Thursday, July 7, 2016

“ድንቁርና እውቀትን ያሸነፈበት የታሪክ አጋጣሚ የለም፡፡ ስለዚህ እኛም እንደምናሸንፍ ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም” ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ



ትግላችን ድንቁርናን አስወግደን በእውቀት ለመተካት ነው
ድንቁርና የዘረኝነት ምንጭ ነው፡፡ ድንቁርናም ቀንደኛ የእድገት ፀር ነው፡፡ ዘረኝነት ደግሞ ከእድገት ፀርነቱ ባለፈ የሰላም ጠንቅ መሆኑ
ጥያቄ የለውም፡፡ በተለይ አለማችን ከደረሰችበት የስልጣኔ ደረጃ አንፃር ሲታይ ዘረኝነት ከከፋ ድንቁርና የመጣ በሽታ መሆኑን አጉልቶ
ያሳያል፡፡ የኛዎቹም ዘረኞች የዚህ በሽታ ተጠቂ ለመሆናቸው የቅርብ ጊዜው የሁለተኛው አለም ጦርነት ያስከተለውን ከፍተኛ የህይወትና
የንብረት ውድመትን እንኳ መመልከት ያለመቻላቸው ያረጋግጥልናል፡፡
ዘረኝነትን ቁልፍ መሰባሰቢያውና በእብሪት መወጠሪያው አድርጎ የተነሳው የሂትለሩ ናዚ የጀርመን ምርጥ የሰው ዘርነት ፍልስፍና ከራሱ
አልፎ የአለም ጦርነትን ከመለኮሱና በሚሊዮን የሚቆጠር የሰው ህይወት የበላና መጨረሻው ተንኮታኩቶ አስከፊ ውድቀት ከመ ውደቅ ማለፍ
አልቻለም፡፡ የሰው ልጅ በተወለደበት አካባቢና በተገኘበት ዘር መስፈርን ዋነኛ ስራው ያደረገው የሂትለሩ ናዚ በሰፈረው ቁና ለመሰፈር ብዙ
አልራቀም፡፡ ከናዚ መንኮታኮት ባለፈ ኩራት ብለው የተነሱለት ጀርመንነት በራሱ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የቆየበት ፈ ተና ቀላል አልነበረም፡፡
እንዲህ አይነት ምሳሌዎችን ካለፉ የሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ብዙ ብዙ ማንሳት ይቻላል፡፡ ዋናው ዘረኝነት ው ሎ አድሮ ውጤቱ ውድቀት፤
ውድመትና ኪሳራ መሆኑና የሰው ልጅን በተወለደበት አካባቢ፤ በቆዳው ቀለም፤ በፆታ፤ በተገኘበት ዘር ወዘ ተ የመደልደል የዘረኝነት ቦታ
ከድንቁርና የሚመጣ ክፉ ደዌ መሆኑ ፤ ይልቁንም ለዘረኝነት ልቡን ክፍት ያደረገ ምንም ያህል በዘመና ዊው እውቀት የመጠቀ ቢሆን ውጤቱ
ውድቀተ በመሆኑ ከደናቁርቱ ተርታ ከመመደብ አልፎ አያውቅም፡፡ ወደፊትም አይሆንም፡፡ የእ ኛዎቹም ደናቁርት እንዲሁ,,,,,..
ወያኔ ህወሀት የፍትህ ፤ የእኩልነትና የዲሞክራሲ ጥያቄ ሳይሆን በዘረኝነት ላይ ተመስርቶ የተወለደ፤ በለስ ቀንቶት ለስልጣን ከበቃበት
ጊዜም በዃላ ፍትህ፤ እኩልነትና ዲሞክራሲ የእሱ ጥያቄ ያለመሆኑን፤ ይልቁንም ዘረኝነት የሀገሪቱ መሪ የፖለቲካ ፍልስፍና በማድረግ ወደዚህ
አቅጣጫ እየተገፋን መቆየታችን ማንነቱን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ የትግራይ ቁጥቋጦ የአማራ መቀበርያ ይሆናል ከሚለው የበረሀ መዝሙር
ጀምሮ ስልጣን ከተያዘ በዃላ ዜጎችን በዘር የመከፋፈል ስራ ከምንም በላይ ሲሰራ መቆየቱ ለዘረኝነቱ በራሱ ፍልስፍናና ተግባራዊ
እንቅስቃሴው በገሀድ የታየ እውነት ነው፡፡እንዲያውም ኮ/ል መንግስቱ የትግራይ ተወላጅ ቢሆን ኖሮ ህወሀት አይፈጠርም ነበር የሚለው
የህዝብ አስተያየት ምን ያህል በዘረኝነትና በመንደርተኝነት የተለከፈ የደናቁርት ስብስብ መሆኑን ያሳያል፡፡
የናዚ በጀርመናዊነት ላይ የተመሰረተው የዘረኝነት ፍልስፍና አንድ ሰሞን ድምፁ ጎላ ብሎ ቢሰማም መጨረሻው ታላቅ እናደር ገዋለን
ባሉት ጀርመናዊነት ላይ ያስከተሉትን ውድመት ስናይ ህወሀት የተነሳለት ትግራዋይነት ሊያስከትል የሚችለውን መዘዝ መገመት
አያዳግትም፡፡በዘረኝነት የደነቆሩት ናዚዎች የደረሰባቸው ውድቀት ህወሀቶች ላይ አይደርስም ማለት ሞኝነት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ነገር ግን
ይህን ተራራ የሚያክል እውነት ናዚዎች እስከ መጨረሻው ሰአት ድረስ አላመኑም፤ አልተቀበሉም፤ ህወሀቶችም ያምናሉ ወይም ይቀበላሉ
ብሎ መጠበቅ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደተባለው ነው፡፡ የዚህ ዋነኘው ምክንያቱ ደግሞ የተጠናወታቸው ድንቁርናና ለእውቀት
ያላቸው ግምት አናሳነት ነው፡፡
በተወሰነ ይህን ካልኩ ወደ ዋናው ርእሴ አብረን እንመለስ፡፡ እኛ በአርበኞች ግንቦት ሰባት የተሰባሰብን የአንድ እናት ልጆች የተ
ያያዝነው ትግል ለፍትህ ፤ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ፤ ባጠቃላይ ለነፃነት መሆኑ በራሱ ድንቁርናን አስወግደን በእውቀት ለመተካት መሆ ኑን
ያረጋግጣል፡፡ሰው በሰውነቱ የሰውነት ነፃነቱን ለማስከበር መታገል መቻሉ እውቀትን መሰረት ለማድረጉ ጥያቄ የለውም፡፡ ምክንያቱ ም ዛሬ
አለማችን ለሰው ልጅ የሰጠችው ክብርና ነፃነት ከደረሰችበት የእውቀትና የስልጣኔ ደረጃ አንፃር መሆኑ ሲያረጋግጥልን በተጨማ ሪ ድንቁርና
መቼም እውቀትን ያሸነፈበት የታሪክ አጋጣሚ ያለመኖሩን ያሳየናል፡፡
ባጠቃላይ ደንቆሮ ፍትህ እኩልነትና ነፃነት ምን ማለት እንደሆነ አያውቅም ፡፡ ዘረኛም ዘረኛ ነውና ሊገባው የሚችል ነገር አይደለም፡፡
ይህ ማለት ደግሞ ዘረኝነት ድንቁርና መሆኑን፤ ድንቁርናም የዘረኝነት ምንጭ መሆኑን ያሳያል፡፡ስለዚህ እኛ አርበኞች ግንቦት ሰባቶች ትግላችን
ከድንቁርና ጋር ነው ማለት ነው፡፡ ድንቁርናም ሆነ ዘረኝነት ለጊዜው ካልሆነ በስተቀር በዘላቂነት ያሸነፉበት አጋጣሚ ባለመኖሩ እንደምናሸንፍ
አንዳች ጥርጣሬ ሊኖረን አይገባም፡፡
ትግላችን ድንቁርና የፈጠረውን ዘረኝነት አስወግደን ሀገራችንንና ህዝባችንን የእውቀት ፍሬ የሆነውን የሰለጠነው አለም ካስገኘው የሰው
ልጆች ነፃነት ተቋዳሽ የማድረግ ትግል መሆኑን በመገንዘብ በሙሉ ልብና በራስ በመተማመን ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ ትግላችንን
በየአቅጣጫው ማቀጣጠል ይጠበቅብናል፡፡ ትግላችን ድንቁርናን አስወግዶ እውቀትን ማንገስ መሆኑ በራሱ አሸናፊነታችንን ያረጋገጠ በመሆኑ
ጠንክረን በመስራት የድንቁርና ምሳሌ የሆነውን ወያኔ ህወሀት እድሜ ለበማሳጠር እንነሳ ስል የመሪያችንን ንግግር በማስታወስ ነው፡፡ “Ύ
ድንቁርና እውቀትን ያሸነፈበት የታሪክ አጋጣሚ የለም፡፡ ስለዚህ እኛም እንደምናሸንፍ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለኝም”

No comments:

Post a Comment