Wednesday, May 11, 2016

በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሃረር ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ታወቀ


ግንቦት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ በብዛት የአማራ እና ደቡብ ተወላጆች ምስራቅ እዝ ሚሊተሪ እስር ቤት ጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። እስረኞቹ ከተለያዩ አካባቢዎች ተሰብሰብው የመጡ ሲሆን፣ አንዳንዶች በሰራዊቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሆነ የብሄር የስልጣን ክፍፍል እንዲኖር የጠየቁ ናቸው። ምስራቅ እዝ እስር ቤት ከምስራቅ እዝ ሆስፒታል ጎን የሚገኝ ሲሆን፣ እስር ቤቱ ከምድር በታች ስቃይ የሚፈጸምበት ቦታ እንዳለው ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
እስረኞቹ በድብደባና በሌሎችም የማሰቃያ ዘዴዎች ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ወታደራዊ ወይም ሲቪል ፍርድ ቤት ይቅረቡ አይቀረቡ የታወቀ ነገር የለም።

No comments:

Post a Comment