በኢትዮጵያ የሚደረጉ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ባለው የጥቅም ቁርኝት እንዲያሸንፍ እየተደረገ ይሰጠዋል እየተባለ የሚከሰሰው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራሽክን ተጨማሪ ግድብ እንዲሰራ የ1.86 ቢሊዮን ፓውንድ ስምምነት ተፈራረመ::
አዲስ ሊሰራ በታሰበ የኮያሽ ሃይድሮ ግድብ ፕሮጀክትን እንዲያሸንፍ የተደረገው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ይህን ፕሮጀክት እንዲያሸንፍ በግልጽ የተደረገና ሌሎች ታዋቂ ኩባንያዎችን ያካተተ ጨረታ አለመካሄዱን የሚከሱት የውስጥ ምንጮች አሁንም ይህ ድርጅት እንዲያሸንፍ የተደረገው ከስርዓቱ ሰዎች ጋር ባለው የጥቅም ቁርኝት ነው ይላሉ::
ፕሮጀክቱ 6,000 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ማጠራቀሚያ ድምጽ መፍጠር 170m-ከፍተኛ ሮለር የተጠቀጠቀ ግድብ የሚያካትተው የኮይሽ ሃይድሮ ግድብ ወደ 6.460 GWh የኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጫል:: የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ከአዲሱ ሃይል ማመንጫ ወደ 2,200MW የኤሌክትሪክ ሃይል ለማከፋፈል ያግዘዋል ተብሏል::
ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት በርካታ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል በርካታ ችግሮችን እየፈጠረ ሲሆን ሃገሪቱ ግን የመብራት ሃይልን ልለኬንያ; ሱዳና ጅቡቲ እየሸጥኩ ነው እያለች ነው::
የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሳሊኒ) ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ እያካሄደ በነበረው የግድብ ግንባታ በኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ዙሪያ በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ የረሃብ አደጋ መፈጠሩን ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል የተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ማስታወቁና በስፍራው በመካሄድ ላይ የነበረው የግድብ ግንባታ የቱርካና ሃይቅ የውሃ መጠን እንዲቀንስ በማድረጉ በሺዎቹ የሚቆጠሩ የካሮ ጎሳ አባላት ለረሃብ መጋለጣቸውን ድርጅቱ ማሳሰቡ እንዲሁም በግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ምክንያት በአካባቢው እያደረሰ ነው ያለውን ጉዳት ለአለም አቀፍ የኢኮኖሚና የትብብር ድርጅት ያቀረበው ሰርቫይባል ኢንተርናሽናል በቱርካና ሃይቅ ላይ ህይወታቸው የተመሰረተ ከ100ሺ በላይ የማህበረሰቡ አባላት ለችግር መጋለጣቸውንም መዘገቡ አይዘነጋም::
No comments:
Post a Comment