Sunday, May 22, 2016

ወቅታዊ ሀገር የማዳን የደጀንነት ጥሪ !!! ________________________________ ሀገርዎ በእንዴት ያለ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳለች ያውቃሉ? ይህን የሀገርዎንና የወገንዎን የማያባራ ችግር ከወገንዎ ጋር በጋራ ለመፍታትስ ቁርጠኛ ነዎት? እንግዲያው አያስቡ በኖርዲክ ሀገሮች የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊያን፤ ሀገራችን ሰላም የሰፈነባት፣ ነጻነት ያበበባትና የሁሉም መብት የተከበረባት ሀገር ትሆን ዘንድ እየወደቀና እየሞተ ላለው የሀገር አድን ሰራዊት የሚውል ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅተውለዎታል። ባጋጣሚውም “ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ” ነውና፤ ትግሉ አሁን የደረሰበትን ሀቅና ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንክሮ በመውጣት ወደፊት በፍጥነት ስለሚገሰግስበት ሁኔታ ከንቅናቄው ሊቀመንበር ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ይመክሩበታል። ከዚህም በላይ ለኢትዮጵያ የማይሆን ኢትዮጵያዊነት አይኖርምና ይህን ሀገር አድን ሰራዊት በገንዘብ በመደገፍ ደጀንነትዎን ከማስመስከርዎም በላይ ከወገንዎ ጋር ኢትዮጵያዊነትን በጋራ ለመዘመር እድል ያገኛሉ። ያስታውሱ በኖርዲክ ሀገሮች የሚኖሩ ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊያን በጁን 4፣ 2016 በኖርዌይ፣ ኦስሎ ከተማ ባዘጋጁት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ለመገኘት ካሁኑ የግል ፕሮግራምዎን ያስተካክሉ። በእርግጥም ለኢትዮጵያ የማይሆን ኢትዮጵያዊነት የለምና በዚህ ሀገራዊ ጥሪ ቀን ቢቀሩ በእውነት ይፀፀታሉ። ምናልባት ልጅ ካለዎት? ልጄን ማን ይጠብቅልኛል ብለው መጨነቅ አይገባዎትም፤ ምክንያቱም ለህጻናት መጫወቻ የሚሆን በቂ ቦታ ተዘጋጅቶልዎታልና!! በሁኔታዎች አለመገጣጠምም ሆነ የምትኖሩበት ሀገር ሩቅ በመሆኑ መምጣት ላልቻላችሁ፤ ነገር ግን ይህ እድል እንዲያልፈኝ አልፈልግም ለምትሉ ቁርጠኛ ዓለማቀፍ ረጅዎችም መላ አልጠፋም Iban number NO6815037614421 Swift code DNBANOKKXXX Account no. 15037614421 ብላችሁ መላክ ትችላላችሁ ጁን 4 2016 በ 14፡00 ሰአት በኦስሎ ከተማ፤ አዘጋጅ ኮሚቴውAG 7

No comments:

Post a Comment