Monday, May 2, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ገና ከጅምሩ አንግቦ የተነሳው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቱ የተከበረበት የኢኮኖሚ ብልጽግና ማህበራዊ ፍትህ የሚያገኝበት የዜጌችን ህይወት ደህንነትና ጥቅም የተከበረበትን ሀገር እንዲኖረው ማድረግ ነው።


ይህንን ራዕይ አንግቦ የተነሳው አርበኛች ግንቦት 7 ገና ከማለዳው ይህን የእናት ጡት ነካሽ የወንበዴ ቡድን በምን አይነት ስልት ስርዓቱን ማስወገድና ላዴና ለመጨረሻ ከስልጣኑ መንግሎ ለመጣል አቅዶ የተነሳው፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኑ በማድረግ በአሁን ሰዓት በሁሉም አቅጣጫ ትግሉን በፋፋም ላይ ይገኛል ፡ይህም በስርዓቱ ላይ ትልቅ መደናገጥ ፈጥሮበታል በዝህም የተነሳ በመከላከያ ሃይሉ ውስጥ ትልቅ የመረበሽና ይህ የአንድ የብሄር የበላይነት የነገሰበት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እስከ መቼ ነው? የበይ ተመልካችና ስልጣን ላንድ ብሄር  የሚታደልና ያለምንም የወታደራዊ ሳይንስና የከፍተኛም ሆነ መስመራዊ መኮንን ኮርስ ሳይወስዱ ሌላውን ብሄር ዝቅ አድርጎ በማየት እነሱ ብቻ ማዕረግ በማዕረግ የሚሆኑት የአንድ ሃገር የመከላከያ ሰራዊት በማይባልበት ሁኔታ በሃገርና ህዝብ ላይ በመቀለድ የራሱን ሆድ በመሙላት የሚታወቀው ወያኔ ሌላውን ኢትዮጵያዊ በማግለል ያለኛ ጀግና የለም በማለት የሀገሪቱ ድበርና የአየር ክልል ሲጣስ ቁጭ ብለው በመመልከት ወራሪ ጦር ከደቡብ ሱዳን ተነስቶ የሀገራችንን ድበር ጥሶ በወገኖቻችን ላይ ጭፍጨፋ ሲያካሄድና አግተው ሲሄዱ በታሪክ ኢትዮጵያን በማዋረድና ክብሯን በማሳጣት አሁን ላይ ስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት ተብዬ ነው።

በአንድ የብሄር የበላይነት የተዋቀረው የመከላከያ ሃይል ከውስጡ ብቅ ብቅ ባሉ የስርዓቱ አስከፊነትና ለኢትዮጵያ የወደፊት ራዕይ የሌላቸው ከሃዲዎች መሆናቸውን የተረዱ ስርዓቱን በመተው ከነጻነት ሃይሎች ጋር በመቀላቀል ለነጻነትና ለፍትህ እንድሁም ለሁላችንም የምትሆን ሁሉን ህዝብ በእኩልነት የምትመለከት ኢትዮጵያን ለመመስረት ቆርጠው ለመታገል ተነስተዋል፡
ዛሬ ከምን ግዜም በላይ እያንዳንዱ ኢትዮጵያ ይህ ትግል የኔ ነው የሚልበት ወቅት በመድረሱ፡ የአርበኞች ግንቦት 7 የሚያካሄደውን የነጻነት የኢኩልነት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የመመስረትና ስፊውን ህዝብ የስልጣን ባለቤት በሚያደርገው ትግል ውስጥ እጅግ ብዙ የሚባሉ ድሎችን በዚህ አረመንያዊ የወያኔ አገዛዝ ላይ ከህዝባዊ አመጽ አንስቶ እስከ ትጥቅ ትግል በሚደረጉ ትግሎች ድልን በማስመዝገብ ላይ ነው።
ይህም ውጤት የመጣው ሰፊው ህዝብ ከጎኑ በሆኑና ሌት ተቀን በሚያሳየው ተሳትፎና አጋርነት  አሁንም ባገኘው ውጤት ሳይኩራራ የተያያዝነው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቱ የተከበረበት የኢኮኖሚ ብልጽግና ማህበራዊ ፍትህ የሚገኙበት የዜጎች ህይወት ደህንነትና ጥቅም የተከበረበት ሃገር እንዲኖረው ማድረግ ይህን ራዕይ ይዞ የሚንቀሳቀሰው አርበኞች ግንቦት 7 ቀዳሚ ተልዕኮ የመንግስትና የፖለቲካ ስልጣን በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበትንና የሀገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገልጽበትን ብሄራዊ ስርዓት እንዲገነባ ማድረግ ነው።
02/05/2016
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
  


No comments:

Post a Comment