Thursday, August 24, 2017

ታላቅ የውይይት መድረክ ለስቶኮልምና ለአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ። እውቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ.ጸሀፊ ተውኔትና የታሪክ ተመራማሪ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ


በ መስከረም 2 ቅዳሜ 2017 በስቶኮልም ስዊድን ስለኢትዮጵያዊነት ተናግሬ ስጨርስ ጥያቄዎችን እመልሳለሁ። የመጻህፍትን ፊርማ ስነስርአት እፈጽማለሁ። በዚህ በመጭው ቅዳሜና እሁድ ደግሞ በለንደን የኢትዮጵያ ኮምዊኒቲ እና ኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያንኑ አካሂዳለሁ። የጀርመን ተልእኮዬን አጠናቅቄ ወደ እንግሊዝ ደርሻለሁ። በመስከረም 11 ለአዲሱ ዐመት በእስራኤል አገር ለአሉ ቤተእስራኤልና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ የክብር እንግዳ ነኝ። የእስሬኤልን ፓርላማ አፈጉባኤ እና ሌሎችን ባለስልጣናት በግሌ ለማናገር ቀጠሮ እየተያዘልኝ ነው። በቴሌቭዥን እና ሬድዮ ቀርቤ በእብራይስጥ ስለተረጎመው የእስሬኤላውያን እና ኢትዮጵያውያን የታሪክ መጽሀፌ አብራራለሁ። ስለ 4000 ዐመት ዝምድናችን እና ግንኙነታችን እገልጣለሁ። በእነዚህ ሁሉ ሀገሮች ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በፕሮግራሜ ላይ እንድትገኙ ጋብዣችኋለሁ።
@Fikre Tolossa ..Image may contain: 1 person, text

No comments:

Post a Comment