Tuesday, May 24, 2016

*በኮንሶ የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ከወር በፊት በእስር ቤት ከታጎሩ እስረኞች መካከል 59 የሚሆኑት እስር ቤት ሰብረው አምልጠዋል። ሰበራውን ያቀነባበሩት "ትግላችን ይቀጥላል!" ይላሉ



*በሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል፣ ከድብደባ እና ጥይት የተረፉ ተማሪዎች ወደየቤታቸው ሄደዋል። ታደሠ የተባለ የሀይርድሮሎሊክ ኢንጂነሪንግ ተማሪ መገደሉ እየተነገረ ነው።
ኅዳር 1 የጀመረው የኦሮሚያ ሕዝባዊ ንቅናቄ ጋብ ያለ ሲመስል አመጹን አንቀሳቅሰዋል፣ ተሳትፈዋል የተባሉ ተማሪዎችን የመንግስት ደህንነትና ፖሊሶች እያፈኑ መውሰዳቸው በዩኒቨርስቲው ዳግም አመጽ እንዲነሳ ማድረጉን ተማሪዎች ይገልጻሉ።
*77 ቢሊየን ብር የፈሰሰበትን 10 የስኳር ፕርሮጀክቶች ግንባታ ኮንትራት ወስዶ ከግንባታ ማጠናቀቅያ ጊዜው አልፎ 3 ዓመታት የተቆጠሩበት ብረታ ብረት እና ኢንጂሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፉ ዳኘው "በግሌ አስተያየት፣ ስኳር ኮርፖሬሽን ውድቀት 
አለው ብዬ አላምንም፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን የወደቀበት ምክንያት በእንቶኔ ነው በእከሌ ነው ቢባልም፣ አይገባኝም፡" ሲሉ የተፈጠረውን ቀውስ አጣጥለዋል።
ተጨማሪ ፕሮግራሞች አሉን ኢሳትን አድምጡ!

No comments:

Post a Comment