Monday, August 21, 2017

የላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው ግሩፕ አባላት ለአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች እርዳታ መለገሳቸው ታወቀ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


በትላንትናው እለት ነሃሴ 14 ቀን 2009ዓ.ም (ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው) በሚል ስያሜ በአለም አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ ድህረ-ገጽ በመሰባሰብ ሃገራችንን ከገጠማት አስጊና አሳፋሪ የህልውና አደጋ ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ለአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በግምት ከ35,000 ዶላር በላይ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ እና ልዩ ልዩ መገልገያዎች እርዳታ መበርከቱ ታወቀ ።Image may contain: text
በዚሁ የስጦታ ስነስርዓት ላይም የድርጅታችን ከፍተኛ አመራር የሆኑት አርበኛ ታጋይ ነዓምን ዘለቀ በአካል የተገኙ ሲሆን እንዲሁም የአርበኞች ግንቦት 7 ድጋፍ አስተባባሪዎች በተገኙበት የርክክብ ስነስርአቱ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ቨርጅንያ በተባለ ከተማ መፈፀሙ ታውቋል።
( ላንች ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው) የአለም አቀፍ ማህበር ተወካዮች፣ ስጦታውን ለአርበኞች ግንቦት 7 ተወካይ ካስረከቡ በኋላ ለእቃው ማጓጓዣ የሚሆን 700 የ አሜሪካ ዶላር በጥሬ ገንዘብ መስጠታቸውንም ለማወቅ ችለናል ።
በእርክክቡ ወቅትም የላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው ዋና አድሚን በቃል አቀባያቸው በኩል ከአውሮፓ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል።
(ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው)
በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ አህጉር እና ሀገሮች በማህበራዊ ድህረ ገፅ የተሰባሰብን ኢትዮጵያውያን፣ ህዝባችንን ከወያኔ የጭካኔ አገዛዝ ለማላቀቅ የሚታገሉትን የነፃነት ሃይሎች በምንችለው ሁሉ በቀጣይነት ለመርዳት ቃል ገብተናል።
አሁንም ይህንን ግምቱ 35,000 ዶላር የሚሆን የመጀመሪያ እርዳት ህክምና መስጫ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ማቴሪያሎችን ስናበረክት በመላው የማህበራዊ ድህረ- ገፅ አባላት እና የክብር አባሎቻችን ስም የተሰማንን ልባዊ ደስታ እንገልፃለን።
ወደፊትም ይበልጥ ተደራጅተን በመጠናከር ከህዝባችን ጎን ለመቆም በድጋሚ ቃል እንገባለን።
ከዚህም በላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህዝባችን ህልውና ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመከላከል እና ሀገራችንን ከመፍረስ ለመታደግ እንዲተባበር በዚህ አጋጣሚ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በተጨማሪ የእምነት አባቶች እና እናቶች ፤ የእውቀት እና የእድሜ ባለፀጋዎች እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ አክቲቪስቶች እና የመገናኛ ብዙሃን ለሃገራችን ህዝብ አንድነት ጉልበት መፈጠር የበኩላቸውን ወሳኝ ድርሻ ለማበርከት ይተባበሩልን ዘንድ በአጽንዖት እንጠይቃለን።
ለህዝባችን የአንድነት ጉልበት መፈጠር የሚረዱ መድረኮችንም አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉ ለማመቻቸት በማህበራችን ስም ከወዲሁ ቃል እንገባለን።
ፈጣሪ ሃገራችንን ከዚህ የህልውና አደጋ ይጠብቅልን።
አሜን።
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው!!!
የቡድኑ መሪ • ዲና ኦል
በማለት መልዕክታቸውን ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ አስተላፈዋል፡፡

No comments:

Post a Comment