Thursday, August 31, 2017
ሎሬት ቴዎድሮስ ካሳሁን
የትኛውም በህጋዊነት የተቋቋመ ኪነ ጥበባዊም ሆነ ሁለገብ የአለም ላይ ተቋም በራሱ ዘርፍ እጩዎችን አዘጋጅቶ የመሾም ሙሉ መብት አለው። ያን ለማድረግ መስፈርቶች አሉት እነዛን መስፈርቶች ላሟላ ሰው ተገቢውን ክብር እዳይሰጥ የሚያግደው የለም። ለምሳሌ ዩኒሴፍ የአለም የሰላም አምባሳደር እና የአመቱ ምርጥ አባት በማለት ሲሾም እና የአለም ምርጥ አባት ብሎ ሲያከብር አይተናል ቴዲንም የአመቱ ምርጥ አባት ሲል አክብሮታል።
ትላንት ምሽት ነሀሴ 23/12/09/ አቢሲንያ የሽልማት ተቋም በሀርመኒ ሆቴል ባዘጋጀዉ የሽልማትና እዉቅና የመስጠት ስነ ስርአት ለሀገራቸዉ ከፍተኛ ስራን የሰሩ ግለሰቦችን በክብር ሸልሟል። ከነዚህም ዉስጥ የሙዚቃ ጥበባት የሙዚቀኝነት ሁለንተናዊ ክዋኔ የከፍተኛ ክብር ተሸላሚ (ሎሬት) የተሠኘው ሽልማት /ማዕረጋዊ የመጠሪያ ስም/ ለቴዲ አፍሮ ተበርክቷል!! ሎሬት ቴዎድሮስ ካሳሁን ተብሎ ተሰይሟል!
@አምለሰት ሙጬ
የስራ ማቆም አድማዎች በትብብር እንዲካሄዱ ጥሪ ቀረበ (ኢሳት ዜና ነሃሴ 25 ቀን 2009 ዓም)
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የስራ ማቆም አድማዎች ብሄራዊ ቅርጽ ይዘው እንዲከናወኑ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል። በመጪው መስከረም 2 ቀን 2010 ዓም የታቀደው የስራ ማቆም አድማ እውን እንዲሆን ከተፈለገ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሊሳተፉበት እንደሚገባ ኢትዮጵያውያን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በቅርቡ በኦሮምያ ተጥርቶ በነበረው አድማ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ ሊሳተፉ ይገባ እንደነበር የሚገልጹት አስተያየት ሰጪዎች ፣ ይህ ባለመሆኑ የህወሃት አገዛዝ ከፋፍሎ ለማጥቃት ተመችቶታል ብለዋል።
ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል፣ “አሁን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዳክሞ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ ትግሉን ለፍጻሜ ለማድረስ ከአካባቢ ፖለቲካ ወጥቶ ብሄራዊ አጀንዳ በመያዝ ሁሉንም ህዝቦች አስተባብሮ ማካሄድ ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚኖር ሌላ ወጣት ደግሞ፣ የስራ ማቆም አድማዎች በህዝብ ላይ ጉዳት ሳያደርሱ በጥንቃቄ ሊካሄዱ እንደሚገባ መክሮ፣ በደንብ በተጠኑ እና ስርዓቱ የገቢ ምንጭ አድረጎ የሚጠቀምባቸውን ተቋማት ለይቶ በእነሱ ላይ አድማ ማድረግ ይገባል ብሎአል። የገዢው ፓርቲ የንግድ ተቋማት የሚያመርቷቸውን ምርቶች ባለመጠቀም፣ እንዲሁም አድማዎች ግልጽ የሆነ ግብ ተደርጎላቸው መካሄድ አለባቸው ብሎአል።
ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ፣ የጠላቶቻችን ሃይል ለይቶ ማወቅ ተገቢ ነው ይላሉ። ትላልቅ መንገዶችን የመዝጋት ጥሪ ሲተላለፍ በጋራ ተግባራዊ ማድረግ አለብን የሚሉት አስተያየት ሰጪው ይህ ካልሆነ የምንከፍለው መስዋትነት ይጨምራል ይላሉ ። አስተያየት ሰጪው አክለው ሲናገሩ “አንዱ ሲመታ ሌላው የሚሰራበት ሁኔታ መቆም አለበት፣ እኛ መናበብ ብንችል ሰዎቹ በትንፋሽ ብቻ ለቀው ይሄዳሉ” ብለዋል። የአጋዚ ወታደሮች አምቡላንሶችን እየተጠቀሙ በህዝብ ላይ እንደሚተኩሱም አስተያየት ሰጪው የአይን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል
ከመስከረም በሁዋላ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተባብሰው ሊቀጥሉ እንደሚችሉ የሚናገረው ሌላው አስተያየት ሰጪ፣ በአድማው በመንግስትና የግል ድርጅቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎችም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል። በተለይ መመህራንና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዋነኛ ተባባሪዎችና አስተባባሪዎች ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጿል።
ኦብነግ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ጠላት የሆነውን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አገዛዝን ለማስወገድ በጋራ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ (ኢሳት ዜና –ነሐሴ 25/2009)
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ጠላት የሆነውን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አገዛዝን ለማስወገድ በጋራ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ።
የህወሀት መንግስት ከዚህ በላይ በስልጣን ላይ ከቆየ ኢትዮጵያን እንደሶሪያና የመን የብጥብጥ ሀገር ሊያደርጋት ይችላል ሲል ኦብነግ አስጠንቅቋል።
አንድ ሀገር አንድ ህዝብ ነን ልዩነታችንን ወደ ጎን በማድረግ የህወሃትን መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንነሳ ብሏል ግንባሩ።
አንድ ከፍተኛ አመራሩ ለህወሀት መንግስት ተላልፈው የተሰጡበት ኦብነግ ዓለም ዓቀፍ ህግን በመተላለፍ የተፈጸመው ተግባር ዋጋ ያስከፍላል በማለት ለሶማሊያ መንግስት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር የተመሰረተው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1976 ነው። ግንባሩ የሶማሌ ክልልን ነጻ ለማድረግ ፕሮግራም ነድፎ ለበርካታ አመታት በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
ሳምንታዊ የሀሳብ ጅረቶች (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የነሐሴ 25 ቀን 2009 ዓ.ም.ፕሮግራም
የሚሉትን ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ http://www.patriotg7.org/ ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ኢትዮጵያ አደገኛ በሆነ አቅጣጫ እየተወሰደች በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ በስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት ለማስወገድ መታገል ይኖርበታል ሲል የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ገለጸ። ኢሳት ዜና –ነሀሴ 24/2009) የኢትዮጵያ ለም መሬቶችን ለሱዳን ለ10ዓመታት በውሰት ለመስጠት በድብቅ ከስምምነት መደረሱን በመጥቀስ ጥሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ፡ የህወሀት መንግስት የጥፋት ግስጋሴ በአስቸኳይ ካልተገታ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው ብሏል። የታላቋን ትግራይ ካርታ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን በማሳየት ህዝቡ እንዲለማመደው እየተደረገ መሆኑና፡ ጎንደርን ለሶስት የመሸንሸኑ እርምጃ የዚሁ የታላቋ ትግራይ ምስረታ አካል ነው ብሏል የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ።
Wednesday, August 30, 2017
እንዴት ሰነበታችኹ ወገኖች? MaMa - ማማ - በማስረሻ ማሞ
እንዴት ሰነበታችኹ ወገኖች?
እርግጥ ነው በቀቢጸ ተስፋና ድንግዝግዝ ባለ ኑሮ ውስጥ የሚላወስን ኅብረተሰብ ‘እንዴት ሰነበትህ ብሎ መጠየቅ ብቻውን አመርቂ አይደለም። ጫዎታና ወግ የሚያምረው ለመሰንበት ቅድሚያ በመስጠት ነውና፦እንዴት ውላችሁ አደራችሁ? እላችኋለኹ በድጋሚ።
በተለያዩ ሚዲያዎች ሲነገር የነበረው የነሐሴ አክራሞት ሁላችኹም እንዳያችኹት በ“ቀቢጸ ተስፋ”ና “በድንግዝግዝ” የተዋጠ ኾኗል። መጪውን ዘመን የጨገገ አስመስሎም እያሳየን ነው።
የአትሌቲክስ ፖለቲካ - የመንፈስ ፖለቲካና የወሰን ግጭት በብሔርተኝትና በማንነት ፈረሶች ላይ እየጋለቡ ነው።
ጥያቄው በአንድም ኾነ በሌላ መንገድ “ጭጋጉን” የምናሳልፈው እንዴት ነው? የሚለው ነው።
ዛሬ ወደ እናንተ የመጣኹት እንደ አንድ ግለሰብ የሚሰማኝን ነገር ለማካፈል በሚል ነው።
ያገር ቤት ናፍቆት ውስጥ ውስጡን እንደሚቦረቡረው እንደ ብዙው ተሰዳጅ ኢትዮጵያዊ ወደ አገር ቤት አልፎ አልፎ ስልክ እደውላለኹ። ከምጠይቃቸው ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ ታዲያ፦ “እንዲያው የሰፈሬ ሰው ሠላምና ፍቅር እንዴት ነው”? የሚለው ነው። በተደጋጋሚ የሚሰጠኝ መልስ ግን አስተካዥ ነው።
“አይ አንተ የምታውቀው ሠላምና ፍቅር አሁን የለም፤ ጎረቤት ከጎረቤት ጋራ መነጋገር ካቆመ ዓመታት ተቆጥረዋል። የተኮራረፈው ይበዛል።” ይሉኛል።
እኔን እንደ አባትም እንደ እናትም ኾነው ያሳደጉኝ ጎረቤቶቼ አይነጋገሩም። በሌላ አነጋገር ከአምስት ቤተሰቦች የተውጣጣ 20 ቤተሰብ በጋራ ተቀምጦ ችቦ አያበራም፤ “ሕዳር ሕዳር - ትወዳለች ማር” ብሎ በየዓመቱ ንፍሮ እየቃመ አይዘፍንም። “አድባር አንቻዬ አንድ ገንቦ ጠላ ለብቻዬ” እያለ የእንቁጢጥ አይጨፍርም።
እንግዲህ በሕይወት እያለሁ የልጅነት ታሪኬ ወደ ተረትነት ኮታ ሲጣል እንዴት አልተክዝ!?
“ለመኾኑ ሽማግሌ የለም በሰፈሩ?” . . . ስላቸው
“ሁሉም ከተጣላ እንዴት ብሎ ሽማግሌ ይኖራል?” ይሉኛል።
ለዚህ ጥያቄ የሚኾን መልስ ለማግኘት ከሰፈሬ ዘበት ወጣ ብዬ ወደ ድሮ ታሪክ ልውሰዳችኹ፡- ታሪኩ ከሽምግልና ጋራ የተያያዘ ነው። በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመን የተፈጸመ ታሪክ ነው። ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ (አባ መላ) በዚህ በኛ ዘመን ቋንቋ - በኾነ ነገር “ይደብራቸውና” ሥራቸውን አስታጉለው ከቤተ መንግሥት ይቀራሉ።
ዳግማዊ ምኒልክ፦ “ይኼ ሰው ምን ኾኗል ሂዱና ጥሩት እስኪ” ብለው ሰው ይልካሉ። አባ መላ “እምቢ” ይላሉ። ምኒልክ ደግመው ሌላ መልክተኛ ይሰዳሉ። አሁንም አባ መላ “አኩርፊያለሁ፤ አኩርፊያለሁ፤ አልመጣም” ይላሉ። መል’ክተኞቹ መል’ክቱን ይዘው ወደ ምኒልክ ይመለሳሉ።
“ምን አላችሁ?” አሉ ምኒልክ።
“አልመጣም አሉን” አሉ መልክተኞቹ።
“ተውት በቃ እኔ እሄዳለሁ።” ብለው ሚኒልክ ወደ ሀብተጊዮርጊስ ቤት ያቀናሉ።
ምኒልክ “አንተ ሰው አኩርፈኸኛል መሰል” ብለው በሩን ከመሻገራቸው - ሀብተጊዮርጊስ ከመቀመጫቸው ተነስተው ኩርፊያቸውን አሽቀንጥረው ይጥላሉ።
ከዚህ ታሪክ የምናተርፈው ነገር፦ “ሁለት የተጣሉ ሰዎች የሚያስታርቃቸው ሽማግሌ ያጡ እንደኾነ፤ አቤቱታ የቀረበበት ሰው ሽማግሌ ኾኖ ወደተበደለው ቤት ሄዶ ነገር ያብርድ የሚል ነው።”
የመከላከያና ፖሊስ አመራሮች ውዝግብ በመከላከያ ሃላፊዎች አሸናፊነት ተጠናቀቀ (ነሃሴ 24 ቀን 2009 ዓም)
ትናንት ማክሰኞ ምሽት አንድ የመከላከያ አባል የሆነ መቶ አለቃ በከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተይዞ በባህር ዳር ከተማ የጣና ክ/ከተማ በሚገኘው 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰረ ቢሆንም፣ ከመከላከያ ካምፕ የመጡ 3 ባለስልጣናት መኮንኑ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀው ነበር። የወንጀል መከላከል ኢንስፔክተር ሙቀት እና የወንጀል መርማሪ ኢንስፔክተር ቢያምር የተባሉት ፖሊሶች ያሰሩትን መኮንን እንዲፈቱ ሲጠየቁ፣ “መኮንኑ ወንጀል በመፈጸሙ መታሰሩን” በመግለጽ እንደማይፈቱት ከመከላከያ ለመጡት ባለስልጣናት ተናግረዋል። ከመከላከያ የመጡት ባለስልጣናቱ “አባላችን ልታስሩት አትችሉም” በማለት ሀይል በተቀላቀለበት ሁኔታ ፖሊሶችን ከተናገሩዋቸው በሁዋላ፣ እስረኛው ከታሰረበት ክፍል እንዲወጣ አዘውታል። እስረኛው ጫማውን አድርጎ ሊወጣ ሲል የጣቢያው ፖሊሶች “በወንጀል ያሰርነውን ሰው እናንተ ምን ስለሆናችሁ ነው የምታስወጡት፣ ስነ-ስርዓት ያዙ ካለበለዚያ እንተኩሳለን” በማለታቸው ፣ የመከላከያ ሃላፊዎች ጉዳዩን ለበላይ ለማቅረብ ተገደዋል። የመከላከያ ሃላፊዎቹ ወደ ፖሊስ ኮሚሽን ቢሄዱም “ ህግ እስከፈለገው ድረስ ልንፈታው አንችልም” የሚል መልስ በማግኘታቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰው በፖሊሶች ላይ ዝተው ወደ ካምፓቸው ተመልሰዋል።
የመከላከያ ባለስልጣናቱ ዛሬ የክልሉን የደህንነት ሃላፊ ፍሰሃ ወ/ሰንበትን ገብተው ያነጋገሩት ሲሆን፣ ፍሰሃም የዞኑን የፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ዳኛውን እንዲፈታው አዞታል።
ONLF decries refoulement of exec member to Ethiopia ESAT News (August 30, 2017)
The Ogaden National Liberation Front (ONLF) denounced the refoulement of Abdikarin Sheikh Muse, an executive committee member of the Front to Ethiopia.
Mr. Sheik Muse, who lived in Mogadishu for three years, was detained by the regional security of the Galkacyo, Galmudug regional state in central Somalia on August 23, 2017, according to a press release by the ONLF.
“He went to Galkacyo to bring back his young niece to Mogadishu for medical treatment where he was apprehended and then transferred to Mogadishu and held by NISA, the Somali national Security for few days,” said ONLF.
Mr. Sheik Muse was then handed over to Ethiopia in violation of the principle of non-refoulement laid out in 1954 UN-Convention, ONLF said adding that “Somali government has forcefully transferred a political refugee to Ethiopia which is known to torture and humiliate its opponents.”
Ethiopia to transfer administrations of disputed territories bordering Sudan ESAT News (August 29, 2017)
The Ethiopian regime is to transfer the administration of disputed areas to the Sudan for a period of ten years, according to sources with access to documents and maps of the disputed areas that locals claim were historically in Gondar.
The new development came after Ethiopia’s Prime Minister paid a visit to the Sudan last month in which border issues were top on the agenda.
The Tigrayan led regime in Addis Ababa has changed the map of Tigray to include areas bordering Gondar and Benishangul regions in what close followers of the political developments say was an attempt to create a “Greater Tigray,” which will border with the Sudan. Map of the Tigray region annexing areas from Gondar and Benishangul was shown on Ethiopian Television twice. The station issued an apology after a storm of indignation and condemnation by the general populace.
Tuesday, August 29, 2017
የህወሃት ደህንነቶች በሌሎች የደህንነት አባላት ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመሩ (ኢሳት ዜና–ነሐሴ 23/2009 ዓም)
በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ስጋት ላይ የጣለው ኢህአዴግ፣ ጥልቅ ተሃድሶ በሚል የዘረጋው አጀንዳ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዳላስገኘለት ከተረዳ በሁዋላ፣ አዲስ የቀረጸው የሙስና አጀንዳ በምን መልኩ ይተግበር በሚለው ላይ የድርጅቱ አመራሮች ግልጽ አቋም መያዝ ተስኖአቸው በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ የህወሃት የደህንነት አባላት ምርመራውን በሚያካሂዱና ሚስጢር ያውቃሉ በሚሉዋቸው የደህንነት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል።
ለወራት ከፍተኛ ባለስልጣናቱን እያወዛገበ የሚገኘው የሙስና አጀንዳ ወደ ስልጣን ፉክክር እየተለወጠ መምጣቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ በቅርቡ የታሰሩ በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ ባለስልጣናትንና ባለሀብቶችን የሚመረምሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሳይቀር በይፋ ራሳቸውን በማይገልጹ ቡድኖች ማስፈራሪያ እየደረሳቸው ነው።
መጀመሪያ በታቀደው መሰረት በሙስና የተጠረጠሩ ባለስልጣናትንና ባለሀብቶችን እንዲመረምሩ ከተመረጡት ደህንነቶች መካከል እስካሁን አንድ የደህንነት አባል መገደሉን ምንጮች ገልጸዋል። ሶሚ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው የደህነነት አባሉ የኦሮሞ ተወላጅ ሲሆን፣ ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር በመቀናጀት በመርምራው ንቁ ተሳተፎ ያደርግ ነበር። ግድያው ከመፈጸሙ በፊት 4 ግለሰቦች ወደ ደህንነቱ ቤት በመሄድ ባለቤቱን ማነጋገራቸው ታውቋል። ሟቹ የደህንነት አባል የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ሲሆን፣ በምርመራው ላይ በስፋት ይሳተፍ ነበር ተብሎአል። ሌላ የደህንነት አባልም እንዲሁ ማስፈራሪያ እንደደረሰውና ተሳትፎውን የማያቆም ከሆነ እርምጃ እንደሚወሰድበት ተዝቶበታል።
የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የነሐሴ 23 ቀን 2009 ዓ.ም.ፕሮግራም
* ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እንዘክረዋለን።
* አቶ ሃብታሙ አያሌው እስር ቤት በነበረበት ወቅት ያሳለፈውን ስቃይና ሰቆቃ አጠር አርገን እናቀርባለን።
የሚሉትን ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን http://www.patriotg7.org/ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
Monday, August 28, 2017
በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ላይ ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ውጊያ መደረጉ ተገለጸ (ኢሳት ዜና–ነሐሴ 22/2009)
በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ላይ ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ውጊያ መደረጉ ተገለጸ።
በሶማሌ ልዩ ሃይልና በኦሮሞ አርሶአደሮች መካከል በተደረገው ውጊያ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው የታወቀ ሲሆን አንደኛው የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ወደ አዳማ ሆስፒታል መወሰዱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ውጊያው መኢሶን በተባለች ከተማ አቅራቢያ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች መካሄዱ ተገለጿል።
በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት የተሳካ የአድማ ጥሪ ያደረጉት የኦሮሞ ወጣቶች በቀጣይ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወጣቶች ጋር ለመስራት እየተዘጋጁ መሆናቸውን በተለይ ለኢሳት ገልጸዋል።
ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ በአንዳንድ አከባቢዎች ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ግጭት የተፈጠረ ሲሆን መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
@ምስል ከፋይል
ከ50 ሺ ኩንታል በላይ ስኳር ወደ ኬንያ እየተጓጓዘ ነው ኢሳት ዜና ነሃሴ 22 ፣ 2009 ዓም
በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስኳር እጥረት ተፈጥሮ ባለበት ሁኔታ፣ ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ መጋዘን ስኳር የጫኑ 125 መኪኖች በኢትዮጵያና ኬንያ ጠረፍ ላይ በምትገኘው ሞያሌ ከተማ ላይ መቆማቸው ታውቛል። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የአገሪቱን የስኳር አቅርቦት መሸፈን ተስኖት፣ ስኳር ከው እያመጣ እንደሚያከፋፍል ቢታወቅም፣ 125 መኪኖች እያንዳንዳቸው 400 ኩንታል በድምሩ 50 ሺ ኩንታል ስኳር በመጫን ወደ ኬንያ እያመሩ ሲሆን፣ በገጠማቸው የቴክኒክ ችግር ምክንያት ላለፉት 25 ቀናት ለመቆም ተገደዋል።
ስኳሩ ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ መጫኑና ወደ ኬንያ እንደሚጓዝ ይታወቅ እንጅ የማን ንብረት እንደሆነ ወይም ለአገር ውስጥ ገበያ ሳይቀርብ ለምን እንደሚወጣ የታወቀ ነገር የለም።
እነዚህ በብራይት ድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት አክሲዮን ማህበር ስር የታቀፉ ከ125 በላይ መኪኖች ወንጅ ፋብሪካ ላይ ለ12 ቀናት ሞያሌ ላይ ደግሞ ለ13 ቀናት ስኳሩን እንደያዙ የቆሙ ሲሆን፣ ወደ ኬንያ ለመግባት በመከልከላቸው ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል።
እያንዳንዱ መኪና በእቁብና በባንክ ብድር የተገዛ እንደመሆኑ እዳችንን መክፈል አልቻልንም የሚሉት ሹፌሮች፣ መኪኖቹ ላለፉት 25 ቀናት በመቆማቸው ስኳሩ በዝናብ ሊበላሽ እንደሚችል፣ እስካሁን ድረስ ለቆሙባቸው የካሳ ክፍያ ማን እንደሚከፍላቸው እንደማያውቁና ኬንያ ውስጥ ከገቡ በሁዋላ ስኳሩን ቶሎ አራግፈው የመመለስ እድላቸው አንስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ። ሹፌሮቹ ስኳሩን ከወንጂ ፋብሪካ መጫናቸውን እንጅ የማን እንደሆነ እንደማያውቁ ይናገራሉ።
ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንለት የ ብራይት ድንበር ተሸጋሪ የደረቅ ጭነት አገልግሎት አንድ ሃላፊ መኪኖቹ ስኳር እንደጫኑ ለረጅም ጊዜ ወንጂና ሞያሌ ላይ መቆማቸውን አምነተው፣ ይህም የሆነው የኬንያ ህግ አንድ የጭነት መኪና ከ280 ኩንታል በላይ ጭኖ እንዳይጓዝ ስለሚከለክልና የእኛ መኪኖች ደግሞ እያንዳንዳቸው 400 ኩንታል የጫኑ በመሆኑ ወደ ኬንያ መግባት አትችሉም በመባላችን ነው ብለዋል። መኪኖች የያዙትን ጭነት እንደያዙ ወደ ኬንያ እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው የኬንያ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ሙከራ እየተደረገ ሲሆን፣ ይህ ካልሆነ ግን ስኳሩ እየተቀናነሰ እንዲጫን ስለሚደረግ በቅርቡ መፍትሄ ያገኛል ብለዋል። ስኳሩ የማን ንብረት እንዲሆነና ለምን ከአገር እንደሚወጣ ግን የገለጹት ነገር የለም።
የኢትዮጵያ ወርኃዊ የስኳር ፍላጎት ወደ 600 ሺ ኩንታል የሚጠጋ ቢሆንም፣ በአገሪቱ ያሉ ፋብሪካዎች በቀን የማምረት አቅማቸው ከ20 ሺ አይበልጥም።
ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ዝነኛው የ“ሕልም አለኝ” ንግግራቸው (የኔነህ ከበደ)
በቀደመው ዘመን አፍሪካ አሜሪካውያን ከባርነት ቢላቀቁም በዘር ላይ ከተመሰረተው ዓይነተ ብዙ መድልዎና ጭቆና ነፃ ለመውጣት እልህ አስጨራሽ ትግልን ጠይቋቸዋል፡፡
ከነዚህ አይነታቸው የበዛ የመብት ማስከበሪያ ጥረቶቻቸው ውስጥ የዋሽንግተኑ ሠልፍ ተብሎ የሚታወቀው ክንውን አንዱ ነው፡፡
የዋሽንግተኑ ሰልፍ የተካሄደው የዛሬ 54 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡
ታዋቂው አፍሪካ አሜሪካዊ የመብት ተሟጋች ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ “ሕልም አለኝ” የሚለውን ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ያስገኘላቸውን አነቃቂ ንግግር ያደረጉት በዚሁ አጋጣሚ ነበር፡፡
በዚያን ጊዜ በአሜሪካ አፍሪካ አሜሪካውያኑ ተመርጠውና ተሾመው ለከፍተኛ ኃላፊነት ለመብቃት ይቅርና መሠረታዊ የመምረጥ መብታቸው በሰፊው ይጣስና ይጨፈለቅ ነበር፡፡
Sunday, August 27, 2017
ኢትዮጵያን ማጥፋት ጭቆናን ማጥፋት አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነትን መካድም ከጭቆና መላቀቅ አይደለም!!! (በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ)
ባለፉት ሃምሳ አመታት በተወሰኑ ኃይሎች ኢትዮጵያዊነትን ማንቋሸሽ ወይም ኢትዮጵያዊነትን መካድ እንደ ተራማጅነትና እንደነፃነት ወይም እንደ ፀረ ጭቆና ትግል የተቆጠረ ይመስላል፡፡ ይህ ግልብና ጥራዝ ነጠቅ አመለካከት በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን ጉልበትና ኃይል አግኝቶ ኢትዮጵያን ማፍረስ ህገ መንግስታዊ እውቅና ተሰጥቶት የማፍረስ መብት ከጭቆና የመላቀቅ አማራጭ ተደርጓል፡፡ በመሰረቱ ግን ይህ የጥራዝነጠቅነትና የቅኝ ገዥዎች ከፋፍለህ ግዛው አስተሳሰብን በጥሞና ለተመለከተው ፀረ ጭቆና ትግል ከሀገርና ከዜግነት ጋር ምንም ዓይነት የሀሳብ ዝምድና የለውም፡፡
በኢትዮጵያ ምድር ዘዴውና ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ከጭቆና እና ከአገዛዝ የተላቀቀንበት ታሪክ የለንም፡፡ በንጉሳዊ ስርዓት፣ በደርግ ወይም በወታደራዊ አገዛዝ፣ በህወሓት/ኢህአዴግ "የብሔር ብሔረሰብ" አገዛዝ ያለፍናቸውን የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን ብንመለከት የጭቆናው ዘዴና ስልት ይለያይ እንጂ በሶስቱም ስርዓቶች ኢትዮጵያውያን ከጭቆና ተላቀን የሀገራችንና የስልጣን ባለቤት ሁነን ወደ እድገትና ብልፅግና አልተራመድንም፡፡ የሀገራችንና የስልጣን ባለቤትም አልሆንም፡፡ ጨቋኞች ይቀያየሩ እንጂ ሁሉም አገዛዞች ለኢትዮጵያውያን የመከራና የግፍ ዘመን ናቸው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት የምናደርገው ትግል ለአገዛዝ ለውጥ ወይም ከጅብ ዋሻ ወደ ጅብ ዋሻ ለመሄድ ሳይሆን በምንም መልኩ የሚፈፀምን ጭቆና እና ኢፍትሐዊነት በማስወገድ በኢትዮጵያ ህዝብ የሀገሩና የስልጣን ባለቤት ሆኖ የሚፈልገውን የሚሾምበት እና የማይፈልገውን የሚሽርበት ህጋዊ ስርዓት በሀገራችን መትከል ነው፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ
የነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዜናዎች
* በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የሥራ ማቆም አድማ በአብዛኛዎቹ የኦሮሚያ ከተሞች ተግባራዊ መሆኑ።
* ጸረ ሙስና ዘመቻው ሥርዓቱን ከመፍረስ የመታደግያ ብቸኛ መንገድ ነው መባሉ።
* በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ለአቤቱታ አዲስ አበባ መግባታቸው።
* በባህር ዳር በግንቦት 20 ክፍለ ከተማ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ መቋረጡ።
የሚሉትን ዜናዎችና ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ http://www.patriotg7.org/ ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የሥራ ማቆም አድማ በአብዛኛዎቹ የኦሮሚያ ከተሞች ተግባራዊ መሆኑ። (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዜናዎች
* ጸረ ሙስና ዘመቻው ሥርዓቱን ከመፍረስ የመታደግያ ብቸኛ መንገድ ነው መባሉ።
* በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ለአቤቱታ አዲስ አበባ መግባታቸው።
* በባህር ዳር በግንቦት 20 ክፍለ ከተማ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ መቋረጡ።
የሚሉትን ዜናዎችና ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ http://www.patriotg7.org/ ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
Saturday, August 26, 2017
Friday, August 25, 2017
አውሮፓውያን በኤርትራ ላይ የያዙትን አቋም ማለሳለስ መጀመራቸው ህወሃትን ስጋት ላይ ጥሎታል (ኢሳት ዜና–ነሐሴ 19/2009)
ከባድመ ጦርነት ጋር በተያያዘም ይሁን የኢትዮጵያን የነጻነት ሃይሎች ትደግፋለች በሚል ምክንያት ህወሃት በብቸኝነት የያዘው የኤርትራ ፖሊሲ እየከሸፈበት መምጣቱ ግራ እንዳጋባው በኒዮርክ የኢትዮጵያ የተመድ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚሰሩ ምንጮቻችን የላኩን መረጃና ሰነድ ማስረጃዎች ያመለክታሉ።
የሌሎችን ብሄር ተወላጆች ባለማመን በህወሃቱ አባልና በቀድሞው የአለማቀፍ ድርጅቶች ዳይሬክተር ጄኔራል በአዲሱ ሹመታቸው የሱዳን አምባሳደር በሆኑት አቶ ሙሉጌታ ዘውዴ እና በጥቂት የህወሃት ባለስልጣናትና ምሁራን የተረቀቀው የኤርትራ ባለስልጣናትን በአለማቀፍ ፍርድ ቤት የማቆም እንዲሁም በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የሚቀጥልበትንና አጠቃላይ አለማቀፉ ማህበረሰብ በኤርትራ ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንዲያጠናክር የተነደፈው ፖሊሲ ውጤት አልባ እየሆነ ነው።
ለፖሊሲው መክሸፍ ደግሞ ህወሃት በተለይ የተወሰኑ አውሮፓ አገራትን ተጠያቂ እያደረገ ነው። ጄኔቭ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኔ፣ 2008 ዓም በኤርትራ የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን የቀረበው ምክረ ሃሳብ ተግባራዊ እንዲሆን ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ ዘመቻ ያካሄደው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት፣ ከአውሮፓ አገራት ውስጥ ኖርዌይ፣ ጀርመንና ስዊዘርላንድ ከኤርትራ ጋር ስደተኞችን በተመለከተ በጋራ መስራት በመጀመራቸው የአውሮፓ ህብረት ቀደም ብሎ የያዘውን አቋም እንዲያለሰልስ ግፊት ማድረጋቸው ራስ ምታት ሆኖበታል። የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ በኤርትራ ውስጥ የሚሰሩ ባለሀብቶች የኤርትራውያንን ጉልበት እንደሚበዘብዙ ያወጣው ሪፖርት እንዲሁም ግለሰቦኡ በቡድንም ሆነ በተናጠል ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ ያስቀመጠው ምክረ ሃሳብ የአውሮፓ ህብረት አባላትን ባለማስደሰቱ ፣ ህብረቱ በኤርትራ ላይ በሚወሰደው እርምጃ ላይ የተቀዛቀዘ ስሜት እንዲይዝ እያደረገው ነው።
ከአውሮፓ አገራት በተጨማሪ የአረብ አገራት፣ ቻይና እንዲሁም የተወሰኑ የላቲን አሜሪካ አገራት፣ ከአፍሪካ ግብጽ እና በከፊል ሱዳን ለኤርትራ ድጋፍ በመስጠት በምክር ቤቱ ውስጥ ጉዳዩ እንዲቀዛቀዝ ማድረጋቸው የህወሃትን ባለስልጣናት በእጅጉ አስቆጥቷል።
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስትሩ የህወኃቱ ምክትል ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብአዴኑ ሊቀመንበር ደመቀ መኮንን የተጀመረው ጥል ወደ ሃይል እርምጃ ተሸጋገረ። (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የነሐሴ 19 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዜናዎች
* በኦሮሚያ የተጠራው የአምስት ቀን የስራ አድማ ባሳለፍነው እሮብ ተጀመረ።
* በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴ ተቀባይነት ያገኘውና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር የሚያስችለው ኤች አር 128 የተሰኘው የውሳኔ ሀሳብ ለአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ሊቀርብ ነው።
የሚሉትን ዜናዎችና ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ http://www.patriotg7.org/ ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
Thursday, August 24, 2017
🇨🇦የካናዳ መንግስት ዜጎቹ በኢትዮጵያ ባሉ ከተሞች እንዳይዘዋወሩ እገዳ ጣለ። በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እያሳሰበው መሆኑንም ባወጣው ሪፖርቱ አመልክቷል።
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 18/2009
በጅማ ዛሬ የደረሰውና ምናልባትም የመንግስት እጅ ሳይኖርበት አይቀርም የተባለው የቦምብ ጥቃትም በሀገሪቱ ያለውን ያለመረጋጋት ሁኔታ የሚያሳይ መሆኑን መረጃዎቹ አመልክተዋል። በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉት የተኩስ ልውውጦችም ሆኑ ያልተረጋጉ ሁኔታዎች በሀገሪቱ ስላለው የጸጥታ ጉዳይ እንዳጤን አድርጎኛል ብሏል የካናዳ መንግስት ባወጣው ሪፖርቱ። በሪፖርቱ እንደተመለከተው በሀረርና በድሬደዋ እንዲሁም በሆለታና አምቦ መንገዶች አዋሳኝ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጦችና ያለመረጋጋት ሁኔታዎች ይታያሉ። የሆለታና አምቦ ከተሞች ደግሞ በኢትዮጵያው ኦሮሚያ ክልል ማእከል ላይ የሚገኙ ከተሞች ሲሆኑ ለዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ደግሞ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች ናቸው።
በነዚህ አካባቢዎች ያለው ያለመረጋጋት ሁኔታ ወደ ዋና ከተማዋ ብሎም ወደሌሎቹ አካባቢዎች ስላለመዛመቱ ርግጠኛ ሆነን መናገር እንችልም ።እናም ሀገራችን ካናዳ ይህን ጉዳይ በትኩረት እያጤነችው ትገኛለች ብሏል ሪፖርቱ። ከዚህም ጋር ታያይዞ ካናዳ ዜጎቿ በኢትዮጵያ ባሉ አጠቃላይ ከተሞችም ጉዞ እንዳያደርጉ እገዳ ጥላላች።ይህን ያደረገቸውም ይላል ሪፖርቱ በሀገሪቱ ያለው የጸጥታ ጉዳይ አስተማማኝ ባለመሆኑ ነው።
ታላቅ የውይይት መድረክ ለስቶኮልምና ለአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ። እውቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ.ጸሀፊ ተውኔትና የታሪክ ተመራማሪ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ
በ መስከረም 2 ቅዳሜ 2017 በስቶኮልም ስዊድን ስለኢትዮጵያዊነት ተናግሬ ስጨርስ ጥያቄዎችን እመልሳለሁ። የመጻህፍትን ፊርማ ስነስርአት እፈጽማለሁ። በዚህ በመጭው ቅዳሜና እሁድ ደግሞ በለንደን የኢትዮጵያ ኮምዊኒቲ እና ኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያንኑ አካሂዳለሁ። የጀርመን ተልእኮዬን አጠናቅቄ ወደ እንግሊዝ ደርሻለሁ። በመስከረም 11 ለአዲሱ ዐመት በእስራኤል አገር ለአሉ ቤተእስራኤልና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ የክብር እንግዳ ነኝ። የእስሬኤልን ፓርላማ አፈጉባኤ እና ሌሎችን ባለስልጣናት በግሌ ለማናገር ቀጠሮ እየተያዘልኝ ነው። በቴሌቭዥን እና ሬድዮ ቀርቤ በእብራይስጥ ስለተረጎመው የእስሬኤላውያን እና ኢትዮጵያውያን የታሪክ መጽሀፌ አብራራለሁ። ስለ 4000 ዐመት ዝምድናችን እና ግንኙነታችን እገልጣለሁ። በእነዚህ ሁሉ ሀገሮች ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በፕሮግራሜ ላይ እንድትገኙ ጋብዣችኋለሁ።
@Fikre Tolossa ..
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) የነሐሴ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ዜናዎች
* በኦሮሚያ ክልል ከእሮብ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ እየተካሄደ ያለው በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የትራንስፖርት አገልግሎት ከወዲሁ መቋረጡ ተሰማ።
* የዳባት ከተማ ማረሚያ ቤት ተሰብሮ እስረኞች ማምለጣቸው ታወቀ።
* የህወሓት ወታደሮች ስርዓቱን በመክዳት የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይሎችን እየተቀላቀሉ ነው።
* አርባ በመቶ ነጋዴዎች ላይ የተጣለው ግብር በተሳሳተ ግመታ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ጠ/ሚኒስተሩ ቢናገሩም ነጋዴዎች ግን አሁንም እየተቀጡ መሆኑ ተገለጸ።
የሚሉትን ዜናዎችና ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ http://www.patriotg7.org/ ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማስወገድ በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ ለማምጣት ሕዝብን ያማከለ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ (ኢሳት ዜና–ነሐሴ 16/2009
ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማስገደድ ወይንም በማስወገድ በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ ለማምጣት ሕዝብን ያማከለ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ጥሪ አቀረበ።
የኢትዮጵያ ሕልውና ከምንጊዜውም በላይ በፈተና ውስጥ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅትም የተቃውሞ ሃይሎችም መተባበር እንደሚገባቸው አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ከነሐሴ 12 እስከ 14/2009 በዩኤስ አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ከተማ ባካሄደው 4ኛ ጉባኤ ማጠቃለያ ባወጣው በዚህ መግለጫ በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰቱና የቀጠሉ ችግሮችን በዝርዝር ተመልክቷል።
ለሀገራችን ችግር ተመራጩ መንገድ እርቅ መሆኑን አመልክቶ ለዚህም ስርአቱን በመወጠር ወደ እርቅ ማምጣት ካልሆነም ከስልጣን በማስወገድ የስርአት ለውጥ ለማምጣት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አስገንዝቧል።
Tuesday, August 22, 2017
የህወሓት ወታደሮች ስርዓቱን በመክዳት የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይሎችን እየተቀላቀሉ ነው። (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ከተማ ከሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ በነሀሴ ወር 2009 ዓ/ም ቁጥራቸው ከ 11 በላይ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ስርዓቱን በመክዳት በአካባቢው ወደ ሚገኙት የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች ጋር ተቀላቅለዋል ፣ ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ በከተማው በሰዎች ላይ በደልን እና ድብደባን ሲፈፅም በነበረ የህወሓት ወታደር ላይ የከተማ ውስጥ ታጋዬች ጥቃት በመፈፀም በወታደሩ ላይ ጉዳት አድርሰው ይዞት የነበረውን ሙሉ ትጥቅ በመቀማት ወደ ታጋዬች ተቀላቅለዋል። የስርዓቱ ወታደሮች በክህደትና ጥቃት ተፈፅሞበት ትጥቁን በተቀማው ወታደር ምክንያት የከተማውን ህዝብ በማንገላታት ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ባለሆቴሎችና ባለመጠጥ ቤቶች እየታሰሩና እየተንገላቱ ይገኛሉ፣ የአካባቢው ህብረተሰብ እያመረረ እና ስርዓቱን በኃይል ሳይቀር እየታገለ ይገኛል።
በኦሮሚያ ወጣቶች የተጠራውን ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በመላው ኦሮሚያ የሚገኙ ነዋሪዎች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ (ኢሳት ዜና –ነሐሴ 15/2009)
በኦሮሚያ ወጣቶች የተጠራውን ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በመላው ኦሮሚያ የሚገኙ ነዋሪዎች እንዲሳተፉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/አለምአቀፍ ድጋፍ ቡድን ጥሪ አቀረበ።
ከነገ በስቲያ እሮብ ጀምሮ ለአምስት ቀናት በሚቆየውና በመላው ኦሮሚያ የተጠራው አድማ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የግብር ጫናን በመቃወምና በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በልዩ ፖሊስ የተጨፈጨፉ ሰዎችን ለማስታወስ ነው።
የኦፌኮ አለምአቀፍ ቡድን አስተባባሪ አቶ ኔጌሳ ኦዶ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት በኦሮሚያ ባልተቀናጀ ሁኔታ ሲደረግ የነበረው ተቃውሞ በአንድ ወጥ ሁኔታ እንዲካሄድ ከመጪው ረቡእ ጀምሮ ለ5 ቀናት ተጠርቷል።
በኦሮሚያ የወጣቶች ሕብረት ቄሮ የሚል ስያሜ አለው።ቄሮ ማለት በኦሮምኛ ወጣቶች የሚል ትርጉም እንዳለው ይነገራል።
እናም በቄሮ የተጠራው ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ከዚህ በፊትም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በአገዛዙ የሚፈጸሙ ግፍና በደሎችን በመቃወም ባልተቀናጀ ሁኔታ ሲካሄድ መቆየቱን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ አለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን አስተባባሪ አቶ ኔጌሳ ኦዳ ይገልጻሉ።
አቶ ኔጌሳ ኦዳ እንደሚሉት ከነገ በስቲያ ረቡእ ጀምሮ ለ5 ቀናት የሚካሄደው የኦሮሚያ ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ግን ሁሉንም አካባቢዎች የሚያዳርስና ለሁሉም የክልሉ ነዋሪዎች የተደረገ ጥሪ ነው።
የአድማው አላማም ዶክተር መረራ ጉዲና እና አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም ሌሎች የኦፌኮ የፖለቲካ አመራሮች ከእስር እንዲፈቱ ለመጠየቅ ነው።
Monday, August 21, 2017
የላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው ግሩፕ አባላት ለአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች እርዳታ መለገሳቸው ታወቀ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
በትላንትናው እለት ነሃሴ 14 ቀን 2009ዓ.ም (ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው) በሚል ስያሜ በአለም አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ ድህረ-ገጽ በመሰባሰብ ሃገራችንን ከገጠማት አስጊና አሳፋሪ የህልውና አደጋ ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ለአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በግምት ከ35,000 ዶላር በላይ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ እና ልዩ ልዩ መገልገያዎች እርዳታ መበርከቱ ታወቀ ።
በዚሁ የስጦታ ስነስርዓት ላይም የድርጅታችን ከፍተኛ አመራር የሆኑት አርበኛ ታጋይ ነዓምን ዘለቀ በአካል የተገኙ ሲሆን እንዲሁም የአርበኞች ግንቦት 7 ድጋፍ አስተባባሪዎች በተገኙበት የርክክብ ስነስርአቱ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ቨርጅንያ በተባለ ከተማ መፈፀሙ ታውቋል።
( ላንች ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው) የአለም አቀፍ ማህበር ተወካዮች፣ ስጦታውን ለአርበኞች ግንቦት 7 ተወካይ ካስረከቡ በኋላ ለእቃው ማጓጓዣ የሚሆን 700 የ አሜሪካ ዶላር በጥሬ ገንዘብ መስጠታቸውንም ለማወቅ ችለናል ።
የማስተር ፕላኑ ‹‹ማስተር›› አቶ ማቴዎስ በቃኝ እያሉ ነው
ለዋዜማ ዋና አዘጋጅ የደረሱና እየተከታተልናቸው ያሉ ግርድፍ መረጃዎችን እነሆ እናጋራችሁ
-አቃቤ ህግ የፀሐይ ሪልስቴት ባለቤቶች ማንነት እንዲጣራ አዘዘ
-የትራንስ ናሽናል ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ባለቤት አሜሪካ ተሸሽገዋል
የማስተር ፕላኑ ‹‹ማስተር›› አቶ ማቴዎስ በቃኝ እያሉ ነው፡፡
በ130 ዓመታት የአዲስ አበባ ታሪክ ከፍተኛ ውዝግብ የፈጠረው 10ኛው የከተማዋ መሪ ፕላን ‹‹አለቃ›› የነበሩት አቶ ማቴዎስ አስፋው ከአዲስ አበባ ካቢኔ መልቀቅ ፈልገዋል እየተባለ ነው፡፡ ማስተር ፕላኑን ካበጁት መሐል በጉልህ ስማቸው የሚነሳው የማስተር ፕላኑ ፊታውራሪ አቶ ማቴዎስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ግል ሥራቸው ማዘንበል ፈልገዋል ይላሉ ምንጮች፡፡ ኾኖም ለከንቲባው በይፋ የሥራ መልቀቂያ ማስገባት አለማስገባታቸው አልታወቀም፡፡
ከጸደቀ ገና ሁለተኛ ወሩን እንኳ ያላገባደደው የከተማዋ መስተር ፕላን አያሌ ውጣ ውረዶችን አልፎ ነው ለዚህ የበቃው፡፡
አዲስ አበባ ባልጸደቀ ማስተር ፕላን ቢያንስ ሦስት ዓመታት ተመርታለች፡፡ ብዙ ፖለቲካዊ ቀውስ ካስከተለ በኋላ ሐምሌ 6፣ 2009 በዕለተ ሐሙስ የጸደቀው ማስተር ፕላን ከተማዋን ከ10 ወደ 13 ክፍለ ከተሞች ይሸነሽናታል፡፡ የወደጎን መስፋፋት ቀርቶ የጥግግት እድገት ላይ ትኩረት ይደረጋል፡፡ በዚህም ዘለግ ያሉ ሕንጻዎች እንዲገነቡና ብዙዎቹ ሕንጻዎች ከ30 እስከ 60 በመቶ ወለላቸውን ለመኖርያ ቤት እንዲያዉሉ ያስገድዳል፡፡
አቶ ማቴዎስ የማስተር ፕላኑን ዝግጅት ብቻም ሳይሆን እንዲተገበር ጥበቃ የሚያደርገው ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ አስተዳደር የጸደቀ ማስተር ፕላንን መቆጣጠር ብቻ ዓላማውን ያደረገ የኮሚሽን ማሥሪያ ቤት ኖሮ አያውቅም፡፡
ከፍተኛ የኪነ ሕንጻና ከተማ አስተዳደር ባለሞያና የአማካሪ ድርጅት ባለቤት የሆኑት አቶ ማቴዎስ ምን ሆንኩኝ ብለው የአዲስ አበባ ካቢኔን ለመሰናበት እንደፈለጉ ምንጫችን የሚገምተው ነገር የለም፡፡
=================
አቶ ጌታቸው አምባዬ የፀሐይ ሪልስቴት ባለቤቶች ማንነት እንዲጣራ አዘዋል
ከፀረ ሙስና ትግሉ ጋር በተያያዘ የከፍተኛ አመራሩ የማይዳሰስ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም የተባለውና በቻይናዎች ባለቤትነት እንደተያዘ የሚነገርለት ግዙፉ የፀሐይ ሪልስቴት የማንነት ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡ ከሕዝብ በደረሰ ጥቆማ ከቻይኖቹ ጀርባ የኢህአዴግ ቱባ ባለሥልጣናት ሳይኖሩበት አልቀረም የተባለው ይህ ኩባንያ በሁለት የቻይና ግዙፍ ኩባንያዎችና በአንድ ቻይናዊ ሚሊየነር ጥምረት እንደተመሠረተ ነው የሚታወቀው፡፡
ኾኖም እውነታው ሌላ ሊሆን ይችላል በሚል የልዩ አቃቢ ሕጉ አቶ ጌታቸው አምባዬ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ማንኛውም ፀሐይ ሪልስቴትን የተመለከተ መረጃ አንድም ሳይቀር እንዲላክልኝ ሲሉ አዘዋል ይላሉ ውስጥ አዋቂዎች፡፡
የስብሰባ ጥሪ !!
በዶ/ ር ታደሰ ብሩ የክስ ሂደትና በሌሎች ተያያዥ የሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ።
በመሆኑም በዩናይትድ ኪንግደም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በተጠቀሰው ሠዓትና ሥፍራ ተገኝታችሁ አጋርነታችሁን በማሳየት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሚሰጠው አጠቃላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሂደት ላይ ተካፋይ እንድትሆኑ
በአክብሮት ተጋብዛችኋል !!
ትግላችን በተፈጥሮ ሞት ህይወቱ ካለፈው መለስ ዜናዊ ጋር ሳይሆን በህወሐት እና በመለስ የተተከሉብንን ዘረኝነት፣የሃሳብ ደሃነት እና የመንፈስ ድርቀት ከስራቸው ነቅሎ በመጣል ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነው!!! (ከሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ)
ሰሞኑን በሀገራችን ህወሐት/ኢህአዴግ በሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን ስለ መለስ ዜናዊ 5ኛ ሙት ዓመት በተመለከተ እየተሰራጨ ያለው ፕሮፓጋንዳና መሪ ቃል ከዛሬ 50 ዓመት በፊት በሶቪየት ህብረት ምድር የጆሴፍ ስታሊን ሞት ተከትሎ ሲደረግ የነበረውን ታሪክ ያስታውሰናል፡፡ ስታሊን በሀገሩ ጨካኝና አረመኔ ቢሆንም እሱ የሚቆጣጠረው መዋቅር በስልጣን ላይ ስለነበረ በ15ቱም የሶቪየት ግዛቶች አስከሬኑ እየተዘዋወረ በብዙ ሽዎች የሚቆጠር ህዝብ እየወጣ እንዲያለቅስና ለስታሊን አድናቆት እንዲሰጥ ይደረግ ነበር፡፡ ዛሬ የሶቪየት ህብረት ግዛቶች ተገነጣጥለው 15 ቁርጥራጭ ሀገሮች ሆነዋል፤ስታሊንም ሆነ አገዛዙ ክፉ ታሪክ ሆነው አልፈዋል፡፡
ዛሬም በኢትዮጵያ መለስና ህወሐት በፈጠሩትና በሚቆጣጠሩት የመገናኛ ብዙሃን ከዚህ አገዛዝ የተለየ ሀሳብ ስላላቸው ብቻ በሽዎች መገደላቸውን ሰምተን ሳናበቃና የተለየ ሃሳብ ያንፀባረቁ በሽዎች በየእስር ቤቱ ታግተው በሚገኙባት፣ ዜጎች በዘር ጥላቻና በጎሰኝነት ከመኖሪያ ቀያቸው በሚፈናቀሉባት ሀገር ሟቹ መለስ ዜናዊ "የሃሳብ ድህነትን ያሸነፈ መሪ" በሚል መሪ ቃል ሙት ዓመቱ በአገዛዙ በመዘከር ላይ ይገኛል፡፡ ሀሳብን እንደ ጦር የሚፈራው ህወሐት/ኢህአዴግ ይህንን መሪ ቃል ሲያስተላልፍ አንድም የኢትዮጵያን ህዝብ በመናቅ ነው ያለዛም የሀሳብ ድህነት ምን እንደሆነ አለማዎቅ ነው:: ከዚያም ካለፈ ሕወሃት ከወደቀና ስልጣናችን ካበቃ በኋላ ስለእኛ የሚወራ ምንም ነገር የለም ከሚል መጭውን የመፍራት የስነ ልቦና ቀውስ ነው፡፡ በእኛ እምነት፡-
-1. በመለስና በህወሐት/ኢህአዴግ ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ የዜግነት ስልጣን የለውም፡፡ እነሱ በፃፉት ህገ መንግስት የስልጣን ባለቤት ዜጎች ሳይሆኑ "ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች" የሚባሉት ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ እነዚሁ "ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች" ከፈለጉ እንዲገነጠሉ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
Sunday, August 20, 2017
በኦሮሚያ በቀጣዩ ሳምንት አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ መጠራቱ ታወቀ (ኢሳት ዜና –ነሐሴ 12/2009)
በኦሮሚያ በቀጣዩ ሳምንት አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ መጠራቱ ታወቀ።
በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች በህቡዕ በመንቀሳቀስ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡእ ጀምሮ ለ5ቀናት የሚቆይ አድማ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
በሌላ በኩል በአማራ ክልል በተለይም ባህርዳርን ጨምሮ በምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ሌላ ዙር አድማና የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊደረግ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
ለነሃሴ 10 ተራዝሞ በነበረው የግብር መክፈያ ቀነ ገደብ አብዛኛው የንግዱ ማህብረሰብ ባለመክፈሉ በአንዳንድ አካባቢዎች ውጥረት መንገሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ሱቆች እየታሸጉ ነው። የነጋዴዎች እስርም ቀጥሏል።
ከሚቀጥለው ረቡእ ጀምሮ ለ5 ቀናት የሚቆይ አድማ በመላው ኦሮሚያ የተጠራው የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣በሕዝቡ ላይ ያለአግባብ የተጫነውን ግብር በመቃወምና ከሶማሌ ክልል ጋር በተያያዘ በተነሳው የወሰን ግጭት የተገደሉትን ለማስታውስ ነው።
ከዚህ ቀደም የነበሩ አድማዎች በውስን ቦታዎች የሚካሄዱና የተዘበራረቁ ነበሩ።በተለይም በአምቦ በወሊሶና በተወሰኑ የኦሮሚያ አካባቢዎች ከግብርና ከፖለቲካ እስረኞች ጋር በተያያዘ የተካሄዱ አድማዎች መጠነኛ ግጭቶች ከደረሱ በኋላ በአገዛዙ ታጣቂዎች የሃይል እርምጃ ለማፈን ሙከራ ሲካሄድባቸው የነበሩ ናቸው።
አሁን ከመጪው ረቡእ ጀምሮ በኦሮሚያ ቄሮዎች ወይም ወጣት ስብስቦች የተጠራው አድማ ግን ለ5 ቀናት በኦሮሚያ እንደሚካሄድ ያወጡት መግለጫ ያመለክታል።
በዚሁም ሁሉም የንግድ መደብሮች ተሽከርካሪዎችና የሕዝብ ማመላለሻዎች ከስራ ውጭ እንደሚሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
የኦሮሚያ ወጣቶች የጠሩት አድማ ዶክተር መረራ ጉዲና፣አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ነው ተብሏል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ
የነሐሴ 14 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዜናዎች
* በወልድያ ነጋዴዎች ግብር አንከፍልም በሚለው አቋማቸው እንደጸኑ መሆኑ።
* ኮንሶና ጎፋ ሳውላ በውጥረት ማሳለፋቸው ተገለጸ።
* ሱዳን በአባይ ግድብ ዙሪያ የያዘችውን አቋም እያለሳለሰች መሆኑ የሚያመላክት መግለጫ መስጠቷ።
Saturday, August 19, 2017
በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት መባባሱ ተገለጸ (ኢሳት ዜና –ነሐሴ 12/2009)
በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት መባባሱ ተገለጸ።
በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሃት የተለየ ድጋፍ የሚደረግለት የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አወዛጋቢ በተባሉ ቀበሌዎች የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ግድያ፣ ድብደባና አስገድዶ መድፈር እየፈጸመ መሆኑንም ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ኦብነግ ለኢሳት እንዳስታወቀው የህወሃት መንግስት በሶማሌ ልዩ ሃይልና በስውር ባስታጠቃቸው የኦህዴድ ሚሊሺያዎች አማካኝነት የእርስ በእርስ ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ነው ብሏል።
ከዚህ ግጭት ጀርባ የህወሃት እጅ እንዳለበት የጠቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ኦብነግ ህወሃት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ግጭቱ መቀጠሉ አይቀርም ብሏል።
ኦብነግ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረጉንና በህወሃት ሰራዊት ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሱ ውጊያዎች መካሄዳቸውንም በመግለጪያው ጠቅሷል።
በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ቀሪ መከላከያ ምስክሮችን የመስማት ሂደት ለቀጣይ አመት ተላለፈ። (ነሀሴ 12/2009)
★የማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ጥፋተኛ ተብለው በተግሳፅ ታልፈዋል።
★አቃቤ ህጉ ጨጓራ ስላለብኝ ምሳ ካልበላሁ መቀጠል አልችልም ብሎ መስቀለኛ ጥያቄ ሳይጨርስ የጠዋቱ ችሎት ተቋልጧል።
★ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ በምስክርነት የተመዘገቡ ባለስልጣናት በቀጣይ ቀጠሮ እንዲቀርቡ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ታዟል።
ነሃሴ 12/2009 የእነ ጉርሜሳ አያና መዝገብን ለማየት የተያዘ የአመቱ የመጨረሻ ቀን ነበር። ችሎቱ በቅድሚያ ከማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ጋር በተያያዘ ይሰጣል ያለውን ትእዛዝ ከተገለፀ በኋላ ነው መከላከያ ምስክሮችን መስማት የቀጠለው።
ከማረሚያ ቤት እንዲቀርቡ የተደረጉት ዋና ሱፐር ኢንቴንደንት አሰፋ ኪዳኔ እንዲሁም በ9/12/2009 ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ከቤተሰብ የመጣ ምግብ እንዲበሉ ካዘዘ በኋላ ትእዛዙን አልፈፅምም ያሉት ኃላፊ ዋና ኦፊሰር ገብሬ አለማ በችሎት እንዲቆሙ ተደርጎ የተሰጠው ትእዛዝ ተነቧል። "ጉዳዩን ስንመረምረው ዋና ኦፊሰር ገብሬ አለማ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ሳያከብሩ ቀርተዋል። ይህም የሆነው በኃላፊያቸው ዋና ሱፐር ኢንቴንደንት አሰፋ ኪዳኔ ትእዛዝ መሆኑን ገልፀዋል። በሁለቱ ሰዎች የፍርድ ቤት ትእዛዝ አልተከበረም። ስለዚህ ጥፋት ተፈፅሟል። ጥፋት እንደሆነም ታምኖ ይቅርታ ተጠይቆበታል። የማረሚያ ቤት ደንብ ተብሎ በኃላፊው የተነበበው ማረሚያ ቤቱ የተመጣጠነ ምግብ ማቅረብ እንዳለበት ይገልፃል። በእለቱ የቀረበላቸው ግን ተመጣጣኝ ምግብ አይደለም። ደረቅ ዳቦ ያለምንም ማወራረጃ ነው የተሰጣቸው። ያቀረቡት ምክንያት የሚያዋጣ የሚያወላዳ አይደለም። ስለሆነም ለተፈፀመው ጥፋት ይቅርታም ስለተባለበት አስተማሪ ይሆናል በሚልም የወሰነው ቅጣት አለ። ቅጣቱም ተግሳፅ እንዲሆን ተስማምተናል። ወደፊት ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ።" በማለት ትእዛዙን ያነበቡት የግራ ዳኛ አቶ ግርማ ደባሱ ፤ ከዚህ በኋላም በዚህ ችሎትም በሌላ ችሎትም ፍርድ ቤት የሰጠውን ትእዛዝ ባይጥማቸውም እየመረራቸውም ቢሆን መውሰድ እንዳለባቸው፤ በተለይ ደግሞ ኦፊሰር ገብሬ አለማ በተደጋጋሚ ለችሎቱ የሚሰጡት ምላሽ የፍ/ቤቱን ክብር በሚመጥን መልኩ አለመሆኑን ስለሆነም እንዲያስተካክሉ ወይም ደግሞ ይሄን ተረድቶ የሚሰራ ሰው እንዲላክ እንዲደረግ ለዋና ሱፐር ኢንቴንዳንት አሰፋ ኪዳኔ ገልፀውላቸዋል። የተነበበው የቅጣት ትእዛዝም ለማረሚያ ቤቱ እንዲደርስ እንደሚደረግ ተገልፇ ኃላፊዎቹ ተሰናብተዋል።
“ለጀግንነቴ በተከፈለኝ ወሮታ እያዘንኩ እኖራለሁ”
መንግሥት እንደ ጠላት፣ ጡረታዬን መከልከሉ ያሳዝነኛል
· የሶማሊያን ወራሪ ሃይል ድባቅ የመቱ ጀግኖች ታሪክ ተቀብሯል
· ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሚሰጠው ትርጉም ተዛብቷል
· ለሶማሊያ የምናደርገው ድጋፍና እርዳታ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል
@አዲስ አድማስ
የዛሬ 40 ዓመት የዚያድ ባሬ አገር ሶማሊያ፤ እንደዛሬው የፀና መንግስት የሌላት፣ ደካማ ጎረቤታችን አልነበረችም። ከጦቢያ እገዛና ድጋፍ የምትሻ ምስኪን አገርም ፈፅሞ አልነበረችም፡፡ ይልቁንስ ኮሙኒስቷ ሶቭየት ህብረት እስከ አፍንጫዋ ድረስ በዘመኑ የጦር መሳሪያ ያስታጠቀቻት የፈረጠመች አገር ነበረች። የመሪዎቿም ዓላማ በዙሪያዋ ያሉትን ጨፍልቃ “ታላቂቱን ሶማሊያ” መፍጠር ብቻ ነበር፡፡ ለዚህም ነው የአገሪቱ ፕሬዚዳንትና የመከላከያ ሚኒስትር በነበሩት ዚያድ ባሬ መሪነትና አዋጊነት ኢትዮጵያን በኃይል ለመውረር የተነሳችው፡፡
በአዲስ የመንግስት ምስረታ ሽግግር ላይ ለነበረችው ኢትዮጵያ ወቅቱ ፈታኝና አስቸጋሪ ነበር፡፡
ቢሆንም የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም፤ ህዝቡ የአገሩን ዳርድንበርና ሉአላዊነት ከወራሪዋ ሶማሊያ እንዲከላከል ላደረጉት የእናት አገር ጥሪ ያገኙት ምላሽ፤ ፈጣንና በአገር ፍቅር ወኔ የተሞላ ነበር ይላሉ - በወቅቱ በጦርነቱ ላይ ከተሳተፉት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አንዱ የሆኑት መቶ አለቃ በቀለ በላይ፡፡ የያኔው ጎረምሳ፣ ለእናት አገር ጥሪው ምላሽ ሲሰጡ፣ ገና የ19 ዓመት ወጣት ነበሩ። ከ3 መቶ ሺ ሚሊሻዎች አንዱ የነበሩት መቶ አለቃ በቀለ፣ የሳቸው ክፍለ ጦር ተመርጦ በአየር ወለድ መሰልጠኑን ያወሳሉ፡፡ በዕብሪት አብጦ ኢትዮጵያን በኃይል የወረራትን የዚያድ ባሬ ሰራዊት፤ መክቶና ድባቅ መትቶ ለመመለስ፣ አያሌ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አልቀዋል፡፡
የዕድል ጉዳይ ሆኖ፤ በህይወት ተረፉ እንጂ መቶ አለቃ በቀለም ከሞት በመለስ ያልቀመሱት አበሳና ፍዳ የለም - ነፃነቷ የተጠበቀች አንዲት ኢትዮጵያን ለማቆየት፡፡ መቶ አለቃ በቀለ፣ ከሶማሊያ ጋር በነበረው አሰቃቂ ፍልሚያ፣ በሰሩት የጦርነት ጀብዱ፣ የአገሪቱን ብሔራዊ የጦር ሜዳሊያ ኒሻን፣ ከኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እጅ ተሸልመዋል፡፡ በአገር ተከብረዋል ተወድሰዋልም፡፡
የፊንፊኔ ደላላ: ከአሳሪ ወገን ነዎት ከታሳሪ?
ጤና ይስጥልኝ፣ ጌታዬ!
ገረመው ነኝ፡፡ እሳት የላስኩ የፊንፊኔ ደላላ፡፡ ምስጉን ጉዳይ–ገዳይ ስለመሆኔ እግዜርምሰይጣንም ያውቃሉ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ መሆኔን ድሪባ ኩማም ያውቃል፡፡
ዉሎዬ ብሔራዊ፣ አመሻሼ ‘አብዮታዊ‘…ሄሄሄ…(ምን ማለቴ እንደሆነ ይገባዎታልመቼስ!)
ላየን ባር ቤቴ፣ ቴሌ ባር ግዛቴ…
ጥሎብኝ አልረጋም፡፡ ካዛንቺስ ነው ሲሉኝ ሳሪስ፣ ቀበና ነው ሲሉኝ ባምቢስ!! ድሮስ የፊንፊኔ ደላላ ምን ቀልብ አለው ብለው ነው!?
እርስዎ ግን እንዴት ከርመዋል? ኸረ ለመሆኑ! ከታሳሪ ወገን ነዎት ወይስ ከአሳሪ?
አለምክንያት አልጠየቅክዎትም፡፡ ሰሞኑን ከታሳሪ ወገን የሚመደቡ ዋና ዋና ደንበኞቼ በሆነ ባልሆነው እየደነገጡብኝ ብቸገር ጊዜ ነው…፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልካቸውበነዘራቸው ቁጥር ይንጰረጰራሉ፡፡ ቦርጫቸው ሳይቀር ነው የሚንዘረዘር…፡፡ ይህን ጊዜ ያን የታፈነ የደላላ ሳቄን እለቀዋለሁ…፡፡ ‹‹ገረመው! ምን አለ በለን ማዕበሉላንተም አይመለስም›› ይሉኛል፡፡ ይበልጥ እስቃለሁ፡፡ ‹‹እኔኮ የመንግሥትን አሠራር ተከትዮ ነው የምደልለው›› እያልኩ አሾፋለሁ፡፡ ‹‹ለአገልግሎቴ ቫት የምቆርጥብቸኛው የፊንፊኔ ደላላ ነኝ?›› እያልኩ እፎልላለሁ፣ እቀደልዳለሁ፡፡ ኾኖም አይስቁልኝም፡፡ እውነቱን ልንገርዎ አይደል? ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሳቅ ያቆሙ ደንበኞቼበዝተዋል፡፡ ከነዚህ መሐል ጋሽ ገምሹ በየነ ቦቴ አንዱ ነው፡፡
ከወር በፊት ኦፊስ ባር ተገናኝተን ነበር፡፡ የእኔ ነገር ሆኖበት እንጂ እሱ መቼ በጄ ይልና፡፡ ቢራም በግድ ነው፡፡ በዚ
Thursday, August 17, 2017
Tuesday, August 15, 2017
የታጋይ አግባው ሰጠኝ ህይወት የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታደጋት ትጮሃለች!!!
ከሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ከቀን ቀን የሚሰማው በአገዛዙ በሚፈፀም በደልና ግፍ ምክንያት ጩኸትና ዋይታ ብቻ ሆኗል፡፡መገለጫችንም እንዲሆን የተፈረደብን ይመስላል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስለ አግባው ሰጠኝ የምንሰማውም የሚያረጋግጥልን ይህንኑ ነው፡፡
ስለ አግባው ሰጠኝ ከአያያዙ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ እየደረሰበት ያለው ግፍና በደል በተለያየ ጊዜ የተገለፀ ስለሆነ ሰሚ ስለሌለ መደጋገሙ ዋጋ የለውም፡፡ የአሁኑን ልዩ የሚያደርገው በደርግ ጊዜ ሲፈፀም እንደነበረው አንድን በስርዓቱ ያልተፈለገ ሰው አብዮታዊ እርምጃ ይወሰድበት እየተባለ ያለቁትን ኢትዮጵያውያን የሚያስታውስ ድርጊት አግባው በማረሚያ ቤቱ በደል እየደረሰበት እንደሆነ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የአግባው ሰጠኝን አያያዝ እንዲያሳውቀው በጠየቀው መሰረት የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለፍርድ ቤቱ በፃፈው ደብዳቤ አረጋግጠናል፡፡
የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፡-
1.አግባው ሰጠኝ የፖሊስ መሳሪያ ለመንጠቅ እንደሚሞክር
2.ከእስር ቤት ሰብሮ ለማምለጥ እቅድ እንደሚያወጣ
3.በእስር ቤቱ ውስጥ ሁከት እንዲፈጠር እንደሚሰራ
4.አግባው ከማረሚያ ቤቱ አቅም በላይ እንደሆነ በፃፈው ደብዳቤ ላይ ገልጧል፡፡
በጥንቃቄ ለተገነዘበው የደብዳቤው ዓላማ በአግባው ላይ ለምንወስደው እርምጃ ለፍርድ ቤቱ አሳውቀናል ለማለት ማረሚያ ቤቱ ለራሱ የሰጠው ነፃ ፈቃድ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የቀረ ነገር ቢኖር በአግባው ላይ የሚወሰደው ነፃ እርምጃ መቼ፣እንዴትና በምን ሁኔታ እንደተፈፀመ መርዶ መስማት ብቻ ነው፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ የነሐሴ 09 ቀን 2009 ዓ.ም. ዜናዎች
* በአርበኞች ግንቦት7 እና በስርዓቱ ወታደሮች መካከል ውግያ ተካሄደ።
* በምስራቅ ሀረርጌ የሶማሌ ልዩ ሃይል ከኦሮሞ ተወላጆች ጋር ሲታኮሱ መዋላቸው ታወቀ።
* በተለያዩ የአገሪቱ ክተሞች የነጋዴዎች አድማ እንደቀጠለ መሆኑ ታወቀ።
እንዲሁም ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ መዓዛው ጌጡ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ አለ፡፡ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡ www.patriotg7.org
( የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) የነሐሴ 09 ቀን 2009 ዓ.ም.
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ መዓዛው ጌጡ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፡፡
* በአርበኞች ግንቦት7 እና በስረዓቱ ወታደሮች መካከል ውግያ ተካሄደ።
* በምስራቅ ሀረርጌ የሶማሌ ልዩ ሃይል ከኦሮሞ ተወላጆች ጋር ሲታኮሱ መዋላቸው ታወቀ።
* በተለያዩ የአገሪቱ ክተሞች የነጋዴዎች አድማ እንደቀጠለ መሆኑ ታወቀ።
Monday, August 14, 2017
በኢትዮጵያ 16 የጥጥ እርሻ ልማት ድርጅቶች ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ተጭበረበርን አሉ (ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009)
በኢትዮጵያ 16 የጥጥ እርሻ ልማት ድርጅቶች በአንድ የቱርክ ኩባንያ ከ21 ሚሊየን ብር በላይ መጭበርበራቸውን አመለከቱ።
የጥጥ ልማት ድርጅቶቹ በደረቅ ቼክ የተጭበረበሩት ኤልሴ አዲስ በተባለ የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ነው።
የቱርኩን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኩባንያው ባለቤት 1 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ብር ተበድሮ መጥፋቱን አስታውቋል።
ኢትዮጵያውያኑ የጥጥ አምራቾች በጠራራ ጸሃይ በኢንቨስትመንት ስም በመጣ የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ 21 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በደረቅ ቼክ ተጭበርብረናል ይላሉ።
Subscribe to:
Posts (Atom)