በሚያዝያ እና በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ እየተሰሙ ያሉት ነገሮች የ እግዚአብሔር ቁጣ ናቸው ያስብላሉ ያሉን አንድ አስተያየት ሰጪ ናቸው:: ከሚያዝያ ወር ጀምሮ እየተሰማ ያለው ነገር እጅጉን የሚዘገንና ሃገሪቱ በተፈጥሮ ቁጣ እየተገረፈች ዜጎቿም እያለቁ ነው:: በባሌ ዞን 9 ሰዎች በጎርፍ አደጋ መሞታቸው በዘ-ሐበሻ የተዘገበ ሲሆን ከሃገር ቤት ሚዲያዎች መረዳት እንደተቻለውም በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳይ ወረዳ በአምስት ቀበሌዎች ላይ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም በደረሰ የመሬት ናዳ 41 ሰዎች ሞተዋል:: በመሬት ናዳው የተነሳ የሞቱ የሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን የአስከሬን መፈለጉና የነብስ አድኑ ሥራ እንደቀጠለ ከመረጃዎች መረዳት ይቻላል::
በባሌ ዞን በደረሰ የጎርፍ አደጋ 9 ሰዎች እንዲሁም በወላይታ ዞን 41 ሰዎች ከማለቃቸው 3 ቀናት በፊት በአዲስ አበባ አዳማ ፈጣን መንገድ ላይ ዛሬ በደ
ረሰ አሰቃቂ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በዘ-ሐበሻ ላይ አንብበን ነበር:: ምንም እንኳን ሰው ሰራሽ አደጋ ቢሆንም ከ4 ቀናት በፊትም እንዲሁ በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 2፣ ልዩ ቦታው ጭላሎ ሆቴል ገባ ብሎ እድሜው 55 ዓመት ገደማ ይሆናል የተባለ ጎልማሳ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል:: ይህ ሰው ራሱን ለማቃጠልና ለመግደል የወሰነበት ምክንያት አይገለጽ እንጂ ሰላማዊ ሰው እንደነበር ታውቋል::
በተጨማሪም በ ዕለተ ትንሣኤ ዋዜማ በምዕራብ አርሲ ዞን ዱምቡሬ ቃቻ ወረዳ መሬት ተሰንጥቆ ሸለቆ በመፍጠሩ ወደ ወላይታና አርባምንጭ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ማለፍ እንዳልቻሉና በሰው ሕይወትላይ ከፍተኛ አደጋ ማድረሱ ተዘግቧል:: የተሰነጠቀው መሬት በግምት 50 ሜትር ጥልቀትና 50 ሜትር ርዝመት እንዳለው ታውቋል::
በሌላ በኩል በሻሸመኔ አካባቢ የተከሰተ የመሬት መንሸራተትም እንዲሁ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል:: ከሻሸመኔ አጄ እስከ አላባ ና ወላይታ እስከ አርባምንጭ የሚያስኬደው መንገድ አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት ሳቢያ ለመንቀሳቀስ ህዝብ ተቸግሯል::
ይህ ብቻ አይደለም ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ለብሔራዊ ስታዲየም ፕሮጀከት ግንባታ በቁፋሮ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች የተከመረ አፈር ተደርምሶባቸው ሕይወታቸው አልፏል::
ከሁለት ሳምንት በፊት ማለዳ 12 ሰአት ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሰሚት አካባቢ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ ተደርምሶ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል:: ቁጣው ይህ ብቻ አይደለም ሸዋሮቢት ከተማ ሚያዚያ 10 ቀን 2008ዓ.ም. ከጠዋቱ 1:30 – 4:30 ሰዓት በጣለው ከባድ ዝናብ በታሪኳ አይታው በማታውቀው ከባድ የጎርፍ አደጋ ተመታለች። ከ400 በላይ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ሲፈናቀሉ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ንብረት አውድሟል፡፡
ድሬደዋ ከተማም በ10 ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጠቅታ በርካቶች ተጎድተዋል:: በአካባቢው ከዚህ ቀደም ሕይወት በቀጠፈው የጎርፍ አደጋ ከተከሰተ በኋላ የተሰራው ድልድይም ጉዳት ደርሶበታል::
የሚሰማው ነገር ሁሉ የሚያሳዝን በመሆኑ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለው የ እግዚአብሄር ቁጣን ለመመለስ ሁሉም በየሃይማኖቶ ሊጸልይበት ይገባል::
No comments:
Post a Comment