Saturday, May 21, 2016

''በዋናነት ማለት የምፈልገው፣ ምንም ክስ ቢነሳም፣ ለእኔ ትልቁ ነገር የኢትዮጵያ መንግስት የጀመረውና የሚመራው የኢኮኖሚ ልማት አቅጣጫ፣ የሚሳካ መሆኑ ነው፡፡


በአንዳንድ ሰዎች ክስ ቢነሳም፣ ድክመታችንን የሚያሳይ አይደለም፡፡ በዚያው ልክ፣ ጥንካሬያችንንም የሚያሳይ አይደለም፡፡ዋናው ጉዳይ እኛ ድክመት ቢኖርብንም ባይኖርብንም፣ የልማታዊ ኢኮኖሚ አቅጣጫ አይቆምም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ያድጋሉ፡፡ እኔ ካጠፋሁ ልቀጣ እችላለሁ፡፡ ተቋማት ግን ይቀጥላሉ፤ መቀጠልም አለባችሁ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ፣ በግሌ አስተያየት፣ ስኳር ኮርፖሬሽን ውድቀት አለው ብዬ አላምንም፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን የወደቀበት ምክንያት በእንቶኔ ነው በእከሌ ነው ቢባልም፣ አይገባኝም፡፡'' የሜቴክ ሃላፊ ብ/ጄ ክንፈ ዳኘው ለኣዲስ አድማስ
እንግዲህ 77ቢሊየን ነው ገንዘቡ። ካጠፋሁ ልቀጣ እችላለሁ ብለዋል። ድብን አድርገው ነው ያጠፉት። ትልቅ ጥፋት። ሀገርን የሚያወድም ጥፋት። እናም ይቀጡ።
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

No comments:

Post a Comment