አዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ሰሞኑን 13,980 ቤቶች መፍረሳቸውን ሰሞኑን አንብበናል።
እናም ከዚህ ውስጥ ብዙ አሳዛኛ ክስተቶች አሉ ዛሬ የአንዷን ቤት አልባ የሆነች ሴት ታሪክ ልንገራችሁ ።
አንዳንዴ ዕድል እግር በእግር ይከተላል መሰለኝ ተወልዳ ብዙም ሳትቆይ እናቷም አባቷም ይሞታሉ የገጠር ነገር እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ አደገች እዚያው አካባቢ በ14 ዓመት ዕድሜዋ ትዳር ትይዛለች ዕውነት የማይመስል ትዳር ስትገፋ አንድ ሴት ልጅ ትወልዳለች በባሏ ቤተሰብ ችግር ይፈጠርና ወደ አዲስ አበባ ይሰደዳሉ አዲስ አበባም ፊቷን አዞረችባቸው እንጂ አልተቀበለቻችውም ኑሮ ሲከፋ ተፋቱ ልጃንም ብቻዋን ማሳደግ ግድ ሆነ ችግሩ እየጠነከረ ሲመጣ ከዘመድ ገንዘብ ተበድራ ልጇንም ለአክስቷ ልጅ አደራ ሰጥታ ወደ አረብ ሃገር ሄደች ።
እዚያም በግርድና (በባርነት) ብለው ይቀለኛል ያጠራቀመቻትን ብመለስም መግቢያ ልጄን ይዬ መግቢያ ትሆነኝ ብላ 120 ሺህ ብር ይዛ የመጣችውን በጠቅላላው አውጥታ ዛሬ ከፈረሱት ቤቶች አንዱን ትገዛለች ቤቱን ከገዛችም በኋላ ባዶ እጃን በመቅረቷ እንደገና ወደዚያው ወደ ባርነቱ የምትወዳትን የልጅነት ልጇንናፍቆት ሳትጨርስ ተመልሳ ሄደች ከሄደችም ያገኘችውን እየላከች ቤቷን ዞሮ መግቢያዋን ለማሻሻል ሞክራ ነበር እጅግ አሳዛኙ በግርድና ተጠብሳ ያፈራችው ልጇን በናፍቆት አንገብግባ ያጠራቀመችው የቀለሰችው ጎጆ ፈረሰልሽ ብለው መርዶ ነግረዋታል እዚያው ሆና እስቲ ወገን ይህን ምን ትለዋለህ ይቺ ድሃ የድሃ ድሃ ከእንግዲህ እንዴት ሰው ሆና መቆም ትችላለች?
No comments:
Post a Comment