Tuesday, August 15, 2017

የታጋይ አግባው ሰጠኝ ህይወት የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታደጋት ትጮሃለች!!!


ከሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ከቀን ቀን የሚሰማው በአገዛዙ በሚፈፀም በደልና ግፍ ምክንያት ጩኸትና ዋይታ ብቻ ሆኗል፡፡መገለጫችንም እንዲሆን የተፈረደብን ይመስላል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስለ አግባው ሰጠኝ የምንሰማውም የሚያረጋግጥልን ይህንኑ ነው፡፡
ስለ አግባው ሰጠኝ ከአያያዙ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ እየደረሰበት ያለው ግፍና በደል በተለያየ ጊዜ የተገለፀ ስለሆነ ሰሚ ስለሌለ መደጋገሙ ዋጋ የለውም፡፡ የአሁኑን ልዩ የሚያደርገው በደርግ ጊዜ ሲፈፀም እንደነበረው አንድን በስርዓቱ ያልተፈለገ ሰው አብዮታዊ እርምጃ ይወሰድበት እየተባለ ያለቁትን ኢትዮጵያውያን የሚያስታውስ ድርጊት አግባው በማረሚያ ቤቱ በደል እየደረሰበት እንደሆነ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የአግባው ሰጠኝን አያያዝ እንዲያሳውቀው በጠየቀው መሰረት የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለፍርድ ቤቱ በፃፈው ደብዳቤ አረጋግጠናል፡፡No automatic alt text available.
የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፡- 
1.አግባው ሰጠኝ የፖሊስ መሳሪያ ለመንጠቅ እንደሚሞክር
2.ከእስር ቤት ሰብሮ ለማምለጥ እቅድ እንደሚያወጣ
3.በእስር ቤቱ ውስጥ ሁከት እንዲፈጠር እንደሚሰራ
4.አግባው ከማረሚያ ቤቱ አቅም በላይ እንደሆነ በፃፈው ደብዳቤ ላይ ገልጧል፡፡
በጥንቃቄ ለተገነዘበው የደብዳቤው ዓላማ በአግባው ላይ ለምንወስደው እርምጃ ለፍርድ ቤቱ አሳውቀናል ለማለት ማረሚያ ቤቱ ለራሱ የሰጠው ነፃ ፈቃድ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የቀረ ነገር ቢኖር በአግባው ላይ የሚወሰደው ነፃ እርምጃ መቼ፣እንዴትና በምን ሁኔታ እንደተፈፀመ መርዶ መስማት ብቻ ነው፡፡
ለይስሙላም ቢሆን በህግ እተዳደራለሁ በሚል አገዛዝ ውስጥ እንደዚህ አይነት ደብዳቤ በቁጥጥሩ ስር ያለን ግለሰብ በተመለከተ ተፅፎ ማየት እጅግ የሚያሳዝንም የሚያስገርምም ነው፡፡ ይህንን ደብዳቤ የበለጠ አስገራሚ የሚያደርገው በመጀመሪያ በተጠረተረበት ወንጀል ከሁለት ዓመት በላይ ከታሰረ በኋላ ምንም አይነት ማስረጃ ባለመገኘቱ ነፃ የተባለንና በዚህ አልበቃ ብሎ በሀሰት በተቀነባበረ ክስ በሲቃይ ላይ የሚገኝን የፖለቲካ እስረኛ መሆኑ ነው፡፡
አግባው ሰጠኝ በጥቂቱም ቢሆን ምርጫ በሚመስለው ምርጫ 97 ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲን በመወከል በምርጫ አሸንፎ ለአምስት ዓመታት የፓርላማ አባል የነበረና በኋላም በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል በመሆን እስር ቤት እስከገባበት ጊዜ ድረስ ለሀገሩና ለወገኑ ያመነበትን ነገር በድፍረት የሚናገር ቆራጥ ወጣት ታጋይ ነው፡፡ በአግባው ላይ በአገዛዙ የሚደርስበት ሲቃይ ሁሉ በዚሁ በፖለቲካ አመለካከቱ መሆኑን ከተፃፈው ደብዳቤ በግልፅ መረዳት ይቻላል፡፡ 
ስለሆነም በፖለቲካ እስረኛ አግባው ሰጠኝ ላይ ከላይ የተገለፀው መንግስታዊ ውንብድና ከመፈፀሙ በፊት የኢትዮጵያ ህዝብ የዚህን ወጣት ፖለቲከኛ ህይወት በመታደግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ነሐሴ 09 ቀን 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባImage may contain: 1 person, standing

No comments:

Post a Comment