Tuesday, July 5, 2016

የሌንጮ ለታ ኦዴፍ እና የፕ/ር ብርሃኑ አርበኞች ግንቦት 7 ወደ ጥምረት እያመሩ ነው ተባለ

lencho leta and berhanu negaከመሳሪያ ትግል ወደ ሰላማዊ ትግል በማምራት ከኦነግ ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባርነት የተቀየረው የአቶ ሌንጮ ለታ ኦዴፍ ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 
አርበኞች ግንቦት 7 ጋር በጋራ ለመስራትና ወደ ጥምረትም ለማምራት ንግግር ላይ እንዳሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳሉት የሌንጮ ለታ ኦዴፍ አሁንም ሃገር ቤት ገብቶ መታገልን እንደአማራጭ የያዘ ሲሆን ሁለገብ ትግልን ከሚያራምደው የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ለመስራትና ለመጣመር የወሰነው በተለይ በሃገር ቤት ያለው የፖለቲካ ምህዳር የባሰ እየጠበበ ከመጣ በኋላ ነው ተብሏል::
በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ንግግሩ የተጀመረው ቆየት ብሎ ነው ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች አርበኞች ግንቦት ሰባትም ሆነ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በመጪው ኦገስት ወር ላይ ጥምረታቸውን ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ ብለዋል::
አቶ ሌንጮ ለታ ትግሎ ሃገር ቤት መግባት አለበት ብለው ወስነው ኢትዮጵያ ሄደው ከኤርፖርት መንግስት እንደመለሳቸው ይታወሳል:: ኢትዮጵያ በሄዱበት ወቅትም ጀነራል ሳሞራና የደህንነቱ ሚንስተር አቶ ጌታቸው አሰፋ አቶ ሌንጮን ለማሰር ሞክረው ሌላ ሃይል ወደ መጡበት ይመለሱ በሚል ወደ መጡበት እንዳስመለሳቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች ይናገራሉ::
http://www.zehabesha.com/amharic/?p=62669

No comments:

Post a Comment