Wednesday, May 4, 2016

ታፍነው የተወሰዱትን ልጆች የምናገኝበት ዕድል እየጠበበ መጥቷል

ሲካሰሱ የቆዮት የደቡብ ሱዳን የሙርሌ አካባቢ ባለስልጣናት ዕርቅ ፈጸሙ
meeting-with-david-yau-yau_1_11የደቡብ ሱዳን ምክትል መከላከያ ሚንስትር ተደርገው በቅርቡ የተሸሙት ዴቪድ ያዩ ያዩ ትናንት ማክሰኞ ከቦማ ክልል ገዢ ባባ ሜዳን ጋር በፕሬዘዳንቱ ሳልቫ ኪር ሸምጋይነት ዕርቅ መፈጸማቸውን አስታውቀዋል፡፡
ያዩ ያዩና ሜዳን ሙ
ርሌዎች በብዛት በሚገኙበት የቦማ ክልል ለወራት ባላንጣዎች ሆነው ቆይተዋል፡፡በቅርቡ የፈጸሙት የዕርቅ ስምምነትም በሁለቱ ሰዎች ታጣቂዎች መካከል የነበረውን መፋጠጥ ያረግበዋል ተብሎ ተስፋ ተደርጓል፡፡
ሁለቱን ሰዎች በማስታረቅ ሂደት የሳልቫኪርን ይሁንታ ውክልና በማግኘት ሲንቀሳቀሱ የቆዩት የሙርሌው ፖለቲከኛ አኮት ሉዋል ዕርቁ ግቡን መምታቱን በማስታወቅ ሁለቱ ሰዎች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ያዩ ያዩ በበኩላቸው ‹‹አሁን በቦማ ክልል በሚገኙ ፖለቲከኞችና መሪዎች መካከል ምንም አይነት ችግር የለም፡፡ፕሬዘዳንት ሳልቫኪር የነበረውን ችግር ፈትተውታል፡፡ፖለቲከኞቹም ይቅርታ በመደራረግ ከአሁን በኋላ ተባብረው ለመስራት ቃል ገብተዋል››ሲሉ በሽምግልና ሳልቫኪርን በመወከል ሲሳተፉ የቆዩት አኮት‹‹ጀነራል ያዩ ያዩ አሁን በአገር አቀፍ ደረጃ ምክትል መከላከያ ሚንስትር በመሆን ለመስራት ተስማምተዋል፡፡ከነበሩበት የተወሰነ ቦታ ገዢነት አንጻር ስንመለከተውም አዲሱ ስልጣን በብዙ መንገድ የተሻለ ነው››ብለዋል፡፡
ባባ ሜዳን የያዩ ያዩ ተከታዩችን በጋምቤላ ክልል ለተፈጸመ ጥቃት ሲከስሱና ታፍነው የተወሰዱትን ህጻናት ለማስመለስ ከኢትዮጵያና ከደቡብ ሱዳን መንግስታት ጋር እንደሚሰሩ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ያዩ ያዩ በበኩላቸው ጥቃቱን ያደረሱት የሜዳን ሰዎች መሆናቸውን ሲናገሩ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡
ሁለቱ ሰዎች የነበራቸውን ቁርሾ በመተው በጋራ ለመስራት በመስማማታቸው አንዳቸው ሌላኛቸውን እንደቀድሞው የሚከሱበትና የሚያጋልጡበት ሁኔታ አይኖርም፡፡የኢትዮጵያ ወታደሮች የሁለቱን ሰዎች ቅራኔ በመጠቀም እስካሁን ምንም ማድረግ ባለመቻላቸውም በቀጣይ አንዱ በሌላው ጣልቃ ለመግባት ስለማይፈቅድ ህጻናቱን በህይወት ማግኘት የበለጠ አስቸጋሪ እንደሚሆን እየተነገረ ነው፡፡
http://www.satenaw.com/amharic/archives/16243
ምንጭ ራዲዩ ታማዙጂ

No comments:

Post a Comment