Wednesday, May 18, 2016

ሰበር ዜና... በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊዉ አማራ እየተፈለገ ነዉ!




አማራን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚል ህሳቤ ዋና አጀንዳዉን ገንዘብ ማሰባብሰብና ብሐረሰቦችን ማጋጨት ያደረገዉ ወያኔ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በሚገኘዉ ኢንባሲዉ አማካኝነት የአማራ ብሔር ተወላጆችን ብቻ እያሰሰ ይገኛል።
የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን ኢትዮጵያዊያን ብሐረሰቦችን ለማጋጨት በዋነኛነት ከሚጠቀምባቸዉ መንገዶች አንዱ እና ዋናዉ አነስተኛ መጠን ያላቸዉ ብሔረሰቦችን ተጠቃሚ ባላደረገ መልኩ የአማራ ልማት መሐበር፣ የኦሮሞ ልማት መሐበር፣ የትግራይ ልማት መሐበር በሚል መነሻ ሐሳብ ከፍተኛ የገንዘብ ዝርፊያዉን በማካሄድ ኢትዮጵያዊነትን በዘር የበላይነትና የበታችነት እንዲተያዩ የማድረጉ ሴራ እና ማናቆሩ ከተጠነሰሰ ሰንብቷል። 
ይህንኑ ተግባራዊ ባደረገ መልኩ ዛሬ በመላዉ አለም ላይ ወያኔ አማራን ተጠቃሚ ያደረገ የሚል የገቢ ማሰባሰብ አጀንዳ የያዘ ተንኮል ጠንስሶ እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም ከወደ ደቡብ አፍሪካ የደረሰን መረጃ እንሚያመለክተዉ የወያኔ ቅጥረኞች በኢንባሲዉ ዉስጥ ተቀምጠዉ አማራ ወደሆኑት ወገኖቻችን በተለይም የቤተክርስቲያን አገልጋዬች፣ የነጋዴ መሐበረሰቦች፣ እንዲሁም ምሁራንና ደጋፊዎቻቸዉ ጋር በቀጥታ ስልክ በመደወል ቅዳሜ ግንቦት 13 ከምሽቱ 11 ሰአት ጀምሮ ስብሰባ በመጥራት ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ የህዝብና የሐገር ጠላት የሆኑ የኢንባሲዉ ተወካዮች የትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን ግፍና በደል አስመርሯቸዉ በስደት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የሚደርስባቸዉን ዉርጅብኝ በመፍራት ምክንያት የስብሰባዉ ቦታን ሳይገልጹ ስብሰባ በመጥራት ላይ ተጠምደዋል በመሆኑም ከዉስጥ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተዉ ስብሰባዉ እዚያዉ ኢንባሲዉ ቅጥር ግቢ ዉስጥ መሆኑን እና እንደአስፈላጊነቱ በቅርብ ወደሚገኝ ስፍራ ሊቀየርም እንደሚል ነዉ። 
በዚህ ሁኔታ ላይ አስተያየታቸዉን የሰጡን አንድ ግለሰብ ከኢንባሲዉ የስልክ ጥሪ እንደደረሳቸዉ ገልጸዉ ነገር ግን እኔ አማራ አይደለሁም የደቡብ ሰዉ ነኝ በማለታቸዉ ምክንያት " ይቅርታ እርሶን አይመለከትም " የሚል ምላሽ ስለሰጣቸዉ " ኢትዮጵያዊነቴን ተፈታተኑት " ሲሉ ምሬታቸዉን ገልጸዋል። 
ሌሎች ወገናዊነት የሚሰማቸዉና የተሰማቸዉ ኢትዮጵያዊያን በበኩላቸዉ ማንኛዉም በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ግለሰብ እንደዚህ ካለዉ የመከፋፈል ስብሰባ እራሱን በማግለል እንዲጠነቀቅ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment