Tuesday, May 17, 2016

መረጃ - ወልቃይት ~~~~~~~~~~~ አስገራሚ ዜና በወልቃይት ኣማራ ህዝብ የተፈጸመ!!!


ምስጋና ለቃብትያ ሶላ ህዝብ ይሁን እና ትላንት በ08/09/2008 ዓ.ም በቃብትያ ኣዲ ህርዲ ከተማ በተደረገው ህዝባዊ ስብስባ ታላቅ ድል እና መልካም ጅማሮ ታየ ። ወደ 4ሺ ገደማ ህዝብ በተገኘበት ስብሰባ የተወሰኑ ውሳኔዎች ሰላማዊ ትግሉ የበለጠ እንዲጎመራ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያደረገ እና ለሌሎችም ትምህርት ሰጪ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በህዝባዊ ስብሰባው ከተወሰኑ ዋና ዋና ውሳኔዎች መካከል
1ኛ) እኛ የቃብትያ -ሶል የአማራ ህዝብ የማንነት ጥያቄ እንጂ ህዋሃት ሊያደናግር እንደሚፈልገው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ኣይደለም።
2ኛ) የማንነት ህገመንግስታዊ ጥያቂያችን እስኪመለስ ድረስ ማንኛውም ማህበራዊ ኣገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋማት ምሳሌ ት/ት ቤት፤ ፖሊስ እና ቀበሌ ጽ/ቤት የመሳሰሉት እንዲዘጉ።
3ኛ) የራሳችንን ህዝባዊ ዳኞችንም መርጠናል ፤ የእኒህ ሽማግሌ ዳኛዎችም ተግባራቸው የእርስ በእርስ ጠብ ካለ ፖሊስ ጣቢያ ወይንም ፍርድቤት ሳይኬድ እራሳቸው በራሳቸው በተመረጡ ዳኞች ይዳኛሉ።
4ኛ) የማንነት ህገመንግስታዊ ጥያቄው መልስ ካላገኘ ማንኛውም የቃብትያ -ሶላ ተወላጅ በትግራዮች ምግብ ቤት፤ መጠጥ ቤት እና ሱቅ የመሳስሉት እንዳይጠቀም ቃል ገብተው ተማምለዋል!!

5ኛ) መሬት እንሰጣችኋለን እየተባሉ ለሚሄዱ ወጣቶች ከዚህ በኋላ ያለንን መሬት በጋራ ተካፍለን እናርሳል እንጂ የማንነት ጥያቄውን ለማዳፈን ለሚቀርብ የመሬት ማባበያ ተገዥ አንሆንም። የህዝባችን እንግልትና ውርደት ነው አሳሳቢው ጉዳይ እንጂ ወልቃይት ጠገዴ ዛሬም ነገም አማራ በመሆኑ እና መሬቱም የራሳችን ስለሆነ ነገ ማንንም ተሽክሞት ስለማይሄድ የማንነት ጥያቂያችንን በትዕግስትና በህግ እልባት እስኪያገኝ ድረስ እንታገላለን ሲሉ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።
ይህ ሰላማዊ ትግል በሌሎች የወልቃይት እና ጠገዴ አካባቢዎች ብሎም በመላው የአማራ ምድሮች መስፋፋት እና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ቤተ-አማራ ለመላው ህዝባችን መልእክት ማስተላለፍ ይፈልጋል።
ድል ለወልቃይት - ጠገዴ የአማራ ህዝብ!

No comments:

Post a Comment