Saturday, May 7, 2016

ድሮ እና ዘንድሮ በ ጀግኖቹ አርበኞቻቸን የኑሮ እይታ ሲነጻጸሩ

በታምሩ ገዳ
Hiber-radio-ethiopian-patriot-001በንጉሱ ዘመን ፦”የኢትዮጵያ አርበኞች ሰለማነነታቸው አስመስክረው የከተማ ቦታ እና የእርሻ መሬት ይሰጣቸው ነበር።”
በደርግ ዘመን፦” ጀግኖቹ አርበኞች እርቃናቸውን ቀሩ፣የጀግነነት ኒሻናቸውን በእየ መስጊዱ እና በእየ ቤተክርሲቲያኑ ደጃፍ እያነጠፉ ይለምኑ ነበር። ሞታቸውንም ይናፍቁ/ይመኙነበር ። ”

በዘመነ ኢሕ አዲግ፦”ድሮ በወር ከ 10 ብር እስከ 50 ብር ያገኙ የነበሩት አርበኞች በአሁኑ ወቅት የጡረታ አበላቸው እስከ 700 ብር ደርሷል።ጡረታቸውንም ወደ ፊት ከፍ ለማድረግ ጥረት እያደረግን ነው።”ምንጭ የ ጥንታዊ አርበኞች ማህበር ፕ/ት ልጅ ዳንኤል መሰፍን ጆቴ ለጀርመን ራዲዮ የእማሪኛው ክፍለ ጊዜ ሃሙስ (በትላንትናው እለት ) የተከበረውን 75ኛው የጀግኖች አርበኞች አባቶቻችን እና እናቶቻችን ተጋድሎ የአልማዝ ኢዮቤሊዩ ክብረ በአልን በማሰመልከት ከሰጡት አሰተያየት የተቀነጨበ ነበር ።
ታዲያ የገበያው ሁኔታ ከሸማቾች የመግዛት አቅም አንጻር ድሮ እና ዘንደሮ ሲገመገምስ?፦
ድሮ(በዘመነ ጃንሆይ ወይም በደርግ) በ50 ብር አንድ ቤተሰብ ጥግብ ብሎ ከወር ወር ይድረስ ነበር። በግ ለመብላት ከተፈለገ የቆዳ ሽያጩ ሳይካተት ከ 75 ብር በታች ይገኝ ነበር። ለ አምሮት ወደ ሆቴል ጎራ ከተባለ ወይም ወንደላጢነት ላጠቃው ደግሞ በትንሹ በ በአንድ ብር ከሃምሳ ሳንቲም (1፡50) ሰጋ ወጥ(ቅልጥም ያለው) አሊያም ትሪ ሙሉ በእየ አይነቱ ምግብ (ወጥ አስጨምሮ) ይበላ ነበር ፡የአበሻ ዶሮ እንቁላል በ አንድ ብር ከ3 እስከ 4 ተመርጦ ይገዛ በር ፡ ዶሮም ቢሆን አውራ ዶሮ ከ 20 ብር ከበለጠ “የዘንድሮ ገበያ ለጉድ ነው! ሰማይ ነክቷል ! ይባልለት ነበር ።
ዘንድሮስ? አ/አ ሳሪስ ገበያ ላይ አንድ አውራ ዶሮ ከ 300 ብር እስከ 340 ብር ድረስ ለፋሲካ በአል ተሸጣል ።በግ ደግሞ ከ 3ሺህ እስከ 4ሺህ መሸጡ ይነገራል። ታዲያ ለእናት ሃገር ኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና ለማነነታችን ክብር ሲሉ በዱር በገደሉ በገንዘብ እና በአልማዝ መተኪያ የሌለው መሰዋትነት የከፈሉት ጀግኖቹ አርበኞቻችን ውለታ የከፈለው የትኛው ስር አት/ትውልድ ይሆን?ዘላለማዊ ከብር ፣ሞገስ እና ረጅም እድሜ ለ ጀግኖቹ አርበኞቻችን ይሁን!!!
ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

No comments:

Post a Comment