Thursday, May 12, 2016

በርካቶች‬ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት እጅግ ጣሩ። ጥረታቸው ግን እንደ ደካማነት ተቆጠረባቸው። በያዙት የጦር መሳርያ ብቻ የሚተማመኑ ጉልበተኞች ቀለዱባቸው። የህዝብን ድምጽ እየሰረቁ መቀመጣቸው ሳያንስ መራጩን ሕዝብ እያሳደዱ መበቀል ያዙ።


 ኢትዮጵያ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ማምጣት ምርጫ ለአምስተኛ ግዜ ተሞከረ። አምስቱም ተጭበረበረ። ከአሁን በኋላ በምርጫ ለውጥ እናመጣለን ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደሆነ የምርጫ 2007ቱ ትዕይንትን ብቻ ማጤኑ ይበቃል። በታሪክ 100% አሸነፍኩ ብሎ የተናገረ አንባገነን መንግስት በኛው ምድር ተፈጠረ። ይህ ሕዝብ ላይ ማፌዝ ነው። ትዕቢት፣ ድፍረት እና ንቀት የተሞላበት ፌዝ። “ምንም አታመጣም!” አይነት ንቀት!
በፖለቲካ አግባብ ጦርነት የዲፕሎማሲ ጣርያ፣ የሰላማዊ ትግል መጨረሻው አማራጭ ነው።
ታጋይ አርበኛ ፕሮፌሰር. ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር

No comments:

Post a Comment