ከፕላን ኤ ወደ ፕላን ቢ በመሸጋገር የኦሮሚያን ማስተር ፕላን በተለየ መልኩ ለመተግበር መዘጋጀቱን በሰሞኑ አቅርበን የነበረ መሆኑ ይታወሳል በመሆኑም ይህዉ የወያኔ ግፈኛ ቡድን ከራሱ ጋር እጅና ጕንት የሆኑ የጥቅም ባለሐቦች ጋር በተገባባዉ ቃል መሰረት በማስተር ፕላኑ የተካተቱ ቦታዎችን ለባለሐብቶች መሸጥ እንዳይችል በደረሰበት ተቃዉሞ ምክንያት በመገደዱ ፕላን ቢ በተግባር ላይ ዉሎአል።
የፕላን ቢ እቅድና ተግባራዊነት የተጀመርዉ በዲስ አበባ ዙሪያ በሕገ_ወጥ ግንባታ ስም መኖሪያ ቤቶችንና የመሳሰሉትን የህዝብ ንብረቶች በማዉደም የተለቀቁ ቦታዎችን ቃል ለተገባላቸዉ ባለሐብቶች መለገስ ሲሆን ሕዝብን ማሰርና ማንገላታት መግደል ፈለገዉም አልፈለገዉ የተገኘበት ማረፊያ ቦታ መወርወር ለተግባራዊነቱ ስከታማነት አይነተኛ መፍትሄ ተደርጎ ተሰምሮበታል።
ፕላን ቢ ይዞታዉን በማስፋት በአረንጕዴ ልማት ስም በአስኮ፣ በቡራዩ፣ በከታ እንዲሁም በሱሉሉታ የሚዘረጋ ሲሆን በካራ፣ በእንጦጦ፣ በካራቆሬ፣ በሰበታ፣ በሜታ አቦ፣ በሞጆ፣ እና በተለያዩ ስፍራዎች በተመሳሳይ መልኩ በልማት ስምና ጠቀም ያለ ገንዘብ ለባለእርስቶች በመስጠት እንዲሁም በሕገ_ወጥ ግንባታ ስም የመሬት ሽያጩን ለመተግበር ኢንቅስቃሴዉ በስራ ላይ ዉሎአል።
በተለይም የአዲስ አበባን ሕዝብ በናቀና ባዋረደ መልኩ ተጠባባቂ የተግባራት መፈጸሚያ የማድረጉ ሁናቴ ህዝቡ ምንም መፍጠር የማይችል ከርታታ ከአፈሙዝ በታች የተገደደ መሆኑን ያመላከተ እጅግ አሳዛኝ ክስተት መሆኑን መረጃዎቻችን በቁጭት ሲናገሩ።
ጉዳዩ ኢጅግ ያሳሰባቸዉ የዉስጥ ሰዎች ደግሞ ይህ ጅማሮ ለብዙሃን የአዲስ አበባ ወገኖቻችን መበታተንና መድረሻ ማጣት እንዲሁም የመሰረታዊ ፍላጎቶች የማግኘት ሁናቴን በማጥበብ ቤተሰቦችን እጅግ የከፋ ችግር ዉስጥ የሚከትና ሕጻናቶች የትምህርት የጤና እና የተለያዩ መሰናክሎች ሰለባ እንዲሁኑ በማድረግ ትዉልድ ላይ የሚሰራ በደል እና በታሪክ ከተጠያቂነት የማያድን ዉርስ ነዉ በማለት ሐዘናቸዉን በመግለጽ ለመላዉ የአዲስ አበባ ህዝብ።
“ በምርጫ 97 ወቅት ቂም የተያዘበትን የአዲስ አበባን ሕዝብ ለማጥፋት በተነሱ ግፈኞች ላይ በአንድነት እንዲነሳ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል “
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
No comments:
Post a Comment