*በመተማ ጓንግ የኢትዮጵያ መሬት ወረራ ተፈጽሞበት ከገዳሪፍ የመጡ 7 የሱዳን ወታደሮች በገበሬው ተገደሉ። ጎዳናው አምዴ የተባለ ኢትዮጵያዊ በግጭቱ ሕይወቱ አልፎ በዛሬው ዕለት በክብር ተቀብሯል። *አበበች በጋሻው የተባሉ ከለንደን የመጡ ዳያስፖራ የእርሻ መሳርያዎቻቸው በሱዳን ታጣቂዎች መውደሙን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። *መከላከያ ሠራዊት ወደ ስፍራው ቢያመራም ገበሬዎቹ ቦታውን እንዲለቁ ከማዘዝ በስተቀር በሱዳን ጦር ላይ የወሰደው እርምጃ የለም። ሆኖም ገበሬው አሻፈረኝ ብሎ መሳሪያውን ታጥቆ ድንበር ላይ አድፍጧል። *የሱዳን ታጣቂዎች በመተማ አካባቢ ባሉ ቦታዎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው እየገቡ በርካታ ዜጎችን እንደሚገድሉ የሚታወቅ ሲሆን የሱዳን መንግስት ገዢው ሥርዓት ህወሓት ለመስጠት የተሰማማውን መሬት(የኢትዮጵያን) በአሰቸኳይ የድንበር ማካለል እንዲያደርግ እና እንዲያስረክብ እየወተወተ ይገኛል ESAT DC Special Program Metema Mon 04 Jul 2016
No comments:
Post a Comment