Friday, May 6, 2016

መረጃ... በደቡብ አፍሪካ ለምትገኙ ወገኖቻችን መልካም ዜና አለን..



በትናንትናዉ እለት 03/05/2016 በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ በተለይም በስደተኝነት ተመዝግበዉ ሕጋዊ ለሆኑና ሕጋዊ ለመሆን መብታቸዉን ለሚጠይቁ እንዲሁም በጥላቻ ( xenophobia ) ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሁሉ አጋር የሆነዉ የደቡብ አፍርካ መንግስት፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጠበቃ ቢሮ ( lawyers of human right in south Africa ) እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በደቡብ አፍርካ ( Ethiopian community in south Africa ) እና ሌሎችም አካላት አጋርነታቸዉን መግለጻቸዉን ከስፍራዉ የደርሰን መረጃ ያመለክታል።
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የወያኔን ስርዐት ጠልተዉ በደቡብ አፍሪካ ጥገኝነት የተሰጣቸዉ ኢትዮጵያዊያን በጥላቻ ( xenophobia ) እንዲሁም በሙስና ምክንያት በብርቱ እየተጠቁ መሆኑን የሰባዊ መብት ጠበቆች በማረጋገጥ መፍትሄ ብጤ ይዘዉ ተከስተዋል ...ለምሳሌ 
___አንድ በደቡብ አፍሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ስደተኛ በደቡብ አፍሪካ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ያለምንም ክፍያ በነጻ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ማግኘት ሲገባዉ በደላሎችና በስተርጓሚዎቹ አማካኝነት ራንድ R. 6.000 መክፈል ይጠበቅበታል.. 
___አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ የ 4 አመት ጊዜያዊ ወረቀት ለማግኘት ፈጽሞ እንዳይችል በሙስና ምክንያት የታገደ ሲሆን የ 6 ወራት ብቻ ጊዜያዉ ወረቀት ይሰጠዋል በየ ስድስት ወሩ ለማደስ የሚደርስብት ስቃይ እጅግ አሳዛኝ ነዉ..
___አንድ ስደተኛ ኢትዮጵያዊ የ4 አመት ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ካለዉ ለመንግስት ራንድ R. 400 ከፍሎ ደረሰኝ በማስቆረጥ የመታወቂያ ወረቀት ( ID ) የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ነገር ግን ራንድ R. 300 እስከ 500 ጉቦ ካልፈከለ ያማግኘት መብቱ የተነፈገ ነዉ።
__አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ጊዜያዊ የመታወቂያ ወረቀት ካለዉ ራንድ ለመንግስት አካል R. 400 ከፍሎ ደረሰኝ በማስቆረጥ ፓስፖርት ( Travel document ) የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ራንድ R. 700_1000 ጉቦ የመክፈል ግዴታ አለበት 
__ በተለይም አንዳንዶች በተለያየ ምክንያት ወረቀታቸዉን ሳያሳድሱ እረዘም ላለ ወቅት የቆዩ ከሆነ ለመንግስት አካል የቆይታ ግዴታ ( over stay ) ራንድ R. 1000 በመክፈል ፕሪቶሪያ ቲሮ አካባቢ በሚገኘዉ የስደተኞች ቢሮ በግንባር ሄዶ ወረቀቱን የማራዘም መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ነገር ግን ጉዳዩ ለሚመለከታት ብቸኛ አካል ለሆነችዉ ጁአና ለተባለች ግለሰብ ራንድ R. 6000_9000 ጉቦ መክፈል ግዴታ አለበት። በመሆኑም የደቡብ አፍሪካ የሰባዊ መብት ተከራካሪዎች ይህንን ሁሉ ጉዳይ ከጥላቻ ( xenophobia ) 
ነጥለው ባለመመልከት በደቡ አፍሪካ ከሚመለከታቸዉ ከፍተኛ መንግስታዊ አካላት ጋር በመምከር ዉሳኔ ላይ ደርሰዋል ! በዉሳኔዉም መሰረት ማንኛዉም ስደተኛ የጥላቻ ጥቃት( xenophobia ) ከደረሰበት ወይም ምንም አይነት የጥቃት እንቅሳሴ ሲመለከት! እንዲሁም በሙስና ምክንያት፤ በትራፊክ ፖሊስ እና በህዝባዊ ፖሊስ፣ በፍርድ ቤቶችና በስደተኞች ቢሮ ( Department Of Home Affairs ) መጉላላትና ሲደርስበት በቀጥታ በመንኛዉም ወቅትና ሰአት ሳምንት ሙሉ ለ 24 ሰአት 24/7 ከዚህ በታች በሰፈሩት አድራሻዎች በመደወል ህግ እንዲከበር ትብብር እንድያደርግ።
ለስቸኳይ እርዳታ ( FOR EMERGENCIES )
helpathand@lhr.org.za
+27(0)11 339 1960 ( JHB )
+27(0)12 320 2943 ( Pta )
+27(0)32 301 0531 ( Durban )
+(0)15 534 2203 ( Musina )
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment