Sunday, August 6, 2017

ESAT መረጃ


በባህርዳር የቦንብ ጥቃቱን ተከትሎ በአሁኑ ሰአት የደህንነት ሃይሎች ስብሰባ ላይ ሲሆኑ፣ ከጎርደማ ገብርኤል አካባቢ የተነሱ በርካታ ወታደሮች ወደ መሃል ከተማ በመግባት ላይ ናቸው። ሌሊቱን ወጣቶችን ለማፈስ እንቅስቃሴ ሊጀመር ስለሚችል ወጣቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የደህንነት ምንጮች ምክራቸውን ለግሰዋል። ስብሰባው እንደተጠናቀቀ ውሳኔውን እየተከታተለን እናሳውቃለን። 
የነሃሴ አንዱን የሰማእታት ቀን ለመዘከር ጥሪ ያስተላልፉትን የከተማዋ ወጣቶች ለመያዝ ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲደረግ ነበር። በተለይ ዛሬ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ከተማዋን በመውረር በህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ሙከራ ሲያደርጉ ውለዋል። 
የብአዴን ዋና ጸሃፊ አቶ አቶ አለምነው መኮንን በቅርቡ በባህርዳር የሚካሄደውን ጥቃት ለመቆጣጠርና ምንጩን ለማግኘት አለመቻሉን በምሬት መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል

No comments:

Post a Comment