በጋምቤላ ክልል ጥቃት መፈጸማቸው የሚነገርላቸው የሙርሌ ታጣቂዎች
(ሳተናው) የደቡብ ሱዳን ቦማ ክልል ባለፈው ወር ታፍነው ከተወሰዱ ህጻናት መካከል 44 ያህሉን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፉ መስጠቱን ትናንት አርብ ይፋ አድርጓል፡፡
የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይ ጁሊያ ጄምስ ለራዲዩ ታማዙጂ እንደነገሩት
ከሆነ ህጻናቱ ከጋምቤላ ክልል በኃይል ታፍነው እንደተወሰዱ ከተነገረላቸው 100 ህጻናት መካከል የሚገኙ ናቸው፡፡
ቃል አቀባይዋ ቀሪዎቹን ህጻናት ለማስመለስ የቻሉትን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ በአካባቢው በመጣል ላይ በሚገኘው ከባድ ዝናብ የተነሳ መንገዶች በመፈራረሳቸው እክል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡
የቃል አቀባይዋ ስለሁኔታው የሰጡት ማብራሪያ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ወደ ደቡብ ሱዳን ፖቻላ ግዛት መግባታቸው በተነገረ ማግስት ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ከቦማ ክልል የተረከቧቸውን ህጻናት በመያዝ ፎቶ ግራፍ በመነሳት ‹‹ህጻናቱን አስለቀቅን››የሚሉትም የክልሉ ባለስልጣናት ባደረጉት አሰሳ ህጻናቱን አሳልፈው ከሰጧቸው በኋላ መሆኑም ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል፡፡http://www.satenaw.com/amharic/archives/16527
ምንጭ ራዲዩ ታማዙጂ
No comments:
Post a Comment