በሐገሪቷ ላይ እንዳሻዉ ሲያስርና ሲያንገላታ ሕገ_ወጥ ኢፍትሐዊ የሆኑ የምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀም መብት ጠያቂ እና የፖለቲካ ልዩነት ያላቸዉን እንዲሁም በቂም በቀል ምክንያት መላዉ ኢትዮጵያዊያንን ያለከልካይ አሰቃይቶ እየገደለ የሚገኘዉ ጨካኙ ብሎም እራሱን እንደ የመረጃዎች ሁሉ አዉራ አድርጎ የሚመለክተዉ በጌታቸዉ አሰፋ የሚመራዉ የብሔራዊ መረጃ ከሐገሪቷ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን የመከላከያ ሚኒስተር ወታደራዊ ደህንነት መዋቅር ጋር ተጋጭቷል።
ከሐገር ደህነንት አንጻር በሚል ብሂል በስልጣን ተዋረድ ምክንያት ወታደራዊ መረጃ ሪፖሮች ባጠቃላይ ይወርድለት የነበረዉ ብሔራዊ መረጃ በመከላከያ ዉስጥ የሚገኘዉን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ጠቅልሎ በሰረዘ መልኩ መረጃ በማዉጣት የጠረጠራቸዉን የመከላከያ አባላት ከሕግ ዉጭ በራሱ አባላቶች እያደነ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤቶች እንዲቀርቡ እያደረገ ይገኛል።
የሐገሪቷ ደህንነት በእጁ የሆነዉ የመከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ሁኔታ እየከዳ እና መረጃ እየሰጠ እንዲሁም በአመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ባለበት ሁኔታ እና የወያኔዉ ቡድን በመፍረክረክ ላይ በሚገኝበት በዚህ የመጨረሻዉ የዉድቀት ወቅት ላይ የበኩሉን ጥረት ከማድረግ አንጻር የወያኔን ወታደራዊ ደህንነት ጭምር በጥቁር ነጥብ ዉስጥ የከተተዉ የህዉ የጌታቸዉ አሰፋ ክንፍ ከመካከለኛዉ እዝ 22ተኛ፣ 31ኛ እና ከተጨማሪ 3 ክ/ጦሮች።
ከሰሜን እዝ 11ኛ፣ 13ተኛ፣ 20ኛዉ፣ 24ተኛዉ እና 25ተኛ ክፍለ ጦሮች እና ከሌሎች ተጨማሪ 6 ክፍለ ጦሮች 239 የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች በቁጥጥር ስር እንዲዉሉና ለሕግ እንዲቀርቡ በመከላከያ ሚኒስቴር ለወታደራዊ ደህንነቱ ትእዛዝ ቢያሳልፍም ወታደራዊ ደህንነቱ የመከላከያ ሰራዊት አባልቶችን ያለበቂ መረጃ አሳልፌ አልሰጥም! በቂ መረጃም ከተገኘባቸዉ መከሰስ ያለባቸዉ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ዉስት ነዉ!
በሚል አለምግባባት አጣብቂኝ ዉስጥ መግባታቸዉን ከስፍራዉ የደረሰን ጥብቅ መረጃ አመልክቷል።
በዚህ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች የተነሳ በመላዉ ሐገሪቷ ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ መደናገጥና አለመግባባት እንዲሁም አለመተማመን ነግሶ የሚገኝ ሲሆን አብዛኞች ባገኙት አጋጣሚና መንገድ እራሳቸዉን ለማግለል ተገደዋል እየተገደዱ ነዉ ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ! !
No comments:
Post a Comment