Tuesday, May 3, 2016

ኦሜድላ ንጉስ ሃይለስላሴ ፋሺስቱ ጣሊያን እንደተሸነፈ ከስደት በሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ነጻነታችንን በማወጅ ሰንደቅ ዓላማችንን በክብር የሰቀሉበት ቦታ ነው። ህወሀት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ስር ባደረጋት መተከል ዞን የሚገኝ ታሪካዊ ቦታ ነው።


ዘንድሮ የሱዳን ወታደሮች መፈንጪያ: የኢትዮጵያውያን የስቃይ ቦታ ሆኗል። ትላንት ከአከባቢው በደረሰን መረጃ የሱዳን ወታደሮች ከቅዳሜ ጀምረው በመተከል ዞን ጎባ ወረዳ ኦሜድላ ቀበሌ ሰርገው በመግባት ኢትዮጵያውያንን ደብድበዋል ። በርካታ መኖሪያ ቤቶችን አፍርሰዋል። የእርሻ ቦታዎችን አቃጥለዋል። ህዝባችንን በገዛ ሀገሩ አርባ ገርፈውታል። ንብረቱን ቀምተው ወስደዋል ። እስከአሁን በህይወት ላይ የደረሰ የሞት አደጋ ባይኖርም 67 ኢትዮጵያውያንን አፍነው ወስደዋል። ጥቃቱ እስከእሁድ ምሽት ቀጥሎ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።
የሱዳን ወታደሮች ድንበር ተሻግረው ሲመጡ: ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃዩና አፍነው ሲወስዱ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በቅርበት ነበር። ሪፖርትም ተደርጎለታል። ለኢትዮጵያውያን የሚደርስም ሆነ ከሱዳኖች ዱላና አፈና የሚያስጥል ግን የለም።
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

No comments:

Post a Comment