Thursday, May 12, 2016

ጎርፍ ሌላኛው የኢትዮጵያ ፈተና

floodጎርፍ ያስከተለ ከባድ ዝናብ በኢትዮጵያ ካለፈው ወር ወዲህ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ እንደሚገኝ ተነገረ፡፡አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም እንደገለጸው ከሆነም 120.000 ኢትዮጵያዊያን በጎርፍ ምክንያት የመኖሪያ አካባቢያቸውን በመልቀቅ ለስደት ተዳርገዋል፡፡
ለሶስት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ጠፍቶ የነበረው ዝናብ በኢትዮጵያ መጣል በመጀመሩና
መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ መንገዶች፣መኖሪያ ቤቶች፣እንስሳት፣ድልድዩችና ሰዎች በወንዞች ሙላት ምክንያት መወሰዳቸው ተነግሯል፡፡
ዝናብ ጠፍቶ በመቆየቱ የተነሳ 15 ሚልዩን ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ሆነዋል ያለው ድርጅቱ በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኙ 6 ወረዳዎች ከሚገኙ ሰዎች መካከል 119.711 ከጎርፍ ጋር በተያያዘ ቀያቸውን ለቀው ወደ አጎራባች ወረዳዎች መሰደዳቸውን አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ 190.000 ሰዎች ክፉኛ በድርቅ ከተጎዱ አካባቢዎች ካለፈው ወር ጀምሮ በመጣል ላይ ከሚገኘው ዝናብ ጋር በተያያዘ መሰዳዳቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
ወንዞች በመሙላታቸውና ጎርፍ በመፍጠራቸው መንገዶች ፈራርሰው ድልድዩች በመሰበራቸው የእርዳታ እህሎችን ለተጎጂዎች በማድረስ ስራ ላይም እንቅፋት መፈጠሩን አይ ኦ ኤም አስታውቋል፡፡ በድርጅቱ ትንበያ መሰረትም በቀጣይ 485.610 ሰዎች በያዝነው ዓመት ብቻ ለስደት ሊደረጉ ይችላሉ፡፡
የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን በደቡብ ኢትዮጵያ ከጎርፍ ጋር በተያያዘ የ50 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን መግለጹ አይዘነጋም፡፡
ምንጭ አይ ኦኤም

No comments:

Post a Comment