Saturday, July 2, 2016

ነዋሪዎች መውደቂያ አጥተናል ሲሉ እያማረሩ ነው በላፍቶ ክ/ከተማ ቀርሳ ከንቱማና ማንጎ ሰፈር በተባሉ አካባቢዎች ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች ከትላንት በስቲያ ጀምሮ በአፍራሽ ግብረ ኃይል እየፈረሱ ሲሆን በአጠቃላይ 20 ሺ ገደማ ቤቶች ሊፈርሱ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ዜጎችን ያለመጠለያ የሚያስቀር ስርዓት! እጅግ በጣም ያሳዝናል!! ህወሓቶች በህዝቡ ላይ የሚፈፅሙት ግፍና በደል እለት በዕለተ ሆኖል። እነሱ ከኮንዶሚኒየም ቤት እስከ ቪላ ቤቶች ብሎም እጅግ በጣም የተንጣለለ አፓርታማ ላይ እየኖሩ ይህን ህዝብ ችግር እንዴት ብለው ይመልከቱ! ወቅቱ ክረምት ነው በዝናብና በብርድ ቤታቸውን በላያቸው ላይ ማፍረሱ እውን ተገቢ ነው ? በልማት ስም የሚደረገው የመሬት ነጠቃ በህብረተሰቡ ዘንድ ትልቅ ችግር ሆኗል። በህወሓት የሚመራው መንግስት ከህዝቡ ጋር አይጥና ድመት መሆኑ እስከመቼ? ህዝቡስ መቼ ይሆን መብቱ የሚከርለት? ኢትዮጵያ ህዝብ ፎቅ አልተራበም! የኢትዮጵያ ህዝብ የተራበው መልካም አስተዳደር! ይህ ትልቅ ችግር ከጉያቸው አስቀምጠው ልማት ኖረ አልኖረ ህዝቡም ሆን ሀገሪቱ ላይ ምንም ፋይዳ አያመጣም!
Vi

a :- Kalkidan Kassahun

No comments:

Post a Comment