Wednesday, May 4, 2016

በቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ ላይ የተመሰረተው ክስ ቻርጅ እጃችን ገባ – ፌስቡክ ላይ በጻፋቸው ጽሁፎች አሸባሪ ተባለ

 የኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ስር ዓቱን በነቀነቀው ወቅት ከታሰሩት በርካታ ሰላማዊ ታጋዮች መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ወጣት ዮናታን ተስፋዬ  ረጋሳ ላይ የሽብርተኝነት ክስ ተመሰረተበት::

“ተከሳሽ የፖለቲካ; የአይዲዮሎጂ ዓላማን ለማራመድ በመንግስት ተጽ ዕኖ ለማሳደር ሕብረተሰቡን ወይም የህብረተሰቡን ክፍል ለማስፈራራት እና የሃገሪቱን መሰረታዊ; ፖለቲካዊ; ሕገመንግስታዊ; ኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ ተቋማትን ለማናጋት እና ለማፈራረስ አስቦ ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ግምባር (ኦነግ) ብሎ በሚተራ አሸባሪ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች ህብረተሰቡን የአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞኖች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሽፋን በማድረግ ከህዳር ወር 2008 ዓ/ም ጀምሮ የተጠቀሱትን አመጽና አድማ መሰረት በማድረግ ከህዳር 24 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በሚጠቀምበት ድህረ-ገጽ በተለይም በፌስቡክ ተጠቅሞ በሽብር ቡድኑ የተጀመረውን አመጽና ብጥብጥ በማስቀጠል” በሚል በቀረበበት ክስ ዮናታን ፌስቡክ ላይ በተለያዩ ጊዜያት የጻፋቸው ጽሁፎች ተጠቅሰው አሸባሪ ተብሎ ተከሷል::
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/54025

No comments:

Post a Comment