ ህወሓት የአማራ ክልል መንግስትን ውስጡ ገብታ መፈረካከስ ቢያቅጣት ብቸኛውን የአማራ ቴቬ ዘጋችው!
የፌደራል መንግስቱን መጠቀሚያ በማድረግ አማራ ክልልን ማጥቃት ቀጥላለች፡፡ የሚገርመው ከመንግሥት ሚዲያዎች አማራ ቴቪ ነበር የምመለከተው፡፡ ለጊዜው ሌላ አማራጭ አያለሁ፡፡ ፈቅደው ከከፈቱላቸው ሃሃሃሃ ገና ብአዴንና ህወሓት ወደ ጦርነት ሳይገቡ አይቀርም በዚህ አያያዝ፡፡ ምክኒያቱም የህወሓት ጥጋብና ትዕቢት ወሰን አጥቷልና፡፡ ነገ ደግሞ ምን ሊዘጉ ይሆን?
No comments:
Post a Comment