Thursday, August 31, 2017

ኢትዮጵያ አደገኛ በሆነ አቅጣጫ እየተወሰደች በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ በስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት ለማስወገድ መታገል ይኖርበታል ሲል የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ገለጸ። ኢሳት ዜና –ነሀሴ 24/2009) የኢትዮጵያ ለም መሬቶችን ለሱዳን ለ10ዓመታት በውሰት ለመስጠት በድብቅ ከስምምነት መደረሱን በመጥቀስ ጥሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ፡ የህወሀት መንግስት የጥፋት ግስጋሴ በአስቸኳይ ካልተገታ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው ብሏል። የታላቋን ትግራይ ካርታ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን በማሳየት ህዝቡ እንዲለማመደው እየተደረገ መሆኑና፡ ጎንደርን ለሶስት የመሸንሸኑ እርምጃ የዚሁ የታላቋ ትግራይ ምስረታ አካል ነው ብሏል የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ።

No comments:

Post a Comment