Tuesday, May 24, 2016

በተለምዶ አሜሪካ ግቢ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ለዘመናት የኖሩ ዜጎች “መጠለያ አልባ” ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናገሩ


ግንቦት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ቤት የማፍረስ እርምጃው መቀጠሉትን ተከትሎ፣ ከትናንት ጀምሮ መርካቶ የሚገኘውና በተለምዶ አሜሪካ ግቢ በሚባለው አካባቢ እና አጎራባች ቀበሌዎች የሚገኙ ቤቶች እየፈረሱ ነው። ይህን ተከትሎ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ የኖሩ ዜጎች ተለዋጭ መጠለያ ባለማግኘታቸው ማደሪያቸውን በቤተክርስቲያን ፣ በመስጊድ ወይም በጎዳናዎች ላይ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ወኪላችን በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው ሰዎች ፣ በአካባቢው አዳዲስ ህንጻዎች መሰራታቸው ተገቢ ቢሆንም፣ ደሃውን እያስለቀሱና ቤት አልባ እያደረጉ መሆን አልነበረበትም ይላሉ።
ነዋሪዎች እንደሚሉት፣ ለተነሽዎች 25 ካሬ ቦታ እንሰጣለን በሚል ከሶስት አመታት በፊት ቃል የተገባ ቢሆንም፣ ምንም አይነት ተለዋጭ ቤትና ቦታ ሳይሰጥ አብዛኞቹ እቃዎቻቸውን ሳየወጡ ልቀቁ በመባላቸው ችግር ላይ ወድቀዋል። ከዚህም አልፎ ደምብ አስከባሪዎችና ፖሊሶች ህዝቡን በዱላ እንደሚማቱ ነዋሪዎች ገልጸው፣ ድርጊቱ አገር እመራለሁ ከሚል መንግስት እንደማይጠበቅ ገልጸዋል።
ቤታቸውን ያላፈረሱ ሰዎች ንግድ ፈቃዳቸውን መቀማታቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ በአገሪቱ አንድ አመጽ ቢነሳ በበዳዮች እና በተበዳዮች መካከል የሚኖረው ግጭት የከፋ እንደሚሆን ያስጠነቀቅቃሉ።
ከሶስት አመታት በፊት በፈረሱ የንግድ ቤቶች ላይ እስካሁን ምንም አይነት ግንባታ አለመፈጸሙንም ወኪላችን አክሎ ገልጿል ።

No comments:

Post a Comment