የሩዋንዳ ማስታወሻ -በታምሩ ሁሊሶ “…..ሩዋንዳ ስር የሰደደ ጥላቻና ውጤቱ ማሳያ ሙዚየም ናት። መገናኛ ብዙሃን ከምንም በላይ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ለማረዳት የፈለገ፤የሩዋንዳን ታሪክ መቃኘት ብቻ ይበቃዋል። ቱትሲዎች በገጀራ ከመሳደዳቸው አስቀድሞ በጋዜጦች፤በቴሌቪዥንና በሬድዮ ተሳደዋል፤ተሰድበዋል፤ተረግመዋል።፡የቤተክርሰቲያን አባቶች፤-“ ቱትሲን ያገባ ሁቱ፤ውሻ ይውለድ!!”ሲሉ ገዝተዋል። ከዚህ ሁሉ ሰይጣናዊ ቅስቀሳ በኋላ ሁቱዎች ገጀራ እንኳን ቢያጡ ቱትሲዎችን በጥርሳቸው እንደሚበሏቸው ግልጽ ነበር።
የዛሬይቱ ኢትዮጵያችንም ውስጥ ከወዲያና ከወዲህ የጥላቻ ጥንስሱ በደንብ ደርሶ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ጠላው እየተጠጣላት ነው። ጥቂቶችም ሰክረው ያዙኝ ልቀቁኝ ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ “ደም መላሾች ነን” ያሉ ድገሙኝ ከጠላው እያሉ ነው፡፡” የማን ቤት ፈርሶ ፤የማን ሊበጅ” እየተዘፈነ ነው፡፡ማዶና ማዶ የቆሙ ባለጌዎች ሰዎችን በጅምላ ይሳደባሉ፡፡ ብሄርን እንደፈለጉ የሚሳደቡ ሞልተዋል፡፡ “የኔ ዘር ባለምጡቅ ጭንቅላት፤የዛኛው ግን እንጭጭና ዘገምተኛ” ነው እያሉ አደባባይ ላይ የሚያስመልሱት እንደልብ ናቸው፡፡ነጭ ባንዲራ ላይ ጥቁር ሽንት የሚሸኑ በርክተዋል፡፡ሽንታቸው ቶሎ ታጥቦ እንደማይለቅ፤ነጩን ባንዲራም እንደሚያመነችከው እርግጠኞች ናቸው……
No comments:
Post a Comment