- 25ኛ አመቱን በማክበር ላይ ያለው ኢህአዴግ ፣ ህዝቡን ለማወያየት በባህርዳር በጠራው ስብሰባ ላይ አባሎቹ “ ኢህአዴግ ለቀብራችን ደርሰህልናልና እና እናመሰግንሃለን” ሲሉ ተሳልቀውበታል።
አንድ አስተያየት ሰጪ “ይህ ህዝብ ያለቀና የሞተ ህዝብ ነው፤ አሁን ነው እንዴ የምትመጡት? ፣ ለህዝቡ ቀብር መጥታችሁዋል ጥሩ ነው ያሉ ሲሆን መንግስት በዲሞክራሲ ረገድ አገኘሁት በማለት ያቀረበውን የድል ዜና ውድቅ አድርገውታል። በየበረንዳው ወድቀው ያሉ፣ መጠጊያ የሌላቸው ከማህበራዊ ህይወትና ከኢኮኖሚ የተገለሉ አባላት አሉን ሲሉ አስተያየት ሰጪው በምሬት ተናግረዋል ።
ተናጋሪው የቤት ችግር በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርት ሲያጣጥሉም፣ “ ዋናው አውራ ጎዳና ላይ የተገነባው እኮ የካቢኔ ቤት ነው፣ የትኛውን የህብረተሰብ ክፍል አቅፎ ነው ተሰርቷል የምትሉት ግንባታ አሳፋሪ ነው ሲሉ አክለዋል። አስተያየት ሰጪው የ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ነገ መቃብር ውስጥ ገብተው ሙታኖችን እንደማይዘርፉ ዋስትና የለንም ሲሉ ያክላሉ ።